@eleni_29: ዶግማ እና ቀኖና ማለት ምን ማለት ነው? ትምህርት ሃይማኖት (የሃይማኖት ትምህርት) በሦስት ይከፈላል፡፡ ይኸውም፦ 1ኛ፡- ዶግማ 2ኛ፡- ቀኖና 3ኛ፦ትውፊት በሚል ነው። ዶግማ ፡- ቃሉ የግሪክ ሲሆን ፍችውም እምነት ማለት ነው፡፡ ቀኖና፡- ደግሞ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ሥርዓት ማለት ነው፡፡ ትውፊት ፦ አወፈየ ከሚለው የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ውርስ ቅብብል ማለት ነው። ዶግማ ወይም እምነት አይጨመርበትም፤ አይቀነስበትም፤ አይሻሻልም፤ ችግርና ፈተናም ቢመጣ እስከ ሞት ድረስ አጥብቀን የምንይዘው ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፦ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ፤ ቢመረምር እንጂ የማይመረመር ሁሉን ቻይ አምላክ፤ የሚሳነው ነገር የሌለ ፈጣሪ፤ የሰማይና የምድር ባለቤት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር (ፈጣሪ) የአካል ሦስትነት አለው፡፡ በመለኮት፣ በመፍጠር፣ በሥልጣን፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ ግን አንድ ነው፡፡ በሦስትነቱ አብ፤ ወልድ፤ መንፈስ ቅዱስ ሲባል በአንድነቱ አንድ መለኮት አንድ እግዚአብሔር ይባላል፡፡ በአዳም ምክንያት ከመጣው የዘለዓለም ሞትና ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ የወጣነው ከሦስቱ አካላት በአንደኛው አካል ማለትም በወልድ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህ ዶግማ ወይም እምነት ይባላል፡፡ ቀኖና ግን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ያደጉ ክርስቲያኖች የሚመሩበት ሥርዓት ስለሆነ፤ በሃይማኖት አባቶች ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት እንደጊዜው ሁኔታ የሚሻሻል_በመሆኑ_የሚጨመርበት_የሚቀነስለት_ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፦ እኛ ኦርቶዶክሳውያን የምንጠመቀው ሴት በሰማንያ ወንድ በአርባ ቀናችን ነው፡፡ የተወለዱ ሕጻናት ሴቷ ሰማንያ ወንዱም አርባ ቀን ሳይሞላቸው ቢታመሙና በሽታው አስጊ ከሆነ በ10፣ በ20፣ በ30…ቀናቸው መጠመቅ ይችላሉ ቀኖና ነውና፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን የቀዳስያን ብዛት መነሻው አምስት ነው፡፡ ምናልባት ከአምስቱ አንዱ፤ ሁለቱ፤ ሦስቱ ቢታጡና ሌላም ተፈልጎ እስከ መጨረሻ የማይገኝ ከሆነ ከአቅም በላይም የሆነ ችግር ከገጠመ ሁለቱ ወይም አንዱ ብቻ ቀድሰው ማቁረብ ይችላሉ፡፡ ቀኖና ነውና፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ታቦት ሲከብር ቤተ ክርስቲያኑን የሚዞረው ሦስት ጊዜ ነው ችግር ካለ አንድ ጊዜ ብቻ ዑደት ተፈጽሞ ሊገባ ይችላል። ቀኖና ነውና። ስለቀኖና (ስለሥርዐት) ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ ሲል ጽፏል። 1. ‹‹ነገር ግን ሁሉን በአግባብና በሥርዐት አድርጉ፡፡›› 1ኛ ቆሮ. 14፥40፡፡ 2. ‹‹ወንድሞች ሆይ በሠራንላቸው ሥርዐት ሳይሆን በተንኮል ከሚሄዱት ወንድሞች ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛችኋለን፡፡ እኛን ልትመስሉ እንደሚገባችሁ እኛም በእናንተ መካከል ያለ ሥራ እንዳልኖርን ራሳችሁ ታውቃላችሁ›› 2ኛተሰ. 3፥6-7›› ቀኖና (ሥርዐት) የሚወሰነው በሃይማኖት አባቶች እንደሆነና ወንጌልን የሚያስተምር ሰው ለሚያስተምራቸው ክርስቲያኖች በሃይማኖት አባቶች የተወሰነ ቀኖና ማስተማርና መሰጠት እንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ያስረዳል፡፡ በየከተማውም ሲሄዱ፥ ሐዋርያትና ቀሳውስት በኢየሩሳሌም ያዘዙትን /የወሰኑትን/ ሥርዐት አስተማሯቸው፡፡ አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ጸኑ ዕለት ዕለትም ቁጥራቸው ይበዛ ነበር፡፡›› ይላል የሐዋ. 16፥4-5፡፡ በዚህ የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ደርቤንና ልስጥራን በተባሉ ቦታዎች ለነበሩ ክርስቲያኖች ወንጌልን ከሰበከ በኋላ ሐዋርያት የወሰኑትን ቀኖና (ሥርዐት) እነደሰጣቸው እንረዳለን፡፡ ስለዚህ ቀኖና ወይም ሥርዐት ቤተክርስቲያንን ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡ በመሆኑም ዶግማንና ቀኖናን ወይም እምነትንና ሥርዓትን ጎን ለጎን ይዞ መጓዝ ሐዋርያትን መከተል ነው፡፡ ምንጭ:- ትምህርተ_ተዋህዶ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር

ፍቅርተ ክርስቶስ†🕊♡
ፍቅርተ ክርስቶስ†🕊♡
Open In TikTok:
Region: SA
Sunday 20 July 2025 05:43:25 GMT
228011
11183
207
1889

Music

Download

Comments

shakiso234
Melese :
ተረት ተረት ተውና ኢየሱስን ተቀበሉ
2025-07-21 08:44:57
5
aka..aka379
አኬ 🦅🇺🇬 :
ዶግማ ማለት የማይሻር የማይቀየር ለምሳሌ ምስጤረ ቁርባን ምስጤረ ጥምቀት ምናምን ቀኖኖ ማለት ደሞ አንድ ሰው ቤተክርስቲያን ስራት ምእመናን የሚታረሙበት ከሀጥያት ወደ ጥሩ ስራ የሚመለሱበት ለምሳሌ ንስሐ ቀኖኖ ይባላል ከተሳሳትኩ አርሙኝ 🙏
2025-07-20 16:56:25
40
user2746304966858
ራሔል ጎንደሬዋ :
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ቃለ በረከትን ያሰማልን ፀጋውን ይብዛላችሁ🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2025-10-12 11:11:02
0
abawasihun
Stub :
ማንኛውም ክርስቲያን ማወቅ ያለበት ዶግማ ቀኖናን ሳይሆን አዳኝ ክርስቶስ ብቻ እና ብቻን ነው እንድንበት ዘንድ ከስማይ በታች የተስጠን ስም ክርስቶስ !!!
2025-07-20 19:47:45
3
user7275708382832
Konjit :
ጅማርያችንን ሳይሆን ፍፃምያችንን የሳምርልን አሜን
2025-10-14 05:17:22
0
tsigu1621
Tsigu yenatua :
#ዶግማ ማለት አንዴ የተሰጠ የማይቀየር የማይለወጥ ማለት ነው ምሳሌ ሐይማኖት#ቀኖና ማለት ደሞ የሚፈፀም የሚደረግ ማለት ነው ለምሳሌ ንስሀ #ትውፊት ማለት ደሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ማለት ነው ከመልሱ ልማር
2025-07-20 11:27:18
27
user4049346019916
ባላገሩ :
አንድ ካህን ብቻ ቀድሶ ማቁረብ ይቻለዋልን?
2025-07-21 04:54:39
1
alemkjnxt2a
mimi :
yezamaw sim( name) mindin new yemibalew? sisemaw betam des yilegnal baygebahnim
2025-08-30 13:13:17
0
tadele.mechale.19
Tadele Mechale 19 :
አስተማሪ ነዉ ቃለ ሄወት ያሰማልን 🥰🥰🥰
2025-08-13 14:59:13
0
abyssinia153
abyssinia15 :
ምዕ/ጎንደር ዞን የገንዳ ዉሃ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን🥰🥰🥰🥰
2025-07-20 23:06:21
1
mekilit.dan
Mekilit dan :
Kale hiwot yasemaln
2025-10-06 08:21:38
0
worku.yenew
Worku Yenew :
እምነትና ስርዓት
2025-07-22 15:07:56
1
dagim.tesfaye79
Dagim Tesfaye :
ቃል ህይወት ያሰማልን ያገልግሎት ዘመንህን/ሺን ይባርክልን ከደሴ ደብረ ቁስቋም እና እየሱስ ቤተክርስቲያን ምእመን
2025-08-11 11:15:11
0
amen6985
አተ ጠብቀኝ :
አቤት ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሆን ፈጣሪን መመረጥ እኮ ነዉ ድባቡ ሰላሙ ፍቅሩ እዉነትና እዉነት የሚመለከበት
2025-07-20 18:21:30
8
s.a.n.c.h.o.8472
SPORT 😍⚽️⚽️🥅🏆 :
እስከዛሬ ካገኘሁት ጠቃሚ መረጃ 🥇🥇አንደኛው ነው።አመሰግናለሁ
2025-07-21 10:17:10
4
fantu.d
Fantu D :
ትልቅ ትምህርት ነው በዙ ጊዜ እነዚህን ሦሰት ቃሎች እሰማ ነበር ትርጉማቸውን ግን አላውቅም ነበር አሁን ግን በደንብ ተረድቻለሁ በጣም አመሠግናለሁ ።
2025-09-14 15:33:54
0
kinfe.gebremedhin1
Kinfe Gebremedhin :
በኦርቶዶክስ የሚቀድሱ ምንም ቢፈጠር ከኣምስት ኣይወንሱም ኣይጨምሩም
2025-08-03 13:32:42
0
estif_ethiopian
Estif Best :
ቃለህይወት ያሰማልን እጅግ ጠቃሚ መረጃ ነው እናመሰግናለን!!!
2025-08-13 10:50:37
1
sebsbeseyfu
የሚኪ ሊጅ :
ቃለህወት የሠማልን በፀጋና በበረከት ያኑርህ🥰🥰🥰🥰🥰
2025-08-09 04:44:41
1
gre1627
freedom :
thank you
2025-07-20 09:55:40
1
yinberberumissay
[email protected] :
ቃለ ህይወት ያሰማልን መ/ር ዘየደ በዚህ ላይ ጠለቅ ያለ ትንታኔ ቢሰጡበት?
2025-07-20 18:36:33
0
merhawi.musie
merhawi musie :
እግዚአብሔር ይስጥልን እንድናዉቅ ስላደረከን 🙏🙏🙏
2025-10-05 17:12:53
0
ethio_tour_and_travels
Ethio💚Tour💛and❤Travels🇪🇹 :
ትውፊት በምሳሌ?
2025-08-17 07:32:19
0
tsfamichael.yirga
Tsfamichael Yirga :
ዶግማ ማለት የማይሻሻል ሲሆን ቀኖና ማለት የሚሻሻል ነው።
2025-07-21 14:49:28
2
fritayye
fritayye :
ተክሊል ዶግማ ነው ቀኖና?
2025-08-08 16:25:51
0
To see more videos from user @eleni_29, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About