@melakufekadu1: አራቱ የአእምሮ ምጥቀቶች! ******** የሰውን ልጅ የአእምሮ ምጥቀት በአራት መንገዶች ልንመዝነው እንችላለን... 1. Intelligence Quotient (IQ) ይህ ቀጥታ የሒሳብ ጥያቄዎችን ከመፍታት ወይም ከማስታወስ ችሎታችን ጋር ይገናኛል! 2. Emotional Quotient (EQ) የስሜት ብልሃትን ያመላክታል። ከሰዎች ጋር በሰላም ትኖራለህ ወይ? ሃላፊነት ይሰማሃል ወይ? ሌሎችን ታከብራለህ? ታማኝና ለሰው አሳቢ ነህ? 3. Social Quotient (SQ) ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለህን ተግባቦትንም ትመዝንበታለህ። ብዙ ወዳጆች አሉህ? ወዳጅነትህስ ዘላቂነት ያለው ነው? ቀልድ አዋቂ፣ ተናግሮ አሳማኝስ ነህ? 4. Adversity Quotient (AQ) ይሄኛው መጥፎ ጊዜያቶችህን የምታሳልፍበትን ብርታት ያመላክታል። በቀላሉ ተስፋ ትቆርጣለህ? ወይስ ወደፊት ገፍተህ ትጓዛለህ? ብዙዎቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ የዩንቨርስቲ ትምህርት እስክናጠናቅቅ ድረስ የተሻለ IQ እንዲኖረን ታትረናል። በከፍተኛ ውጥረትና ጭንቀትም ውስጥ ሆነን ሃያ አመታትን ካሳለፍን በኋላ የአእምሯችንን ልህቀት የሚያሳይ ወረቀት እንቀበላለን። ሆኖም ይህ በእውኑ አለም ለሚገጥመን ፈተና በቂ አይደለም። ከፍተኛ IQ መያዝ ብቻውን ትርጉም አልባ ነው። የተሻለ ማህበራዊ ተግባቦት ያላቸው ሰዎች ከዋንጫ ተሸላሚ ተማሪዎች በተሻለ ስኬታማ ሁነው እናገኛቸዋለን፤ እናም አንድ ሰው የስሜት ብልሃት፣ ማህበራዊ ተግባቦትን እና በችግር ጊዜ የማለፍ ብርታትን አጣጥሞ ከተጓዘ የፈለገበት ስፍራ መድረስ ይችላል።
መላኩ ፍቃዱ
Region: ET
Sunday 09 November 2025 19:41:33 GMT
Music
Download
Comments
amanu@nine :
ከዚህ በላይ ሁሉ፡እራሳችን የማናውቀው የተሰጠን ረቂቅ ና ምጡቅ ሰማያዊ ጥበብ ተሰጥተናል በልዑል እግዚአብኄር አምላካችን ልዩ ና ወደር የሌለው ስጦታ🥰
2025-11-10 17:07:33
3
praise the lord. :
thanks
2025-12-02 16:01:39
0
zz :
ok
2025-11-11 10:45:06
0
kindalem :
good idea thank you
2025-11-12 20:28:35
0
ሰላም ለኢትዮጵያ :
💯💯💯❤❤❤
2025-11-10 05:39:28
1
estiph ki :
🥰🥰🥰
2025-11-11 18:23:12
0
BBB@ :
👍
2025-11-11 07:39:06
0
simon :
🥰🥰🥰🥰
2025-11-10 19:38:05
0
Komete Birhanu :
🥰🥰🥰🥰
2025-11-10 17:09:40
0
Abega fc barcelona :
🥰🥰🥰
2025-11-10 03:48:35
0
To see more videos from user @melakufekadu1, please go to the Tikwm
homepage.