@m_uhammet4: بفضل الله اقوى فرشه صيفي💪✨ #X_LARGE🔥🦅 #ملابس_العيد #ملابش_صفي_جديده @xxLARGE

X LARGE 🦅
X LARGE 🦅
Open In TikTok:
Region: EG
Tuesday 06 May 2025 19:46:54 GMT
276
25
6
47

Music

Download

Comments

shadeymasoud
🦅shadey Masoud🦅★★ :
❤❤❤
2025-06-05 16:55:40
1
user586467100
user586467100 :
❤️❤️❤️❤️
2025-05-06 22:18:56
1
karimmohammad580
karimmohammad58 :
🥰🥰🥰🥰
2025-05-06 20:27:11
1
To see more videos from user @m_uhammet4, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

“ኋላ እንዳይቆጭሽ
“ኋላ እንዳይቆጭሽ"☺️ ታላቁ የዘፈን ግጥም ደራሲ ይልማ ገብረአብ ስለ ኤፍሬም ታምሩ ሲናገር " የድምጹ ቅላጼ ልዩ በመሆኑ ግጥም ስደርስለት እጠነቀቃለሁ" ይላል።🙌 11 የሚደርሱ አልበሞችን ሰርቷል። የመጀመሪያ ሥራው ‹‹ ጋሜ›› የተሰኘዉ ሙዚቃ ነበር ገና ልጅ ነኝ ጋሜ ገና ልጅ ነኝ ጋሜ ለአቅማዳም አልደረስኩ አላውቅም ታምሜ" እያለ ይህን አስገራሚ የሙዚቃ ህይዎት "ሀ" ብሎ የጀመረው። የመጀመሪያ ስራዉን የደረሰዉ አያሌው መስፍን ነዉ። አያሌዉ ተስረቅራቂዉን ሙዚቀኛ ኤፍሬም ታምሩን በ1973 ዓ.ም. ሙሉ ሹራብ አስለብሶ አልበም እንካችሁ እንዲል አደረገዉ😁፡፡ • ያኔ ገና ልጅ ነኝ ጋሜ ብሎ እንደዘፈነ በፒያሳ ዋልያ ሙዚቃ ቤት ብቅ ባለ ቁጥር ሙሉቀን መለሠ እና ሌሎች በወቅቱ ዝና የነበራቸዉ ዘፋኞች "እዉነት ፍቅር አልያዘህም ወይ?" እያሉ ያበሽቁት ነበር አሉ።😂 ታዲያ ለዛሬ በቁ.23 የሚጣል ዘፈን የሌላቸው አልበሞች ዝርዝር ስር ይሄን ድንቅ አልበም አካተን በጥቂቱ ላወጋቹ ወደድኩኝ🥰🙏 በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው "ኋላ እንዳይቆጭሽ" በ1990 ዎቹ መገባደጃ ላይ ሙዚቀኛ አማኑኤል ይልማ ከአንዲት መልከ መልካም ቆንጆ ወጣት ጋር የበረታ ፍቅር ያዘው ፍቅሩን ለመግለጽ አላመነታም ነገራት መወደዷ የተነገራት ቆንጆ ግን ኩራት ይሁን ለማጥናት በማሰብ እሺም እንቢም ሳትል ዝምታ ሆነ መልሷ የአማን ፍቅር በረታ እንቅልፍ እንቢ አለው ሙሉ ጊዜውን ያስባታል በእርሷ ሰበብ በእንቅልፍ ማጣት በረዘመ አንድ ሌሊት ከአልጋው ላይ ወረደና ብእሩን አነሳ የሚከተለውንም ግጥም ጉዳቴን አልተረዳሽልኝም ይዘት አላብሶ ፃፈው ። ‹‹እንቅልፍ የማይወስደኝ ሌቱ የሚረዝምብኝ የእውነት ብወድሽ ነው ፍቅርሽ ቢጠናብኝ ቁርጤን የማትነግሪኝ መውደድ መጥላትሽን በስስት እንዳልሞት እባክሽ አደራሽን ›› እያለ በእነዚህ እና መሰል ቃላት አሽሞንሙኖ ከእነ ዜማው ደረሰው ። የ1970ዎቹን ሙዚቃ አብዝቶ ይወድ ነበርና ከ1970ዎቹ ጀምሮ ገናና ስም የነበረውን ኤፍሬም ታምሩ እንዲያዜምለት በልዩነት መረጠ ለወትሮውም ዜማ እና ግጥምን በጥንቃቄ በመምረጥ እና ለአድማጭ በመጠንቀቅ የሚሰራው አንጋፋው ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ ጊዜያዊ መኖሪያውን ካደረገበት ሀገረ አሜሪካ የሙዚቃ አልበም ለመስራት ወደሀገሩ የመጣበት ወቅት ስለነበር ይህን ማራኪ ግጥም እና ዜማ በመቀበል በታሪኩ ባለቤት አማኑኤል ይልማ እና በታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋዝ ክብረወርቅ አቀናባሪነት በግሩም ሁኔታ ተሰርቶ የአልበሙ መጠሪያ ለመሆንም በቃ ። ይህ በ1998 አ.ም መገባደጃ በኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ለአድማጭ የደረሰው የኤፍሬም ታምሩ “ኋላ እንዳይቆጭሽ” አልበም ላይ ከተካተቱ ሙዚቃዎች መሀል በታላቁ የግጥም ደራሲ ይልማ ገ/አብ በተደረሰው እና ዜማው በሞገስ ተካ በተሰራው ደሞ “ሰው መሰረቱ” የተሰኘ እና በማህበራዊ ኑሮ ደስታ እና መከራ መውረድ እና መውጣት ማግኘት እና ማጣት ላይ መሰረቱን ባደረገው ሙዚቃው ሁሌ በከፍታ ሁሌም በዝቅታ መኖር እንደሌለ ከሁሉም በላይ ሀያል በሆነው በጊዜ ውስጥ ሁሉም ተለዋዋጭ ስለመሆኑ እንደሚከተለው ያስታውሰናል ። ‹‹ ሰው መሰረቱ መቼ ይለያል በአንድ አምሳል ተፈጥሮ አንድ ሆኖ ይታያል ሀብትንም የታደላት ትልቅ ሰው ይባላል ያጣም ድህነቱን አምኖ ይቀበላል... ›› በሙዚቃው አጠቃላይ መልእክቱ የሰው ልጅ ደረጃ ምን ቢለያይ ሞት ግን ለሁሉም እኩል እና ፍትሀዊ መሆኑን አበክሮ ያነሳል ። “ኋላ እንዳይቆጭሽ” አልበም ከላይ ያነሳናቸውን ሙዚቃዎች ጭምሮ በፍቅር ውስጥ ቁንጅናን፣ መለየትን፣ ናፍቆትን፣ በደለን፣ ይቅርታን፣ አግራሞትን እና እድለኝነትን መሰረት ያደረጉ 12 ሙዚቃዎችን አካቶ የያዘ በእጅጉ ተደማጭ የሆነ እንዲሁም በሀገራችን ሙዚቃ ትልቅ ስም እና አሻራ ያላቸው ባለሙያዎች የተጣመሩበት በእጅጉ የተዋጣለት አልበም ነው🙌 ። ይልማ ገ/አብ፣ ሀብታሙ ቦጋለ፣ መሠለ ጌታሁን፣ አማኑኤል ይልማ በግጥም ቴዲ አፍሮ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ፣ሞገስ ተካ፣ እንዳለ አድምቄ፣ ፋንታሁን ወጨፎ በዜማ እንዲሁም ታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋዝ ክብረወርቅ፣አማኑኤል ይልማ፣ሳምሶን ጎሳዬ በቅንብር የተሳተፉበት ሲሆን አንጋፋው ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ ሳላስበው፣ሙሉ ጎጃም፣ ቂም አልይዝም ባንቺ በተሰኙ በ3 ስራዎች ላይ በሙዚቃ ማቀናበርም ተሳትፎበታል ። በዚህ አልበም ላይ የተሳተፉ ሁሉም ጥበበኞች ክብር ይገባቸዋል🙌 ዝነኛዉ ተዋዳጁ እና ኩሩው 😎ኤፍሬም ታምሩ ለ50 ዓመታት ጨው ሆኖ ሙዚቃን ሲያጣፍጣት የኖረ ዕንቁ ኢትዮጵያዊ ነው። እድሜን ከጤና ጋር እየተመኘሁ ለዛሬ አበቃሁ🙏🙌 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🙌🙏 @musictube 🇪🇹 #fyp #ኤፍሬምታምሩ #የ90ዎቹ #ኋላእንዳይቆጭሽ #musictube369 #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

About