@binigirmachew16: ለራስ የሚመልሱት ጥያቄ ወደ ትዳር የሚሄዱ ለራሳቸው የሚመልሱት ጥያቄ ✍ Bini Girmachew የወደፊት ባል የምትሆነው ወንድም 1)ሚስትህን በእውነት ትወዳታለህ?በሚገጥማት ችግር የራስህን ሕይወት አደጋ ላይ ጥለህም ቢሆን ለመርዳት ፈቃደኛ ነህ? 2)ምርጫዋንና መልካም ስብእናዋን ለማድነቅ ፍቃደኛ ነህ? 3) ከተወሰነ ዓመት በኋላ ቢያንስ ከ40ዓመት በኋላ ሚስትህ ይህን ዓለም ስለምትንቅ መንፋሳዊ ፍላጎቷን ተከብርላታለህ? 4)ስሜቷ ስስ ስለሆን ብሶቷን ስትነርግህ ያለ ነቀፋ ታዳምጣታለህ? 5) ፈጣሪ የሚያስተምርህን እውነት አስበህ ታስተምራታለህ? 6)ነገ ከፍተኛ ሹመት ላይ ብትደርስ በከፍተኛ ትምህርት ብትመረቅ የእኔ ብለህ ትቀበለዋለህ? 7)በልጆቿ እና በሠራተኞቿ ፊት ላትነቅፋት ቃል ትገባለህ? 8)ምንም ብስጭት ቢገጥምህ ዱላን ላለመሰንዘር ቃል ትገባለህ? 9)ትዳርህ አንድ መንፈሳዊ አማካሪ በጋራ የምታከብሩት አንድ አዋቂ ወዳጅ አንዲኖረው አስበኀል? 10)አካላዊ ንፅሕናን የአፍ ንፅሕናን ያለማቋረጥ መጠበቅ ተዘጋጅተሀል?ይህ ለራስህ ያለህን ክብር ማያሳያ ነው። 11)ሱስንና ደጅ ማምሸትን ለመተው ዛሬ ወስነሀል?ልጅህ ምን አይነት ሰው እንዲሆን ትፈልጋለህ?ጻፈውና አንተ በሙሉነት ኑረው።ያን ጊዜ ልጅህ አንተ ይሆናል። 12)ያለህን ሀብትና ደሞዝህን ለማሳወቅ ፍቃደኛ ነህ? 13)ልጅ ባትወልዱ ከአሥር ልጅ ሚስትህ እንደምትበልጥ ታምናለህ? 14)በልጆቻችሁ ላይ የጋራ አቋም እንዲኖራችሁ ትመካከራላችሁ? 15)ቤተሰቦቿ ባይወዱህም ለመውደድ ፍቃደኛ ነህ? 16)ወደ ትዳር ስትገቡ ከመንፈሳዊ አገልግሎቷና ወዳጆቿ ጋር ያላትን ኅብረት ታከብርላታለህ? 17)ሚስትህ እኩያህ እንጂ ተማሪህ አይደለችምና በእያንዳንዱ ነገር ልታርማት ትፈልጋለህ?አንዳንዱን ለማለፍ ዝግጁ ነህ? 18)የጋራ ጸሎታና ማዕድ እንዲኖራችሁ አስበህበታል? 19)ስጦታን መስጠት የሕይውትህ ሥርዓት ልተደርገው ትፈቅዳለህ? ፈጣሪ የሌለበት ኅብረት በድን ነውና እባክህ ፈጣሪህን ያዝ። የወደፊት ሚስት የምትሆኚ እህት 1)ባልሽን በልብሽ ታከብሪዋለሽ?የቤቱ ራስ እንደሆነ ትቀበያለሽ? 2)ለልጆችሽ ባልሽ ክቡር መሆኑን ለመንገር ፍቃደኛ ነሽ? 3)ውበትሽ ፀጥታና ዝግታ መሆኑን አውቀሽ ራስሽን በእውቀትና በማስተዋል እየገነባሽ ነው ወይ? 4)የቤቱ ኃላፊነት በይበልጥ ያንቺ መሆኑን ተረድተሽ የራስሽንና የቤትሽን ንጽሕና ለመጠበቅ ንቁ ነሽ? 5)የትኛውም ውጥረት ቢኖርብሽ ቤትሽ ቀድመሽ በመግባት ባልሽን መቀበል እንዳለብሽ ታውቂያለሽ? 6)ጣፋጭ ምግብ ሰርተሽ ለባልሽ ለማቅረብ ሙያ አለሽ ወይ? ምግቡን ሠራተኛ ቢሠራው ማቅረቡ ግን ያንቺ መሆን እንዳለበት ትገነዘቢያለች? አብዛኛው ወንድ ልጅ በሠራተኛው እጅ ምግብ ሲቀርብለት የራሱ ቤት አይመስለውም። 7)ከወደፊት ባልሽ ጋር ምንም የስጋ ዝምድና እንደሌላቸው አረጋግጠሻል?ከእህትሽ ወይም ከጓደኛሽ ጋር ጓደኝነት ያልጀመረ መሆኑን አረጋግጠሻል? 8)በትምህርትም በገንዘብም ራስሽን መቻል እንዳለብሽ ትገነዘቢያለሽ?ሁለታችሁ ከተስማማችሁ ችግር የለውም።ግን እንዳትቀሪ አስቢ። ደጁን ከረሳሽ ለባልሽም ማዘን አትችይም። 9)የባልሽ ቤተሰቦች አንዳንዴ ሊጠሉሽ ይችላሉ።አንድ ወንድን ብዙ ሰው ሲወደው ይህ ይከሰታልና በደስታና በማስተውል ተቀበይው። 10) የልጆችሽ ኃላፊነት ይበልጥ ባንቺ ላይ እንዳለ ተረድተሽ ልጆችሽን በፈሪሃ እግዚአብሔር ለማሳደግ ቁርጥ ውሳኔ አድርጊ። 11)ልጅ መውለድ ያንቺ ችሎታ ሳይሆን የፈጣሪ ስጦታ መሆኑን ተረድተሽ ቢከለክልሽ እንኳ ደስተኛ ነሽ ውይ?ምናልባትም በሽታ ልጅ እንደ ይሁዳም ጌታውን የሚሸጥ እንዲወለድ አስበሻል ወይ?እንኪ ብሎ ቢሰጥሽ እንጂ ያውልሽ ብሎ ሲሰጥሽ ከባድ ነው። 12)የባልሽን ቤተሰቦች እንደ ራስሽ ቤተሰቦች ይቅርታ ታደርጊላቸዋለሽ?ካለሽ ላይስ ታካፊያቸዋለሽ? 13)ባልሽ ከደጅ ሲገባ ምንም ቢከፋሽ በብሩህ ፊት ትቀበይዋለሽ ወይ?ያንቺ ብሩህ ፊት ከሌለ ቤቱን ይጠላል። 14)የባልሽን እንግዶች በደስታ ታስተናግጃለሽ? ወንድ ልጅ በቤቱ እንግዶችን መጋበዝ ይፈልጋል።አንቺ ደስተኛ ካልሆንሽ ግን ሆቴል ይጋብዛል። 15)ወደ ትዳር ብትገቢ ብትወልጂም አንደ ድሮ ራስሽን ለመጠበቅ ጎበዝ ሴት ነሽ? 16)እስከ ጋብቻ ድረስ ክብርሽን ጠብቀሽ ለመቆየት ወስነሻል።ቆራጥ ሴትን አንበሳም እንደማይደፍራት ተገንዝበሻል? 17)ዘመናዊነት ሴት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊት ሚስጥ ለመሆን ፈቃደኛ ነሽ? 18)በቅንዓት እየፈጠርሽ ባልሽን መጠራጠር ባልሽን ስርቆት ማስተማር መሆኑን ተገንዝበሻል? ቤትን የሚሠራ ፈጣሪ ነውና በጸሎት ትጊ! ፈጣሪ ያማረውን ቤት ይስራልሽ!!! # #binigirmachew #life #foryoupage

Bini Girmachew
Bini Girmachew
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 08 May 2025 06:55:13 GMT
135534
4748
113
1968

Music

Download

Comments

markdot0523
ضع علامة على النقطة :
አመሰግንሃለው ከልብ
2025-06-17 11:00:41
1
www.tiktokyadinal
Yetadegal :
Doctor Thank You !!!!!
2025-07-01 19:56:04
0
gech24yeteklye
የተክልዬ :
እናመሠግናለን
2025-07-31 19:17:29
0
eyuel415
Eyuel :
ከመልዕክቶችህ በጣም አትርፍያለሁ እግዚአብሔር ያክብርልኝ ።🙏
2025-06-30 10:10:22
15
nani__l
Nani :
ያነተ ሚስት የታደለች ናት በዚህ ልክ የተረዳ ሰው
2025-05-08 18:45:19
10
millatesfaye
Milla 👑 :
በነካ እጅህ የሴቶችም ፃፈው
2025-06-30 11:22:44
1
tameratselemon471
@Hazardinho :
እጆችህ ይባረኩ
2025-06-29 09:56:54
0
mekdeswolde7
mekdeswolde7 :
libam mist endhon erdagn 🙏🙏
2025-06-12 20:02:09
0
meryyo56
@Mery_Bo :
3??? mn malet nw? " b gubezenah werat fetarihn asb" almenn Ahun balenbet enji k hon ametat bhuala ayidelm emnenekew
2025-05-08 16:41:56
1
user8374705326606
beztufa :
እናመሠግናለን
2025-06-23 11:05:48
0
retaabebe11
Reta :
ፈጣሪ ሄዋኔን ይስጠኝ እንጂ በአምላክ ፍቃድ ይሆናል
2025-07-10 08:41:54
0
mercyyemariyam27
Mercy :
በጣም ጥሩ ትምርት ነው
2025-05-09 16:29:33
0
user67781836938078
user67781836938078 :
በጣም እጹብ ድንቅ የሆነ ትምህርት ነው ወንድማችን እግዚአብሔር ይባርክህ
2025-06-10 15:29:12
0
user9613694720223
Gebrsh :
በጣም ነው እሚገርመው እንደ ቅዱሳን መጻሕፍት እቀቡለዋለሁ ግን ወደ PDF መቀየር አልቻልኩም
2025-05-10 20:56:37
0
wubrst.ademe
Wubrst Ademe :
ስለ ትክክለኛ ምክርህ እናመሰግናለን
2025-06-29 17:20:45
0
elenialemayehuele
yididiya@jesuse :
ተባረክ 🙏🙏🙏
2025-05-08 09:30:14
1
natnaelsolomon875
Natnael Solomon :
በሁሉም በተባለው ፍቃደኛነኝ
2025-06-29 14:27:01
0
proudtobeethiopian
Mekdi@12 :
ሁሉም ከፈጣሪም አይደል ከእርሱ ለኔ ያለውን የፈቀደውን ያድርግልኝ🙏
2025-07-30 09:04:47
0
netsi1538
Netsi✝️ :
ባክህ ተወኝ ትርፉ ዋጋ መክፈል ነው እዛ ውስጥ ሆኜ ነው ምነግርህ 🥺
2025-05-09 09:10:25
8
asm5758
asm :
አሜን
2025-06-15 14:46:29
0
afibiabahiru
fiya46 :
Berta wondime,enem bizu eytemarku naw🙏
2025-07-01 08:36:19
0
user1052666686152
የዝገት :
Thanks a lot 🥰🥰🥰🥰
2025-06-27 03:59:30
0
teddy.tedoo
Teddy Tedoo :
የባሰ ትዳርን እንድፈራ አረከኝ
2025-06-22 14:05:50
0
To see more videos from user @binigirmachew16, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About