@melakulegalcosultant: የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ! ************** 1. ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡ 2. የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡ 3. ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:- 1=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው 2=በራሱ ፈቃድ 3=በጤና ጉድለት 4=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት 5=በሞት ናቸው፡፡ 4. የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:- 1= በእርጅና 2=በህመም 3= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ 4= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ 5=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡ 5ኛ. የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:- 1=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ5 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡ 2=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 5 ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም):: 6. በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:- * ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡ 7. በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡ 8. በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡ 9. የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡ 10. ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:- 1=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2) 2=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ 3= የጡረታ መለያ ቁጥር 4= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ 5= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ 6= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ 7= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ ናቸው፡፡
መላኩ ፍቃዱ
Region: ET
Thursday 24 July 2025 18:20:44 GMT
Music
Download
Comments
Amanuel Chucha :
28 ዓመት ያገለለ የመንግስት ሠራተኛ ጡረታ አሠራሩ ላይ 10x30%= 3 ነው፤ 18X1.25 = 22.5 ከሆነ 3+22.5= 25.5 ነው እንጂ 53.5 አይሆንም በዚህ ላይ ምን ትላለህ ?
2025-07-25 19:01:55
2
aberham ewnetu :
አንድ የመንግስት ሰራተኛ 10አመት እንዳገለገለ ስራ ቢለቅ የሰራበት ይከፈለዋል ወይስ እንዴት ነው
2025-07-25 05:30:40
15
senait :
10 አመት ያገለገለ ሰው ስራውን ትቶ ቢዋጣ እድሜው 60 ሲደርስ ጡረታ ይያዝለታል?
2025-07-25 10:42:04
1
sol :
አንድ ሰው አገልግሎቱ 25 ዓመት ቢሆንና ዕድሜው 57 ቢሆን በገዛ ፈቃዱ ጡረታ መወጣት ይችላል?
2025-07-25 05:51:13
2
Teme Boss28 :
እባክህን መልስልኝ 2አመት ከ7ወር ሰርቸ በራሴ ፊላጎት ተቋሙን ለቀቁ አሁን ከለቀኩኝ 2አመት ሞልቶኛል ጥቅማጥቅመን መጠየቅ ይችላለሁ????
2025-07-25 11:00:39
3
Shimekit :
ቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት የነበረና በጉዳት ቦርድ ወጥቶ የጡረታ መብቱ የተከበረለት ሰው። በሲቢል ስራ በቋሚነት ተሰማርት ጡረታ ሲወጣ ።ቀደም ሲል በጉዳት የጡረታ መብቱ የተከበረለትን ክፍያና ከተቀጠረበት መ/ቤት በእድሜ ጡረታ ሲወጣ በምን አግባብ ሁለቱን ማስታረቅ ይቻላል ። ከተቻለ አብራሩልን?
2025-07-25 21:11:34
0
Yenayt Esheta :
አንድ ሰራተኛ 10 አመት ሳይሞለው በጠረታ ቢሰናበት ምን ይኖረዋል
2025-07-26 05:46:10
1
Hamziya feyiso Tufa :
አንድ ሰዉ ጡረታ ስሞላ ቀንና ወሩን ሳይሞላ ቢቀር መቸ ተብሎ ይሰራለታል እባክ መልስልኝ
2025-07-25 14:45:38
1
Kin. :
10*30% =30 how?
2025-07-25 03:34:30
3
Befikir Gizachew Te :
የኮንትራት ቅጥር ስራተኞች የጡረታ አበል ይቆጣሉ ?
2025-07-25 14:12:53
2
መለኛው ደላላ ባህርዳር :
አንድ የመንግስት ሰራተኛ 10አመት ሰርቶ ጥሮታመውጣትይችላል?
2025-07-26 01:58:43
0
እንደ ፈቃድህ አኑረኝ :
ስሌቱ ላይ የ10 አመቱ አገልግሎት በ30% ተባዝቶ 30 የሆነበት ምክንያት አልገባኝም:ወይስ ተሳስተህ/ሽ ነው ማብራሪያ
2025-07-25 08:08:41
0
piter :
በዘጠኝ አመት በራሴ ፋላጎት ስራ ለቅቃለሁ የተቆረጠብኝ የጡረታ መቀበል እችላለሁ ???
2025-07-26 06:34:42
0
Demam Tseganeh :
መንግስት ሰራተኛ የሆነሰዉ በ53እድሜዉ እና አገልግሎት 26አመት ቢኖረዉ ጥሮታ ሊከፈለዉ ይችላልን
2025-07-25 12:07:09
1
Haptsh K. :
ከ ጡረታ ግብር ይከፈላል?
2025-07-25 05:58:53
0
Wendesen Mya 21 27✝️ :
የወንድሜን ልጅ በማደጎ ባሳድገው ጡረታ ለእሱ ማድረግ አልችልም?
2025-07-25 18:50:00
0
Dan :
የመስራት አቅም ካለው ከ60 አመት በላይ ከሆነ ጡረታ ሳይወጣ ስራውን መቀጠል ይችላል?
2025-07-25 11:21:56
0
Ermi Vatican :
ጡረታ ሚኒስትር የት ነው !? አዲስ አበባ የት አካባቢ ነው!?
2025-07-25 12:37:51
0
ሊቀ ጎጃም :
ጡረታ ማቋረጥ ይቻላል በራስ ተነሳሽነት!እንዲሁም ገንዘቡን ማስመለስ ይቻላል??
2025-07-25 07:56:13
2
Jetua :
እኔ ስቀጠር የጡረታ ፎርም አልሞላሁም ነበር ደጋግሜ ጠየኩ ግን ማሽኑ ተበላሽቷል ሌላ ጊዜ እያሉ በስተመጨረሻ መስሪያ ቤቱ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከስራ አሰናበተን ምን ተሻለኝ
2025-07-25 07:47:32
0
abeba :
በራስ ፍላጎት በ55 አመት ቢወጣ የጡረታ አበሉ 60 አመት እስኪሞላ ያስጠብቃል
2025-07-25 03:06:01
5
Abajobir Aba Dula :
በጣም ጥሩ መረጃ ነው በዝሁ ቀጥሉበት
2025-07-25 04:19:05
1
Queen Elleni :
55እድሜ 25የስራልምድ ካለው ጡረታ የተከፈለበት ከሆነ ይወጣል
2025-07-25 10:33:40
3
Abel Yefikirlij :
እኔ በምንግስት ቤት 22 አመት አገልግያለዉ የጡረታ ዕድሜዬ አልደረሰም ግን በህመም ምክንያት ስራ አቁሜ አንድ አመት ሆነኝ ደሞዜ የመጨረሻዉ የዲጊሪ ጣሪያ ላይ ነኝ በህመም ምክንያት ጡረታ ስወጣ ስንት ፐርሰንት ይደርሰኛል ? እንደ ህጉ አስረዱኝ ከይቅርታ ጋር 0911986117
2025-07-25 12:18:08
0
azezewassefa :
ጥሩ መረጃ ነዉ በዉነት ማህበራዊ ዋስትና ተሻሽሏል ማለት ነው
2025-07-25 07:57:11
2
To see more videos from user @melakulegalcosultant, please go to the Tikwm
homepage.