@melakulegalcosultant: ለህዝብ ጥቅም መሬት ለማስለቀቅ ስለሚፈፀም ሥነ-ሥርዓት! *************** ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሣ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 1161/2011 ከአንቀጽ 5-10 ድረስ እንደተመለከተው፣ 1. የሚለቀቀው መሬት ለሕዝብ ጥቅም መሆኑን ስለመወሰን አግባብ ያለው የፌዴራል አካል ወይም የክልል፣ አዲስ አበባ ወይም ድሬደዋ ካቢኔ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሻለ ልማት ያመጣል ብሎ በመሬት አጠቃቀም እቅድ ወይም በልማት እቅድ ወይም በመሠረተ ልማት መሪ ፕላን መሠረት የሚለቀቀውን መሬት ለሕዝብ ጥቅም መሆኑን ይወስናል፡፡ በዚህ መሠረት ለመወሰን መሪ ፕላኑ ዝርዝር የማስፈፀሚያ ፕላን ሊኖረው ይገባል፡፡ ለሕዝብ ጥቅም መሬት አንዲለቀቅ ሲወስን ለካሣ እና መልሶ ማቋቋም የሚያስፈልግ በጀትና በጀቱ በማን እንደሚሸፈን አብሮ መወሰን አለበት። የመሬት ባለይዞታዎች በዚህ በላይ የተገለፀው መስፈርት ሳይሟላ መሬታቸው ለሕዝብ ጥቅም እንዲለቀቅ የሚሰጥ የሕዝብ ጥቅም ውሳኔ ላይ አቤቱታ ሊያቀርቡ ይችላል፡፡ እንደአስፈሊጊነቱ የክልል፣ የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ ካቢኔ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል መሬት ማስለቀቅ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣኑን ለከተማ ወይም ለወረዳ አስተዳደሩ በውክልና ሊሰጥ ይችላል፡፡ 2. መሬት የማስለቀቅ ሥልጣን ለሕዝብ ጥቅም አንዲለቀቅ ውሳኔ የተሰጠበትን መሬት የከተማው ወይም የወረዳው አስተዳደር መሬቱ የማስለቀቅ እና የመረከብ ሥልጣን አለው፡፡ 3. ለባለይዞታዎች ቅድሚያ የማልማት መብት ስለመስጠት በከተማ ለመልሶ ማልማት በተከለለ ቦታ ውስጥ ያለ ባለይዞታ በፕላኑ መሠረት ይዞታውን በግልም ሆነ በጋራ ቅድሚያ የማልማት መብት አለው፡፡ የገጠር መሬት ባለይዞታ ለእርሻ ስራ የሚለቀቅ ሲሆን አቅሙ ካለው ይዞታውን በግልም ይሁን በቡድን በመሬት አጠቃቀም ፕላኑ መሠረት ቅድሚያ የማልማት መብት አለው፡፡ በዚህ መሰረት ለተነሺው ቅድሚያ የማልማት መብት የሚጠበቅለት በፕላኑ መሠረት ለማልማት አቅም ማሳያ ማቅረብ ሲችል ነው። ቅድሚያ የማልማት መብት የሚሰጥበት ዝርዝር ሁኔታ እና አቅም ማሳያ መጠንና የጊዜ ገደብ በደንብ ይወሰናል፡፡ 4. መሬት የሚለቀቅበት ሥርዓት የከተማ አስተዳደር ወይም የወረዳ አስተዳደር መሬት ሲያስለቅቅ መከተል ያለበት ቅደም ተከተል፡- ሀ/ ተነሺዎች ከመነሳታቸው ቢያንስ ከአንድ ዓመት በፊት ስለልማቱ ዓይነት፣ ጠቀሜታና አጠቃላይ ሂደት በማወያየት እንዲያውቁት ማድረግ አለበት፡፡ ለ/ በዚህ አንቀፅ ፊደል ተራ (ሀ) የተጠቀሰው ቢኖርም የሚመለከተው የፌዴራል ወይም የክልል መንግስት ሀገራዊ ወይም ክሌላዊ ፋይዳ ላለው ለአስቸኳይ ልማት መሬት እንዲለቀቅ ከወሰነ ተነሺዎች ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ስለልማቱ አይነት፣ ጠቀሜታና አጠቃላይ ሂደት በማወያየት እንዲያውቁት ሊደረግ ይችላል፡፡ ሐ/ እንዲለቀቅ በተወሰነው ቦታ ላይ ከሚገኙ ተነሺዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች የባለመብትነት ማስረጃ እና ካሣ የሚከፈልባቸውን ንብረቶች የልኬትና የመጠን መረጃ መሰብሰብ አለበት። ተነሺዎች ስለልማቱ እንዲያውቁት ከተደረገ በኋላ የተጨመሩ ማናቸውም ንብረቶች ካሳ አይከፈልባቸውም፡፡ መ/በዚህ ንዑስ አንቀጽ ፊደል ተራ “ሐ” መሠረት የተሰበሰበውን መረጃ አጣርቶ ለልማት ተነሺ የሚሰጥ መብት ተጠቃሚነት ይወስናል፣ የካሣ መጠኑንም አስልቶ ካሣና ሌሎች ተያያዥ መብቶችን ክፍያ ይከፈላል፡፡ ሠ/ ለሕዝብ ጥቅም እንዲለቀቅ በተወሰነው ቦታ ላይ ለሚገኝ ተነሺ ወይም ሕጋዊ ወኪል የሚገባውን የካሣ መጠን እና/ወይም ምትክ ቦታ ስፊትና አካባቢን ወይም ቤት በመግለጽ በጽሑፍ የማስለቀቂያ ትዕዛዝ መስጠት አለበት፡፡ ረ/ የሚለቀቀው ይዞታ የመንግሥት ቤት የሰፈረበት ከሆነ የማስለቀቂያ ትዕዛዙ የሚደርሰው ቤቱን ለሚያስተዳድረው አካል እና ቤቱን ለተከራየው ሰው ይሆናል፡፡ ሰ/ ተነሺን ከቦታው ማስነሳት የሚችለው ለተነሺው ካሣ ከከፈለ እና ምትክ ቦታ ወይም ቤት ከሰጠ በኋላ መሆን አለበት፡፡ ሸ/ መሬት የማስለቀቅ ስርዓት ዝርዝር አፈጻጸሙ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ ይወሰናል፡፡ 2. ተነሺ ወይም ሕጋዊ ወኪል ባለመብትነቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም ሠነድ በገጠርም ሆነ በከተማ መሬት የማስተዲደር በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል በሚያወጣው መርሐ-ግብር መሠረት ማቅረብ አለበት፡፡ 3.ተነሺው የካሣ ግምት በጽሑፍ እንዲያውቅ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ፦ ሀ/ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ተገቢው ካሣ ካልተከፈለው በመሬቱ ላይ ከቋሚ ተክልና ግንባታ በስተቀር ሌሎች ሥራዎችን መስራት ይችላል። ለ/ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ተገቢው ካሣ ካልተከፈለው በመሬቱ ላይ ማንኛውንም በፕላን የሚፈቀድ እና ቀጣይ የቦታውን የልማት ወጪ በመንግስት ላይ የማያዛባ ሥራ መስራት ይችላል፡፡ ሐ/ በዚህ ንዑስ አንቀጽ በፊደል ተራ “ሀ” እና “ለ” መሰረት የተሰራ ሥራ ወይም የተደረገ ለውጥ በካሣ ስላቱ ውስጥ እንዱገባ መደረግ አለበት፡፡ 4. የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የደረሰው ባለይዞታ ትዕዛዙ በደረሰው በ30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ ካሣ እና ምትክ ቦታ ወይም ቤት መውሰድ አለበት፡፡ 5. የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የደረሰው ባለይዞታ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 መሠረት በተቀመጠ ጊዜ ገደብ ውስጥ የካሣ ክፍያውን ካልወሰደ በከተማው ወይም በወረዳው አስተዳደር ስም በሚከፈት ዝግ የባንክ ሂሳብ እንዲቀመጥለት ይደረጋል፡፡ 6. ለባለይዞታ የሚሰጠው የመልቀቂያ የጊዜ ገደብ ካሣና ምትክ ቦታ ከተቀበለ ወይም ካሣው በዝግ ሂሳብ ከተቀመጠበት ቀን ጀምሮ ከ 120 (አንድ መቶ ሀያ) ቀናት መብለጥ የለበትም፡፡ 7.በሚለቀቀው መሬት ላይ ሰብል፣ ቋሚ ተክል ወይም ቋሚ የሆነ ሌላ ንብረት ከሌለ ባለይዞታው የልማት ተነሽ ካሣ ከተከፈለው በኋላ በ30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ ይዞታውን ለከተማ ወይም ለወረዳ አስተዳደር ማስረከብ አለበት፡፡ 8. በሕገ-ወጥ መንገድ በተያዘ ቦታ ላይ ለሰፈረ ንብረት ካሣ መክፈል ሳያስፈልግ ለ30 ቀናት የሚቆይ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ወይም በቦታው በሰፈረው ንብረት ላይ በመለጠፍ እንዲለቀቅ ይደረጋል፡፡ 9. የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የደረሰው ባለይዞታ ወይም ባለንብረት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ እና (2) በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያለ በቂ ምክንያት መሬቱን ካላስረከበ የከተማ ወይም የወረዳ አስተዳደሩ መሬቱን በራሱ ይረከባል። አስፈሊጊም ሲሆን ለመረከብ የፖሊስ ኃይል ትብብር ሊጠይቅ ይችላል፡፡ 5. መሬት እንዲለቀቅለት የተወሰነለት አካል ኃላፊነት መሬት እንዲለቀቅለት የተወሰነለት አካል ለሥራው የሚፈለገውን መሬት መጠንና የሚገኝበትን ትክክለኛ ስፍራ የሚያሳይ ውሳኔ የተሰጠበት ማስረጃ ቢያንስ ሥራው ከመጀመሩ ከአንድ ዓመት በፊት ለከተማው ወይም ለወረዳው አስተዳደር ማቅረብ አለበት፡፡ መሬቱ ለሕዝብ ጥቅም እንዱውል ሲወሰን የመሬት ይዞታቸውን እንዱለቁ ለሚደረጉ ባለይዞታዎች የሚከፈለውን ካሣ እና የመቋቋሚያ ድጋፍ ወጪ እንዱሸፌን ከተወሰነ ገንዘቡን ለከተማው ወይም ለወረዳው አስተዳደር ገቢ ያደርጋል፡፡ ገንዘቡ ገቢ ተደርጎ ለተነሺዎች ካልተከፈለ የከተማው ወይም የወረዳው አስተዳደር መሬት አያስለቅቅም፡፡ 6. የአገልግልት መስመሮች ስለሚነሱበት ሥርዓት የከተማው ወይም የወረዳው አስተዳደር በሚለቀቀው መሬት በላይ ወይም በታች የአገልግልት መስመር መኖር አለመኖሩን የአገልግልት መሥመር ባለቤት ለሆኑ ተቋማት ምላሽ እንዱሰጡበት በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረብ አለበት፡፡

መላኩ ፍቃዱ
መላኩ ፍቃዱ
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 21 July 2025 12:02:17 GMT
374952
4425
96
1725

Music

Download

Comments

ghiwetgirmay27
ghiwet :
ለመረጃው እጅግ እናመሰግናለን። እስቲ ስለ የእርሻ መሬት ወደ ከተማ ልማት ሲገባ ለገበሬው የሚሰጠው ካሳ የስንት ዓመት ካሳ እንደሚሰጥ መረጃ ኣካፍለን👏👏👏
2025-07-21 13:19:51
30
kiya5621
Kiya :
ምርጫ ሲደርስ ሁሉ ነገር ካሳ ይኖረዋል
2025-07-28 15:11:17
1
user2223500437491
user2223500437491 :
ይኸውልህ ለሚ ኩራ ለኮሪደሩ ልማት የተወሰደብንን መሬት ምንም ካሳ ሳይከፍለን 3 አመት አልቆ 4ተኛ አመታችንን ልንይዝ ነው ከተባበሩት አደባባይ ወደ አቤም የሚወስደው ግሪን 30 ሜትር የ15 ባለዬዞታ ካሳ አልተከፈለም እባካችው የሚሰማን አካል አጣን
2025-07-22 09:14:51
1
addaba4
addaba4 :
ማዕድን ያለበት መሬት በባለይዞታው ሊለማ ይችላልን
2025-07-21 13:46:33
2
user70088060818720
user70088060818720 :
ያለአግባብ ካርታ የተሰጣቸዉ ሰዎች ብንከሳቸዉም ፍርድ በቱም ለነሱ ነዉ የወሰኔዉ አርሶ አደሩ በምን አቅሙ ነዉ ይግባኝ ብለዉ ምከሰዉ ግዘዉ ብርሆነዋል ህግካለ ይስማን
2025-07-22 10:15:26
3
user5332602490228
አለ ግን የለም ማለት አድካሚ ነው!!? :
በጣም ጥሩ ወንድሜ። ጥያቄ የካሳ አከፋፈል ዝርዝር ዋጋ፣ካሬ መሬት፣ነባርና ባለይዞታ እናየውርስን ወዘተ ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ብታጋራን አባክህ(pdfካለህ በ0913940232 tem ላክልኝ።
2025-07-21 16:35:55
5
hello.666.or.777
Hello :
ምን ዋጋ አለው የተቆለፈበት ህግና አዋጅ በባለስልጣናት ፍላጎት የሚሰረግ እንጂ ህግ የታለ😁😁😁😁
2025-07-22 09:05:19
6
yonnites933
yoናs :
ከአመት በፊት ተነስተው እስካሁን ካሣ ክፍያ ያልተፈፀመላቸው አሉ
2025-07-22 07:25:05
4
cr7.suiiiiiiiiiii4
Cr7 Suiiiiiiiiiii :
የገበሬ መሬት የባለስልጣን ካቢታል ማስፋፊያ ነው እየሆነ ያለው ምሪት ይባላል የሚወሰደው ቦታ ላይ ቢያስ 4 ወይም 5ቦታ የመራሉ በመከላከያ ስም እያረጉ በሚሊዬን ሸጠው ይወጣሉ መልሰው ባዲስ ምሪት ደሞ ይገባሉ በተለይ ቃሉ ወረዳ
2025-07-22 14:13:38
2
havi0061
Havi :
በኦሮሚያ ክልል ማለትም በገላን ከተማ ለአዳማ ቆርቆሮ ተብሎ ተወስዶ እየው አመት ሊሆናቸው ነው አርሶ አደሩ ሲመላለሱ አቅመ ደካማዎች አሉ ጡረታ የሌላቸው በዚህ ለይ ግሪን ካርድ የሌለው ይበዛል በውር እና ባለ ይዞታ የሆኑ ናቸው አረ መፍትሄ አጡ አቤት የሚባልበት ጠፋ
2025-07-22 11:19:23
2
tesh0345
ተሸ ሳቅ በሳቅ :
ምን ዎጋ አለው ሁሉም ወሸት ምሬት ማውቀውለሁሉም ሰው ሲጥ ነው ማውቀው የባለስልጣ ስልጣን ለያዘ ብቻ
2025-07-22 11:15:45
1
user6186598234476
bekele :
ሳይከፈለን ሰባት አመት
2025-07-22 07:57:22
2
a611621
ዓ :
አራት አመት ሞላን ካሳ ሳይከፈለን
2025-07-21 15:24:06
1
pogacaruae
Lotto :
አቦ ገፈፉን እኮ
2025-07-21 17:19:04
2
kalebfanotayegmail.com
መድሎት/ወንድም ካሌብ :
አረ የት እንሂድ እኛ የቸገረን ህዝብ ማን ነው? ከህዝብ ነጥቆ ለግለሰብ ሲሰጥ ነው ያየነው
2025-07-22 04:02:15
1
sualihul2025
Aminu :
yametu mert awaje
2025-07-21 20:11:58
3
user901903755
abenezer :
የመንገድ ስፋትን ይመለከታል
2025-07-21 18:52:28
1
bogelamulata
B @ m :
ለመረጃው እናመሰግናለን፣በከተማ በሊዝ የተወሰዱ፣ፎቆች አስፓልት ዳር ያሉስ መረጃ ክለህ ብታጋራን
2025-07-29 09:04:52
0
wello1a
Abdurehman :
ለመረጃው ከልብ እናመሠግናለን ነገር ግን የካሳ ክፍያና ምትክ ቦታ ሳይሰጥ ከአንድ አመት ካለፈስ በመሬቱ ላይ ቋሚ ንብረትም ሆነ ቤት መገንባት ይቻላል ወይስ አይቻልም ብታብራራልን?
2025-07-27 14:50:45
0
livelyoracles
ማንጁስ :
thanks for sharing
2025-07-31 05:14:28
0
derejerpop
Dereje Mengistu👓 :
ወንድሜ እርዳኝ 1998 ጀምሬ የምኖርበት ቤት የይዞታ ማረጋገጫ የለኝም የቤተሰብ ውርስ የፍርድ ቤት ኣለኝ ግን የይዞታ ስለሌክ ብለው 1000 ካሬ ነበረ 620 መንገድ ወሰደው 480 ወንም ኣታገኝም ኣሉኝ ዩይዞታ ስለሌለክ ኣሉኝ
2025-07-24 05:05:13
0
aliebrahim544
Ali ebrahim :
የገጠር መሬት አስተዳደር ውስጥ በባለይዞታ ገበሬወች ያለን መሬት ለማህበራትና ለከተማ ልማት ከተከለለ 3 አመት አለፈው ገበሬውም ካሳ ሳይከፈል መሬቱንም ለእርሻ አገልግሎት እንዳይጠቀሙ ተደርጓል። ይህስ ጉዳይ እንደት ይታያል
2025-07-23 12:24:36
0
user5773078595304
የማሪያም የማሪያም :
በከተማ ውሰጥ ያለ የይዞታ ቦታ ቤቱን በህንፃ መነፅ ይችላል ? በአዲሱ አዋጂ መሠረት በእርሻ ቦታ ላይ ያለው የትኛውም አይነት አትክልት ካሳ ያስከፍላል ወይስ አያሰጥም ? ከባዶ የእርሻ ቦታ እና ከአትክልት የትኛው የተሻለ ካሳ አለው?
2025-07-22 11:23:43
0
asrar.ahmedin0
Asrar Ahmedin :
አበቴ፡ያአር፡ካርታ፡የላው፡ቤት፡ኦመላከታል።
2025-07-23 22:44:49
0
papiabi8
Abipapi :
አዋጅ ቁጥር 1336/2016 ተሻሽሎ ወጥቷል እኮ
2025-07-26 17:56:58
0
To see more videos from user @melakulegalcosultant, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About