@tibletgiragn: የዓይኑ ቀለም ጥቁር አይደለም ያምራል፡በጣም ረዥም ነው፡ ደንገጥ ብዬ ወሬ ለመጀመር ሳብሰለስል፡ ለምን ወሬ ከማወራው በእጄ የያዝኳቸውን ፈተናዎች አላርምም ብዬ ማረም ጀመርኩ፡ ከዛ ራሱ ፈገግ ብሎ "አምጪው ያረምሽውን ልያዝልሽ" አለኝ፡ ሰጠሁት፡ ከዛ "set by Tiblet" ሚለውን አየና "ትብለጥ" አለ፡ ስሜ እኔ እንደሆንኩት ለመሆን እንደማያስችል ባውቅም ጉዳዩ በ"አቤት" እንደማይታለፍ ስለገባኝ በተቻለኝ መጠን ትብለጥ ሚለውን ወደ ምን እንደሆነ ባላውቅም ቀያይሬ "ወዬ" አልኩት "አስተማሪ ነሽ?" "አዎ" "ቆንጆ ነው" "እኔስ?" "አንቺም ቆንጆ ነሽ" ሳቀ (እግዜር ስራው ብዙ) እቀፈኝ እና የአንድ ሰው እንክፈል ለማለት ትንሽ ነበር የቀረኝ፡ "ጠጋ ብለሽ ቁጭ በይ" ስሩ ገብቼ ውትፍ፡ ቅጥነቴን አመሰገንኩት እንኳንም 45 ኪሎ ሆንኩ፡ ተመስገን የኔ ጌታ የበላሁት ሁሉ የት እንደሚደርስ እንዳላውቀው ስላደረከኝ፡ "ቅጥነቴ ውበቴ ሚሉት ለዚህ ነበር ለካ" አልኩ፡፡ ለትንሽ መንገዶች ዝም ከተባባልን በኋላ "ልጆችሽ ጎበዝ ናቸው" አለ "አዎ ግን ልጆችሽ መባል እንደምወድ በምን አወክ?" "ያው ልጆችሽ ማለት እኮ ናቸው" ፈገግ እያለ ታዲያ እያረምኩ ስሰጠው ሲቀበለኝ መውረጃው ደረሰ እና በመሀል "ውይ በቃ ልወርድ ነው ቻው ትብለጥ" ብሎ ጥሎኝ ወረደ.... እናማ ፍቅሬን ዓለም እያየ ወደ ፍልውሀ ሸኘሁት😭
Tiblet Giragn
Region: ET
Sunday 27 July 2025 17:58:48 GMT
Music
Download
Comments
remu baba 92👑 :
ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ልጅ በታክሲ በሚሄድ ወንድ ስትማለል😁
2025-07-28 10:18:10
196
GIዜ1216MAK :
ውይ ትብለጥየ ያን ቀን እኔም ስልክሽን ሳልወስድ በመውረዴ ተናድጀ ነበር።የት አግኝቸ ልቀበላት ብየ ሳስብ ነበር።ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በዚህ መልኩ ስላገኜሁሽ ደስ ብሎኛል።🥰የቀረውን ታሪክ አብረን እንቀጥልላቸዋለን በውስጥ አዋሪኝ ።
2025-07-28 02:52:39
0
Brkt,G✒️ :
በእበጥ ምትክ በልብ ቅርስ የተፈረመ exam sheet የደረሰው ተማሪ😁
2025-07-27 18:39:51
246
Aman :
እቀፈኝ እና የአንድ ሰው እንክፈል
2025-07-27 18:31:47
116
Bling :
🤣🤣🤣 እንዴ ሚስ💥
2025-07-29 12:38:31
8
ጌትነት ♏✝️3️⃣3️⃣3️⃣ :
ደሞ በ tiktok መጣሽ
2025-07-28 03:43:21
1
Awi-Lemon :
ትብለጥ እህቴ ምን መሰለሽ: አሁን ይህችን 45ኪሎ ወስጄ ምን ላድርጋት? ለእናትና አባቴስ ምን ብዬ ላስተዋውቃቸው ነው? የአልሚ ምግብ እደላ ኤንጅኦ ድርጅት ለጊዜው ቤትህ ወስደህ አቆይልን ብለውኝ ነው ልበል? እያለ ሲወዛገብ ቆይቶ ኧረ ላሽ በቃ መውረጃዬ ደረሰ ብዬ ላምልጥ ብሎ ነው የወረደው እንጅ የመጨረሻው ፌርማታ ወራጅ ነበርኮ😂😂😂
2025-07-28 10:34:26
5
Absalat eshetu :
ከለማ ይሄ ይሻላል ለማ ከምር ሳላውቀው ነበር የጠላውት በተለይ መብራቱን ስያጠፉት የጮኸ ግዜ😭💔😂😂😂
2025-07-27 18:50:58
7
Amen 12 Meski :
ወይ ትብለጥ 😁😁
2025-07-31 21:27:02
1
spaghetti Mafia :
romantic tragedy yehone film
2025-07-28 12:02:56
1
3H :
32 ደቂቃ በታታ ነው
2025-07-30 15:05:49
2
User9111 :
Literally አሁን ታክሲ ውስጥ የ 12 ደቂቃ ፍቅር አጊኝቼ ወረድኩ😂። ከፈለችልኝ ሁላ። ለካ ህዝቤ ሁላ ታክሲ ውስጥ እየተፋቀረ ነው
2025-07-28 06:56:37
3
yadahabeshawi12 :
ውሀ በላሽ😂
2025-07-29 19:51:30
2
𝕄𝕚𝕜𝕒𝕨 1012 :
ብትንግሪኝ እኮ 1 ሰዓት እናደርገው nber
2025-07-28 07:02:18
1
Kale kiristose@21 :
ጉድ ነው የ32 ደቂቃ ፍቅር😂😂የዶክመተሪ ፍቅር ነው በይኛ
2025-07-28 10:56:32
1
AB z :
32 dekika hula kjemo mexico nw
2025-07-28 11:06:31
1
Begize OptiMAX :
አንች ከሆንሽ የፃፍሽው የእውነት ጎበዝ ነሽ🥰
2025-07-29 09:42:42
1
Abel Tesfaye 🦅 :
32 ደቂቃ ከጀሞ ኮዬ ነው አ
2025-07-28 11:11:09
1
HENOK Tesfa :
እና ስምሽ ነዋ ጠላትሽ
2025-07-27 19:22:09
26
Tedy :
Ere 1 seat yhunlat 😁
2025-07-29 09:38:49
0
Zeberga :
የአይኑ ቀለም ጥቁር ቢሆን የተሻለ ይሆን ነበር
2025-07-28 08:22:44
1
Emric :
ፀሃፊዋ🔥
2025-07-29 06:34:45
1
Moshe Dayan :
የልጄ ፈተና ወረቀት ላይ የተፃፈዉ የስልክ ቁጥር ሚስጥር አሁን ገባኝ ምን ያደርጋል በዉጤቷ በጣም ተናድጄ ፈተናዉን ቀዳድጄ ጣልኩት እንጂ
2025-07-27 21:01:11
39
Beya :
ከኔ ጋር ቢሆን ደግሞ ያረምሽው ሳይታጨድ ድረስ ጥየሽ አልሄድም ነበር።
2025-07-29 17:51:30
0
call me fun💀 :
33 ደቂቃ ቢሆን አሠብኩት😂😂
2025-07-28 07:06:45
1
To see more videos from user @tibletgiragn, please go to the Tikwm
homepage.