@goodstoriesb613975: «ዝምታ ወርቅ አይደለም» (ከዳንኤል ክብረት) ሰውዬው ከሚስቱ ሌላ አንዲት ሴት ወደደና እፍ ክንፍ አለ፡፡ ፡ ልጁን እና ሚስቱን እየተወ ከዚህችኛይቱ ጋር ማምሸት፣ ብሎም ማደር ጀመረ፡፡ ፡ በመጨረሻም አንድ ቀን ወደ ሚስቱ መጣና ድንገተኛ የሆነ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ፡ «እኔ እና አንቺ እንድንፋታ እፈልጋለሁ፤ ለምን ብለሽ ምክንያቱን አትጠይቂኝ፡፡ መፋታት ብቻ እፈልጋለሁ፡፡ ደግሞም ሌላ ቀን አይደለም፣ ነገ እንዲሆን እፈልጋለሁ» አላት፡፡ ፡ ሚስቱ በሁለት ነገሮች ተጨነቀች፡፡ ፡ በአንድ በኩል ምንም ነገር አትጠይቂኝ ብሏታል፡፡ ፡ በሁለተኛ ነገር ልጇ ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና ልትቀመጥ ጥቂት ቀናት ቀርቷታል፡፡ ፡ «ባልፈልገውም፣ ባልስማማበትም፤ ካልክ የግድ እቀበለዋለሁ፡፡ ነገር ግን በኛ ምክንያት ልጃችን መጎዳት የለባትምና የአንድ ወር ጊዜ ያህል እንታገሥ፡፡» አለችው፡፡ ፡ እርሱም አሰበና «ጥሩ አንድ ወር መታገሥ አያቅተኝም፤ ነገር ግን በዚህ አንድ ወር ውስጥ ሽማግሌ መላክ፣ ምክንያቱን መጠየቅ የለም፤ ስለ ፍቺው ማናችንም ምንም ነገር ማንሣት የለብንም፤ በዚህ ቃል ግቢ» አላት፡፡ ፡ እርሷም «እስማማለሁ፤ ግን አንተም የምነግርህን ለመፈጸም ከተስማማህ ነው፤ ፡ ታድያ በዚህ አንድ ወር ጠዋት ጠዋት ከዕንቅልፌ ስነሣ፣ ማታ ማታም ወደ አልጋዬ ስሄድ ያኔ የሠርጋችን ዕለት አቅፈህ እንደ ወሰድከኝ አድርገህ አቅፈህ ትወስደኛለህ» ስትል ጠየቀችው፡፡ ፡ ነገሩ ያልጠበቀው እና ያልተለመደ ዓይነት ቢሆንበትም፣ ቀላል እና ሊያደርገው የሚችል ስለሆነ እሽ ብሎ ቃል ገባላት፡፡ ፡ አንዱ ወር ተጀመረ፡፡ ፡ ጠዋት ጠዋት ከዕንቅልፏ ስትነሣ አቅፎ፣ ከፍ አድርጎ፣ ወደ በረንዳ ካደረሳት በኋላ ወደ ሥራው ይሄዳል፡፡ ፡ ማታ ማታም እንዲሁ አቅፎ ወደ አልጋዋ ይወስዳታል፡፡ ፡ ስለ ፍችው አይነጋገሩም፡፡ ፡ እየዋለ እያደረ ሲሄድ የሰውነቷ ጠረን፣ የምትለብሳቸው ልብሶቿ፣ የዓይኖቿ እና የፀጉሯ ሁኔታ፣ የገላዋ ልስላሴ እና የአካሏ ቅርጽ እየሳቡት መጡ፡፡ ፡ በየቀኑ እያቀፈ ሲያወጣት እና ሲያስገባት ሰውነቷ እየቀለለው፤ ለርሱም እርሷን አቅፎ መሸከሙ አንዳች እንግዳ የሆነ የደስታ ስሜት እየፈጠረለት መጣ፡፡ ፡ ከራሱም ጋር ሙግት ጀመረ፡፡ «ለምንድን ነው እንፋታ ያልኳት፤ አሁን የሚሰማኝን ስሜት ያህል ስሜት ከአዲሷ ወዳጄ ጋር ለምን አይሰማኝም? ለምንስ ነበር ይህንን ነገር እንዳደርገው ቃል ያስገባችኝ ? ይህን የመሰለውን ገላዋን፣ እንዲህ የሚማርከውን ጠረንዋን፣ እንዲህ የሚያስደስተውን ፈገግታዋን፣ እንዲህ የተዘናፈለውን ፀጉሯን፣ እንዲህ ልዩ የሆነውን አካሏን እንዴት እስከ ዛሬ አላስተዋልኩትም ?እርሷ ናት ከኔ ጋር የነበረችው ወይስ እኔም ከርሷ ጋር ነበርኩ?» ፡ የወሩ መጨረሻ እየደረሰ መሆኑን ሲያውቅ ከእርሷ መለየቱ ጨነቀው፡፡ ፡ እንዲያውም ይህ ሁኔታ የፈጠረበትን እንግዳ ስሜት እየወደደው መጣ፡፡ ፡ ነግቶ እና መሽቶ እርሷን አቅፏት እስከሚወስዳት በጉጉት መጠበቅ ጀመረ፡፡ ፡ በሌላም በኩል ደግሞ በዚህ ድርጊቷ በውስጡ ያሳደረችበትን ስሜት እያሰበ ያደንቃትም ጀመር፡፡ ፡ ብልህነቷን፣ አስተዋይነቷን እና በቀላል ድርጊት ቀልቡን ልትገዛው መቻሏን ሲያስበው «ምን ዓይነት አስገራሚ ሴት ናት?» ይላል፡፡ ፡ ወሩ ሊያልቅ ሁለት ቀን ሲቀረው የመፋታቱን ሃሳብ በውስጡ መረመረው፡፡ ነገር ግን አላገኘውም፡፡ ፡ በዚህ ሁኔታ መፋታቱ ደግሞ ለሕይወቱ የማይፈታ ዕንቆቅልሽ እንደሚሆንበት እያሰበ ተጨነቀ፡፡ ፡ ይቀጥላል... #ከብዕር #ደራሲ #booktoker #danielkibret

Good Stories
Good Stories
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 18 June 2025 04:08:22 GMT
78553
1299
62
259

Music

Download

Comments

alexandrociero
alexandrociero :
የቀጣፊ ሰው ፅሁፍ እላነብም!!
2025-06-19 18:05:40
11
ashutdf2
ashu :
ታሪኩ ኣስተማሪነው
2025-07-18 11:43:45
1
user79982815381604
user79982815381604 :
የተረት አባት።
2025-07-04 06:27:38
4
solomon.astatkie
Solomon Astatkie :
እራስህ አንብብ😏
2025-07-30 06:15:57
0
dad8429
Dad :
እዉነትም የተረት አማካሪ!ዳንኤልና አብይ ምንም ብትነግሩን በራበና በጠወለገ ሰዉነት እና ሆድ ስለሆነ አናምናችሁም!
2025-06-19 08:08:11
3
sisay.werke
Sisay Werke :
ባንተ ዝምታ ወርቅ አይደለም በእኔ ዝምታ ወርቅነው
2025-07-18 16:16:49
1
ebnat039
Ebnat :
ሰውየው ችሎታ የሌለው ነው ለማለት የቻለ አስተያየት አላየሁም፣
2025-06-20 11:08:49
2
hailye_31
HB 🔌🔋 :
ዘንዘሪጡ
2025-07-01 09:03:11
2
tilahun.geme
Tilahun Geme :
groom!!!!
2025-07-04 17:47:33
2
meketruth
meketruth :
በጣም ድንቅ ታሪክ ነው❤❤❤
2025-07-08 07:10:29
1
keda886
keda بابا>.<:-P :
bezi geza belah mehon new ❤
2025-07-11 09:04:51
1
ahmedmuhaba156
ahmedmuhaba156 :
ጨነቀኝ ብዛቱ
2025-06-30 12:32:30
1
user5888853594657
user5888853594657 :
እና ብልግናን ለመፋታት አታስቡት እያልከን ነው?😂😂
2025-07-05 06:43:07
1
user3980069462705
jafar :
በጅ ያለወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል፡፡
2025-06-19 18:52:31
2
ethio121addis
ethio121addis :
ዳንኤል ክስረት
2025-07-29 03:55:22
0
noahh.noahh4
Noahh Noahh :
መሃይም ነው ቁጭብሎ አልተማረም አንድተራ አንባቢ እንጂ ደረጃያለውሊቅ አይደለም
2025-07-27 18:29:35
0
hadushagibreselase
atnasiya 21 :
መድሀይናለም ዕድሜውን ያሳጥረው።ሸሌ
2025-07-22 00:30:41
0
user5561028762129
dan :
የህሰዉኮ የሰዉ መልክነዉ ያለዉጂ አዉሬ እኮነዉ
2025-07-16 18:13:09
0
kasyeagegnehu
Kasye :
እስስት
2025-07-16 17:47:00
0
abrishdream
Abrish black :
copy past yilal😂😂😂
2025-07-16 13:13:39
0
user96278595971828
ሰው እንደ ሳሙና ! :
ለምሳሌ በዚህ ዘመን ከዝምታ ውጭ አማራጭ የለም ብትናገርም መጮኽ ብቻ ነው ሁሉም ተናጋሪ አውቃለሁ ባይ ስለሆነ መናገርህ ትርጉም የለውም ስለዚህ ዝም ብለህ እየሰራህ ታዳምጣለህ እንጂ
2025-06-30 10:44:32
0
esubalew024
ጅሩየው :
ዋው ገራሚ ታሪክ
2025-07-14 18:00:07
0
gedionf
Geddy :
የነፈሰበት
2025-07-02 18:26:55
0
mekuanent2
mekuanent agid :
ይሄን ፁፍ ካነበብኩት ቆየው አሁን የርሱን ታሪክ ከሰማሁ በሁአላ የራሱ ታሪክ ሳይሆን አይቀርም ብዬ እንድጠረጥር አድርጎኛል
2025-06-19 13:14:48
0
satenaw492
እውቀት በየፈርጁ :
ይህ ድሮ ነው የምናውቀው...አትደሰኩርብኝ
2025-07-04 20:01:04
0
To see more videos from user @goodstoriesb613975, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About