@orthodox_tewahedo_church: ፍቅር ቊስል ነው እውነቱ ይህ ነው ፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው። እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል። እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል። ምክንያቱም ፍቅር የሚታየው በታገስነው ቊስል ውስጥ ነው ፍቅር የሚታወቀው የተለዋወጥናቸውን ቃላት ሳይሆን በምንታገሠው ቊስል ፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም ፣ በከፈልነውን መሥዋዕትነትና በተካፈልነውን ብርሃን ነው። ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤው ድል ማብሠሪያ መለከት አይደለም ፣ የፍቅሩ ማስረጃ ቊስሉ ነበር። "ወደ እኔ ኑ ቊስሌን ዳስሱ ፣ እጃችሁንም ስለ እናንተ ፍቀር በቆሰልሁት ቊስል አስገቡ" ነበር ያላቸው። አታስታውሱኝም? አላወቃችሁኝም? እስከ ሞት ድረስ የወደድኳችሁ እኔ ነኝ። ለፍቅሬ ማረስጃ እንዲሆናችሁ ደግሞ ቊስሌን ተመልከቱ! ነው ያላቸው። ፍቅር ቊስል ነው። በእግዚአብሔር መንግሥት ክብርና ምስጋና የምናገኘውም በምድር ሳለን በነበሩ ስኬቶቻችንና ባስገኘናቸው ውጤቶቻችን ሳይሆን በታገሥናቸው መከራዎችና በተሰቃየንባቸው ሕመሞች ልክ ነው። ለዚህም ነው በአበው መጽሐፍ አንድ ቅዱስ አባት ለረጅም ዓመት በሰውነትዋ ላይ ቆስሎ የምትሰቃይን ሴት ሊጠይቁ ሲሔዱ "እዩት ቊስሌን አጎንብሰው ቢያዩት አጥንቴ ይታይዎታል" አለቻቸው። እርሳቸውም ጎንበስ ብለው "ብዙ ዓመት በታገስሽው በቊስልሽ ውስጥ የሚታየኝ አጥንት ሳይሆን ገነት ነው" አሏት። ጸሐፊ: Fr Haralambos Libyos Papadopoulos ተርጓሚ: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ #ጌታዬ_ብርታቴ❤🙏 #ኦርቶዶክስ⛪ተዋህዶ⛪ለዘለዓለም🙏ትኑር #ኦርቶዶክስ⛪ተዋህዶ⛪ለዘለዓለም🙏ትኑር
የጃንደረባው ትውልድ☦፲፮
Region: SA
Sunday 29 June 2025 14:33:05 GMT
Music
Download
Comments
Abrsh yaya :
የኔዋ ሂዋኔ ወደኔ ስትመጪ እንዲ ያለ ፍቅር ሰንቀሽ ነይ
እኔም ይሄን እንድሰጥሽ
ቃለ ህይዎትን ያሰማልን 🥺🥺
2025-07-06 22:09:36
6
Soliyana Abrha :
እዉነት ነዉ ክበርና መሥጋና ለአንተ ይሁን ዝቅ ብለህ ፈቅርን ያስተማርከን የቀራኒዮ ጌታ ዛሬም ተመሥገን🥰🥰🥰
መምህራችን ድንቅ ትምህርት ቃለህይወት ያሰማልን🥰🥰🥰
2025-08-01 16:48:54
0
ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ ፀንታ ለዘለአለም#ትኑር :
እረ መምሕር የዚሕን ክላሲካል መዝሙር ስሙን።ንገሩኝ ።ላዳምጠው እፈልጋለሁ
2025-07-03 14:06:12
1
Biruk Demessie :
እንዴት የሚያሳርፍ ቃል ነው በዘመናት መለዋወጥ ውስጥ የማይለወጥ እርሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ክብርና ምስጋና አምልኮትና ውዳሴ ከምድር እስከ አርያም ለስሙ ይሁን አሜን። ለመምህራችንም ቃለ-ህይወት ያሰማልን ረጅም እድሜንም ከጤና ጋር ያድልልን አሜን!!
2025-07-03 07:57:26
0
ቅድስት ሰሜንአዊት :
በጣም❤❤❤
2025-07-30 20:35:23
0
ሳምሪ የድንግል ማርያም ልጅ :
ቃል ህይውት ቃል በረከት ያስማልን በእውነት ትልቅ ትምህርት ነው
2025-06-29 19:38:23
17
abity :
እውነት ንው ለሁላችንም ትግስትን ይስጠን
2025-06-30 04:22:11
10
kalkidan@michael :
የፍቅር ባለቤት ክብር ምስጋና ይግባው
2025-07-01 10:19:08
6
tigist818 :
ቃለህይወት ያሰማልን
2025-06-30 17:43:57
0
mulu :
እዉነት ነዉ ክበርና መሥጋና ለአንተ ይሁን ዝቅ ብለህ ፈቅርን ያስተማርከን የቀራኒዮ ጌታ ዛሬም ተመሥገን🥰🥰🥰
2025-06-30 20:13:19
1
Dereje :
ቃለ ሕይወት ያሰማልን
2025-07-06 17:03:40
1
1221 :
ቃለ ህይወት ያሠማልን ትልቅ ሠው
2025-07-04 15:59:16
0
Melku 21 ✝️ ✝️ ✝️❣️ :
ቃለ ህይወትን ያሰማልን መምህር🙏
2025-06-30 17:55:46
0
Girmshe :
እውነት ነው የነፍስ ምግብ በላሁ
2025-06-30 18:06:51
0
ለምለሚቱ እንፍራዝ💘😘😍😍 :
የኔ ጌታ ልቦናችን አብራው አስተዋይም አድርገን የህይወት ቃል ያሰማልን😢😢🙏🙏🙏
2025-07-01 09:56:00
2
@ጌዜ_ለኩሉ🙏 :
አሜን(3)ቃለሂወት ያሰማልን 🙏🙏🙏
2025-07-01 19:31:25
0
Yenework Belay :
ልክ
2025-06-30 12:27:45
0
tina🇪🇹🇮🇱✌ :
ፍቅር ቁስል ነዉ😔✝✝😔
ግን የክርስቶስ ፍቅረ ብቻ🥺🥺🥺🥺🥺
2025-06-30 22:19:11
0
engidashet :
kale hiwot yasemalin
2025-06-30 16:44:43
0
rose :
amen kale heywet yasmaln
2025-07-30 05:13:34
0
Miker የድግል ማርያም ልጅ 21"19"11 :
ቃለህይወት ያሰማልን 🙏🙏🙏
2025-07-18 16:57:37
0
Hagi :
ቃለ ህይወት ያሰማልን
2025-07-01 01:42:22
0
dagi :
ere ketay
2025-06-30 17:09:12
0
To see more videos from user @orthodox_tewahedo_church, please go to the Tikwm
homepage.