@iseefurniture: 0909230000 #homedecor #dinningtable #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #viral_video #addisababa #addisababa #interiordesign #metalart #sofacover

I see furniture
I see furniture
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 28 July 2025 11:49:30 GMT
120885
6289
2480
903

Music

Download

Comments

umuadil30
Bint Naik :
ረጅም ዓመት ወደ ኃላ....አባቴ ሱቅ ይሰራ ነበር እናቴም አልፎ አልፎ አብራው ትሆን ነበር:: አንድ ቀን ብቻዋን ሳለች አንድ ደንበኛ መጥቶ condom ይጠይቃታል "condom ምንድነው" ስትለው የሚቀመጥበትን ቦታውን ሰለሚያወቅ በምልክት ያለበትን ያሳያታል እሷ ደሞ ይሄንንማ በ እጄ አልነካም ብላ father እስኪመጣ ጠብቆ ገዝቶ ሄደ ይሄ የዋህነቷ ሁሌም ያስገርመኛል አሁን ግን ታማብኛለች 😢😢😢😢😢😢 ምንም አታቅም አታወራም አትራመድም ልጆቹዋንም አታቅም ምን አልባት ካሸነፍኩ ለ እናቴ diper
2025-07-28 20:31:34
421
missesru
Miss Esru :
University ስሄድና ለ ስራ ወደ AA ስመጣ አይኖቻ ላይ ያየዉት እንባና ፍረሀት፣ ሳጠና ቁጭ ብላ ለሊቱን አብራኝ ምታሳልፈዉ፣ ሲያመኝ የምትጨነቀዉ …….ሁሉ ነገር ብቻ እናት እንቁ ናት። እናታቹን ጌታ ያቆይላቹ!!!
2025-07-28 17:55:58
5
m8815141prk
የኢትዮጵያ ሰላም ናፈቀኝ :
እናቴ ለልጆችሽ ስትይ ከሰዉነት ተራ ወተሽ ህመምሽን ደብቀሽ ኑረሻል እግዚአብሄር የምለምነዉ አንችን ለወርም ቢሆን የሚያስፈልግሽን ነገር ሳላረግ እርፍ ሳላረግሽ እንዳልሞት ነዉ
2025-08-02 03:38:10
0
evaenaenatwa
ኢቫና እና እናቷ :
አንድቀን ከባሌ ተጣልቼ ሳለቅስ ሰማቺኝና ልጄ እኔኮ ከምበላት ለይ ማጠራቅማት ሳንቲም አለችኝ ላንቺ አንድቀን ከፍቶሽ ስራ ብታጪ ብዬ ብላ ያጠራቀመችዉን ገንዘብ ሳየዉ ደነገጥኩ በዝቶ ወይም አንሶ ሳይሆን ለራሷ ጫማ እንኳን ሳትገዛ ልጄ ከፍቷት ብትመጣ ብላ ማሰቧ አስደነገጠኝ😢😢😢😢😢😢😢
2025-07-28 17:49:27
668
noahyeshi
Noah_Yeshi @16 :
የዛሬ 30 አመት 4 ሴቶች እድሜቸው 6,4,2,1 ዓመት ልጆችን ጥላ አረፈች እናቴ . ለአባቴ ከባድ ግዜ ነበር እሱም 1 ድም ቀን እንዳይከፋን አድርጎ የሱን ደስታ ምቾት ትቶ ለኛ ኖረ አላገባም ። እና ይህ አባት እናት መባል ይነሰው
2025-07-28 17:18:19
226
diborah26
Diborah :
እናቴ በጣም ምትገርም ሰው ነች 7 ልጆችን ከወለደች በኋላ ትምህርቷን ካቆመችበት ከ9ነኛ ክፍል ቀጥላ አሁን ጨርሳ ቅዳሜ ትመረቃለች ጥንካሬዋ ይገርመኛል
2025-07-28 20:19:38
99
berabera83
brhan :
ልፅፍ ኣልኩና እንባየ ኣልቋረጥ ኣለኝ የቱስ ቃል ነው የኔን እናት የሚገልፃት ግን ባለፈው እናቴን ሳያት ኣነገቷ ተሸብሽቦ ሳይ እመቤቴን እባክሽን ትንሽ ቀን ሳላሳርፋት አናቴ እንዳታረጅብኝ በየ ለመንኳት🥺 ኣንድ ቀን እንኳን ጥሩ ኣልጋ ለይ ሳትተኛ ለኛው ምቾት እንደኖረች ግን ይሁን እንደዚሁ ሁና ትኑርልኝ ኣንድ ቀን እግዚኣብሔር ሲፈቅድ እክሳታለው🙏🥺🥺
2025-07-28 19:14:53
74
user2137662543258
Hiwi Bonda :
እናቴ በጣም ወድሻለው የመንግስት ሰራተኛ ናት እና ሳይክል ካልተገዛልኝ ብዬ ተገዛ ግን ትወድቃለች ብላ እሶ በእግር እኔ በሳይክል ትምህርት ቤት አድርሳኝ ትመለሳለች አሁን ድረስ አታምነንም ሁላችንንም ቤት ይዘንም
2025-08-01 14:09:43
1
rebza90
Rebza (ሳሟ) :
ጉርምሳ ገና እየፈነዳሁ ባለሁበት ወቅት ነበር ከላይ ለስላሳ አስቀምጬ ከስር ቢራ የጀመርኩበት 2000 ሚሊኒም አከባቢ ነው አንድ ቀን በጥናት ሰበብ አልመጣም ብዬ የመጀመሪያዬን ስካር ሰክሬ ከቤታችን ፊትለፊት ወዳለው ግንብ ግቢ ( የጓደኞቼ ቤተሰብ ቤት ባዶ ግቢ) በግንቡ ተጠላጥለን ለመግባት እኔ ስልክ እንጨት ላይ አየወጣሁ ግንቡ ጫፍ ልደርስ ስል ከስር ድምጽ ሰማሁ እባክህ ልጄ ና ውረድ አይዞህ ና በበር ግቡ ዝቅ ብዬ ሳያት እናቴ አቤት ድንጋጤ ሳቅ ሁሉም ነገር ተቀላቀለብን መቼም አረሳውም አይ እናት ለሊት ሙሉ እስከ 8 ሰአት አየጠበቀችን ነበር ለካ አሁን የልጅ ልጅ አሳይቻት በተቻለኝ እየጦርኳት ነው አልጋ ግን እኔ የተገረዝኩባት ሶፋዋም በወቅቱ ውድ የተባለች ነበረች እነሱን መቀየር ግን አሁን ከበደኝ ምክንያቱም ልጆችም እዚህም ቤተሰብ መስርቻለሁ ይቅናህ በሉኝ
2025-07-30 18:42:14
0
seada.queen
seada Queen❤ :
እንኳን ወደ ኮሜንት ሴክሽን በሰላም መጡ ሻይ ወይስ ቡና 😁😁😁
2025-07-29 18:37:32
1
um.rdu.123
ረዲና የአቤኑ እናት🧑🌍 :
እናትነት ምን እንደሆነ አላውቅም በ8 ወሬ ነው የሞተችው🥺😭😭ግን አሁን እናት ሆኛለሁ ከእርግዝናዬ ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት ከልጄ ጋር የማሳልፋት ጊዜ እናቴን እንድወዳት ያደርገኛል ለልጄ የምከፍለው መሰዋትነት ወይም የኒ ያልሆነ ማንነት መኖሬ ቅር አይለኝም🥺😭😭😭🙏🙏🙏ብትሸልሙኝ ደስ ይለኛል
2025-07-28 21:29:54
12
hibist69
HIBIST🧚‍♀️🧚‍♀️ :
እህቴ ከኔ ከፍ ትላለች እኔ ልጅ ነበርኩ የምንበላው ምግብ ትንሽ ነበር ያን ምግብ አብልታን እሷን እንዳይርባት ሚጥሚጣ በውሀ በጥብጣ ጠጥታ ያደረችው እለት መቼም አይረሳኝም ያም ቀን አልፎል ይሄም ያልፋል🥺🥺
2025-07-29 07:27:14
20
tirhastiru
tirhas :
በጣም ናፍቀሽኛል ግን አላገኝሽም ብዙ ሚስጥር አለኝ ግን አልነግርሽም ትልቅ ስጦታ አለኝ ግን አልሰጥሽም ምክንያቱም አላገኝሽም የእውነት አሁንም ኮራ ብዬ የምሄደው ያንቺ ልጅ ስለሆንኩ ነው ብዙ ጨለማዎችን አብረን ተሳስቀን ብርሀን መስለውን አልፈናቸዋል እልፍ ችግሮችንንም አብረን በፍቅር ቸቸግረን አልፈነዋል ምክንያቱም ጠንካራና ጀግና እናቴ ስለነበርሽ ነው አሁንም ልክ እንዳንቺ ጠንካራ ለመሆን እየሞከርኩ ነው ላንቺ ይሄ ቀን ይገባሻል የኔ ንግስት አንቺ የአለም ምርጣ እናቴ ነሽ ናፍቀሽኛል አልልሽም ታቂዋለሽ የኔ ንግስት ፈጣሪ ነብስሽን ይማርልኝ ♥♥♥፨፨፨
2025-07-29 20:18:57
1
eldanaaragie
𝓮𝓵𝓭𝓪𝓷𝓪🦋🦋🦋 :
የኔ እናት ከአራስ ቤት እስከ እዚ እድሜየ ለብቻዋ ለፍታ ማንም ሳያግዛት ያለ አባት ለሰው ቤት ዉሀ እየቀዳች የውሀ ጀርኒካ በጀርባዋ እኔን በፊቷ አዝላ ብዙ ሆና ነው ያሳደገችኝ ግን እናቴን አንድ ቀን ሳላስደስታት እንዳላጣት እፈራለሁ
2025-07-29 10:22:13
20
teddysoldier3
soldier3🌴🌴🌴 :
ከ9 አመት በፊት ከደሞዟ ላይ ደሞዝ ነበረኝ አሁን ሳስበው ይገርመኛል አንሶኛል ብየ ከ600 ወደ800 ደሞዜ በጣም የሚገርመኝ ጀለሶቼ ሁሉ አብረው ይጠብቁ ነበር የኔ ውድ አራዳ እናት አፈቅርሻለሁmom
2025-07-29 19:23:53
4
aba.sisay
Aba Sisay :
ልጅ አያለው ebat ወስጥ ምግብ ልንበላ ብለን የምግብ አጥረት አንዳለ kawekich egha ብቻ አንድንበላ ብላ yihan ምግብ ሲበላ እኮ yameghal አይስማማግህም ብላ ቶምዋን ምታድረዌ niger ይገርመኛል
2025-07-30 10:05:05
2
rachelblacky2
🌔Rachel 🌼 :
ማልቀስ አይቻልም 🥺?
2025-07-28 20:46:47
21
bethlihemassefa
bethlihemassefa :
ስለ እናቴ ተናግሬ የሚያልቅ አይደለም ተከታታይ መፅሀፍ ብፅፍ እንኳን አያልቅም እናቴ በጣም ምታሣዝን እናት ናት በብዙ ስቃይ ያለፈች 7ልጆቾን ለብቻዋ ያሣደገች አንድም ቀን ለራሶ ያልኖረች በአዘን የተጎሣቀለች
2025-07-30 05:40:10
3
eskendir.desta
Lalalalapa :
በ8ዓመቴ እናቴ እና አባቴ ተለያዩ እኛ ከአባታችን ጋር ቀጠልን ማረሳው ት/ቤት ፀጉር ማበጠሪያ ይዛ መጥታ ታበጥረን ነበር ያኔ አቅሞ ይህ ብቻ ነበር በጉጉት በፍቅር ምንናፍቀው ቀን ኑሪልኝ እናቴ አለፈ ያጊዜ ከአባታችን ያለያዩሽ እኛን እናትነትን የነጠቁን ግን ይሁኑ የአልሻቸውን ሆኑ አለፋ
2025-07-30 19:38:53
1
user6519240493466
ረቡኒ :
እናቴ ትምህርት ቤት ልሄድ መሳፈሪያ ሳጣ ብረታብረት ለቅማ ሽጣ ቡና መጠጣት እያማራት ምንም ሳታስቀር ለመሳፈሪያ ሰጠችኝ ያን ጊዜ አረሳውም😭😭😭😭😭😭
2025-07-31 12:21:37
1
juweriaonlineshop12
🦋Juweria🦋 online shoppin🛒🛍 :
እናቴ...በእንቅልፍ ሰመመንውስጥ ሁኜ በስጋት የልብ ምቴንያዳመጥሽውንን...እናቴ በሳቄ ውስጥሀዘኔን ያነበብሽው በምንም በማንም የማልተካሽ እቅፏ፣ጉርሻዋ የማይጠገብ።ማግኘትማጣት የማይለውጥሽልጅሽመሆኔን ብቻ ያየሽ እናቴ ብቻ ነሽ
2025-07-29 16:58:09
1
emu21mam
Emu😘 :
እናቴ ብቻዋን ነው ያሳደገችኝ 😍,ሳጠና ቁጭ ብላ ለሊቱን አብራኝ ነው ምታሳልፈዉ፣ ሲያመኝ የምትጨነቀዉ …….ከዛ ሁሉ ነገር ግን 12ኛ ክፍል eyetemarku, ከገጠር ከተማ ሂጄ ነበር እማር የነበረው, አልቻልኩም tekerayehu,  ቢያንስ 10ኪ.ሜ ይሆናል መንገዱ  እናቴ ማገዶ ተሸክማ ታመጣልኝ ነበር...😌 አንድ ቀን ግን ማገዶ ተሸክማ ስትመጣ ቤት ስትገባ እሚበላ የለኝም... እንጨቱን አስቀምጣ ያን ሁሉ መንገድ😭😭 ተመልሳ ሂዳ ገጠር ደርሳ ለኔ እንጀራ ይዛ ያን መንገድ ተጉዛ ተመልሳ መጣች😭😭😭, ያን መንገድ እኮ እኔ ሳስበው አሁን ድርስ ዉስጤ ይረበሻል, ግን እኔ አሁን ምንም አለማድረጌ ሁሌም ይከፋኛል😭😭😭 ስላወራሁ  Bayiwetalgnim tinsh kelognal Thankyou 😍😍😍
2025-07-30 16:23:01
1
amaya_962
°~Ämaya ~° :
ስለ እሱዋ ቃላት ያጥሩኛል ትግስቱዋ ፅናቷ ያስገርመኛ ሕይወቱዋን በሙሉ በችግር እና በፈተና ነው ያሳለፈችው ግን ሁሌም ቢሆን አመስጋኝ ናት አታማርርም የሴቶች ሁሉ ጀግና ናት በልጅ በባል በቤተሰብ በሕይወት ያልታደለች ናት ግን አታማርም በፈጣሪ ላይ ትልቅ ተስፋ አላት የኔ ጀግና እናት እወድሻለሁ 🥰
2025-07-29 06:45:58
3
betelhame.s
#Betelhem :
እናቴ ለኛ ብላ ያሳለፈችው ብዙ ነው አንዳንዴ እራሴን ወቅሳለው በመሀላችን ብዙ ነገር ተፈጥሯል እማልዘረዝረው ጥፋተኛ ሳረጋት ኖርያለው መቻል ስም ቢኖረው የእናት ነው ባሁን ሰአት በሷ መመረቅ ነው ምፈልገው መዳኒአለም ቢረዳኝ🥺
2025-07-28 17:57:08
5
adeyzsaba
አደይ ዘ ሳባ :
እማ ታማብኝ hospital ገብታ ነበር በጣም አሟት ስለነበር አልጋ ትያዝ ሲባል ለልጆቼ ምሳ ሳልሰራላቸው ብላ "ሂዱላቸው" ያለችን ቀን🥺 የኔ እናት የደሀ ሁሉ እናት ቤቷ ተከራይቶ የገባ ሁሉ የራሱን ሳይገዛ የማይወጣባት, ለእህል ማስፈጫ ሳይኖራት ለተከራይዋ ከሰረች ብላ ከየት አምተው ይከፍሉኛል ብላ ብድር የምትገባው, ከ2008እስከ አሁን በ 500 ብር ኪራይ የሚኖሩባት እናት. . እማ🥺 . .አለሁ አይዟችሁ ያልሻቸው ባያስቡሽም. . ሳልደርስልሽ ክፉ አይይብኝ🙏 እወድሻለሁ እማ ለጊዜው ያለኝ ይሄ ነው❤🥺❤
2025-07-28 21:42:07
6
To see more videos from user @iseefurniture, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About