@melegnaa: ፔፕሮኒ ፒዛ @Melegna መለኛ የመከለሻ ቅመም@Melegna መለኛ የፒዛ ቂጣ @Melegna መለኛ አይብ ወጥ የአይብ ወጡን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጋችሁ የግብዓት እና የማጣፈጫ ቅመሞች አይነት እና መጠን የዛሬ የመጠን ለ3 ሰው የሚበቃ ሲሆን እናንተ በዛ አድርጋችሁ ማዘጋጀት ከፈለጋችሁ የግበዓት መጠኑን ከፍ ማድረግ ይጠበቅባቹሃል ፡፡ - 4 የሾርባ ማንኪያ አይብ - 3 ራስ መካከለኛ በጣም ደቆ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት - 3 የሾርባ ማንኪያ ዘይት - ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ብስል ቂቤ (ቁሌት ለማቁላላት ) - 1 የሾርባ ማንኪያ በርበሬ - ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ላም ተደርጎ የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት - ግማሽ ብርጭቆ ሙቅ ውሃ ቁሌቱን ላላ ለማድረግ - ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቂቤ - የምትፈልጉትን ያህል ጨው የቅመም አይነቶች ፡ - ግማሽ የቡና ማንኪያ የማቁላያ ቅመም - ግማሽ የቡና ማንኪያ የኮረሪማ ቅመም - ግማሽ የቡና ማንኪያ የሮዝሜሪ ዱቄት - 1 ቁንጥር የመከለሻ ቅመም ማስታወሻ፡ - አይብ ወጡ ለየት ያለ እና ግሩም ጠዓም እንዲኖረው ሽንኩርቱን ስታቁላሉት በዝቅተኛ ሙቀት ቢያንስ ለ 20 ደቂቃ ቀለሙ ወርቃማ እሲሆን በትግስት መጠበስ፡፡ መጥበስ ሲባል ታድያ መቃጠል የለበትም ትዕግስት ካደረጋችሁ እና በዝቅተኛሙቀት ከጠበሳችሁት ግሩም የሆነ ጠዓም ታገኛላችሁ፡፡ ማባያ - እንጀራ - ዳቦ - ቂጣ #fyp #habeshatiktok #ethiopian_tik_tok #oromotiktok #amharatiktok
Melegna መለኛ
Region: ET
Thursday 15 May 2025 06:48:36 GMT
Music
Download
Comments
ሜሮን🦅 :
አብይ ብለህ አይብ እንዳታስጠላን😂😂😂
2025-05-15 07:15:33
166
B€ŋŋ¥🕺 :
ቀጣይ የ አይብ ገንፎ ብትሰራ
2025-05-30 14:58:08
0
user93127598673271 :
ጠፍተሃል እኮ ግን በሰላም?
2025-05-30 16:57:13
0
markon :
የሰው ስህተት ከመልቀም የምግብ አሰራሩ ላይ ብታተኩሩ ይጠቅማችኋል እሺ
2025-05-15 07:43:04
49
Rahima Siybani :
ዛተር አሰራር አሳየን በጦሲኝ ነው ሚሰራው
2025-05-26 05:16:46
0
ገጠሬዋ ነኝ የከላላዋ የሙቬ ብቻ♥ :
በመለኛ እጅ የተዘጋጀ የወጥ ማጣፈጫ ቅመሞች የትነው የሚገኙት ከሀገር ውጭ 🥺
2025-05-16 21:11:50
0
ህይወት አጭር ናት :
ሽሮና በርበሬ ሀገር ውስጥ ላለነው አትሸጥም እኔ ባልትና ቤቶች አማረውኛል ውጭ ሀገር ላሉ ያልከው ውድ ናቸው እንዴ
2025-05-16 12:38:14
5
Nunu koo :
የምን ዓብይ ወጥ ነው ደሞ😲
2025-05-15 09:30:36
1
rita zegeye :
መጣጣ አይብ ስለሚባለው ታውቃለህ?
2025-05-15 09:16:17
1
rbka happy :
እመነኝ ከእኔ የበበለጠ እንደማትስራው አቅርቦት ነው ዋናው ...😭😭😭
2025-05-15 11:56:59
0
𝐛𝐮𝐫𝐚𝓑❤️𝓑 :
ይህን ምግም እንዴት ነው ያለአይብ የምርሰራው🥰🥀
2025-05-15 09:52:12
0
user2142402504057 :
እንደ ሀሳብ ቅመማ ቅመሞችን ብታዘጋጁና በአገር ውስጥ ገበያ ብታቀርቡ ማለት ኦርጋኒክ
2025-05-15 13:42:44
4
user234566778899 :
የሰራው ሰው ይንገረኝ ትንሽዬ አይብ ነበረችኝ በረዶ ቤት risk lwesedbat🤭
2025-05-15 19:46:36
2
BENYAM_1818 :
How do you make atekano ?pls ke video ga Aserarun asayun
2025-05-17 18:46:54
2
ymacollection :
የቂጣውን አሰራር ?
2025-05-15 07:03:14
1
Natu Afro :
የአብይ ወጥ?
2025-05-15 19:09:07
1
pearl :
ዉሀ ዉስጥ ጨው ጨምረው እንቁላል መቀቀል....ለምን???
2025-05-15 19:55:25
1
tade ቡና :
አይብ ከሌለን በምን እንጠቀም
2025-05-15 15:03:31
0
Orange :
መቁላላቱ ግዴታ ነው?
2025-05-16 20:00:33
0
Berry☪️🕋🕌 :
እንደው ዝም ብዬ ሳይ አንተን ቪዲዮዎች ሳስበው ሳስበው የባልአባት ሚስት ትመስለኛል
2025-05-15 10:37:52
0
ኢሳ :
ዉሀ ከሌለ በአርቂ ብናደርገውስ
2025-05-22 14:19:31
0
shalom :
መለኛ ምነው ዛሬ መልስ አበዙሳ
2025-05-24 14:53:15
0
AmbaGold :
ከየት አምጥተን እንስራው አይብ አንጅ ጆግ 600 ብር እንቂላል ዛሬ 19.50 ብር ገባ ያው 20 ብር በለው ፣ የተረገመች ሀገር ለዜጎቾ ሲኦል ሆነች
2025-05-16 17:42:25
0
semuti :
Ethiopia wst yalen esa?
2025-05-15 11:43:31
0
mihret_ge :
Le baltinaw delivery benante nw?
2025-05-20 05:56:46
0
To see more videos from user @melegnaa, please go to the Tikwm
homepage.