@nar_dy: አምርሪያለው መሰል ግድ የለኝም ሂጂ መረብሽ ይስፋልሽ ሌላ ዘር አጥምጂ አምርሪያለው ስልሽ ለስንብቱ ቃል ደብዳቤ አትፃፊ ቻው ማለት ይበቃል ቻው ማለት ይበቃል ለእርምም ለስምም ሀክ እንትፍ ለማለት ሂጂ ልቤን ልየው እስኪ ይለይለት ይለይለት እስኪ ይቀላቀል ቀለም ሰው ቅፅበት ነው እንጂ ዘላለም አይደለም እንባሽን ጠራርገሽ ሂጂ ይቅናሽ አንቺም አወዮ ሴትነት… ስንቴ ታነቢያለሽ ለሰርግም ለፍቺም? አንዱ እንኳን ይቅርልሽ አንዱ እንኳ ይቅርብሽ ጀምሪው ንጋቱን ሂጂ ሳይመሽብሽ። እየሄድሽ… እግርሽን ከመሬት ብድግ አድርገሽው ብሆንም እንዳልሆን ግን ደሞ አውቃለሁኝ… በዚህ በኩል መሄድ … በዚያ በኩል መምጣት አንዳንዴ እንደሚሆን እግርሽን ከመሬት ብድግ እንደማድረግ መንበርከክ መለመን የትንሽ ሰው ማዕረግ አረግ… ግድ የለም ብረሪ እስክትሰበሪ ግድ የለም ቅዘፊ እስከምትጠፊ እስክትቀጠፊ አይንሽ አይን ይውጣል ይቀላውጥ ያማትር ሌላ ልብ ስፊ የኔን ልብ ይተርትር ታቀፊ በመዳፍ ታቀፊ በፍርጥም እንደ ካህን ጥምጥም ዙሪያሽን… ሰርክ ጠዋት ጠዋት ይክበብሽ ተባአት ሰው ይሁንሽ መአት አንቺ… አሜን በይ ከሰአት እራቂኝ ሂጂልኝ በእንባ ጉንጉን ደምቀሽ እራቂኝ ጥፊልኝ በእንባ ጉንጉን ደምቀሽ ግን…ይሄን ሁሉ ያልኩት ጤነኛ ሆኜ እንደው እይኝ ተደብቀሽ። #Nar_Dy #ኤልያስ_ሽታሁን #ግጥም
🅽︎ᴬᴿᴰʸ ✞
Region: ET
Wednesday 23 July 2025 16:12:27 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @nar_dy, please go to the Tikwm
homepage.