@gigi_shebabawfan2: ዓባይ በጂጂ ዜማ #ጋዜጣ_ፕላስ | እነሆ የዓባይ ቁጭት ወደ ፈንጠዝያ ሊቀየር ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። ከተጓጓለት ብስራት አስቀድሞ ቁጭትን ወስውሰው፤ የተዳፈነውን ረመጥ ቀስቅሰው እጆቻንን ለሥራ ያበረቱ በርካቶች ናቸው። ሀ ሳይባል ሁ ብለው አንድ ሳይባል ተሻግረው ሩጫውን ጀምረው ያስጀመሩ፤ በዜማቸው የቆሙትን ያንደረደሩ ምሥጋና ይገባቸዋል። ቁጭት ለዘመናት የተንቆረቆረባቸው፤ እነኛ አንጎራጓሪዎች ዛሬ ላይ የደስታ ዜማ ሊቀኙ ነው። ዓባይ ባዕድነቱን አቁሞ በትውልድ ሀገሩ ጎጆውን ቀልሷል። ኢትዮጵያም የእናትነት ወጓ ደርሷት በልጇ ልትጦር የመስከረም ጠባትን እየተጠባበቀች ነው። ኢትዮጵያን የዓባይን ታሪክ ግርማውንና ምስጢሩን ይተርካሉ። ከተረክ ተሻግረውም በመረዋ ድምፅ ያዜሙታል። ስለ ዓባይ ዕልፎች በየትየለሌ ስልተ ምቶች ሁሉ አዚመዋል። ከኢትዮጵያ በገና እና ከበሮ ጋር ተደባልቆ እንደ ዥረት እንዲፈስ ጠብታቸውን አዋጥተዋል። የሷ ግን ከሁሉ ይልቃል ለማለት የሚያስደፍር ነው። ገለባ የሌለበት የቅኔ ፍሬ በውሃ መልክ ለሚፈሰው ጥቁር ወርቅ አንካችሁ ብላለች። ብቻዋን ሀገር ሆነ ሄደብኝ ብላ አልቅሳለች። ለዓባይ ንግስቱ ናት፤ እንዳሻት የምታዘው። በእሷ ራሳችንን እናያለን። ደስታን እንቃርማለን። ዓባይን በዜማ ከሰከላ ተነስታ እዚያ በረሀ ድረስ ትሸኘዋለችና፡፡ ሀሳቧን፣ አመክንዮዋን፣ ቁጭቷን፣ ተስፋዋንና ችሎታዋን በዓባይ ውስጥ እንደጅረት ታፈሰዋለች፡፡ ዜማዋ በጊዜና ታሪክ ሰርክ እንደ አዲስ እያደር የሚናፈቅ፤ በይደር የሚጎመራ፣ በቃል የሚገለጽ ሳይሆን ለዘመን የጸና ሀሴት የታመቀበት ነው። በረቀቀ ቅኔ በአዲስ አስተሳሰብ በዓባይ በውበት ተገለጠች፡፡ ስለዓባይ ሲነሳ አብራ ትነሳለች እጅጋየሁ ሺባባ ወይም ጂጂ፡፡ እሷ እንደዓባይ የሀገር ሀብት ናት፡፡ የሀገር ጸጋ። የሀገሬው መኩሪያ። እሷ ማለት ጥበብ ለራሷ መኖሪያነት ወገቧን ታጥቃ የኳለቻት ሴት ናት። በማይነቃነቅ መሰረት ጥበብ ጎጆዋን የቀለሰችባት። የኢትዮጵያዊነት ገድል መፍሰሻ መንገድ ናት። በዜማዋ ለአፍታ እንኳን የማይናወጥ እንደአለት የፀና አንድነት ሰጠችን። በግጥሞቿ ውስጥ እልፍ ጉዳዮችን፣ የጥበብን ጥግ በሰላ ብዕሯና በዜማ ዓይናችንን ገለጠች፡፡ ጠያቂም አደረገችን፡፡ ሀገር በተሰራችባቸው ጽንሰ ሀሳቦች ሁሉ ሀገርን አየንባት፡፡ ስለ ዓባይ አዜመች የማያረጀውን ውበት የማያልቀውን ቁንጅናውን አሳየችን፡፡ ‹‹ትናገር አድዋ›› እያለች በወኔ ሞላችን የተከፈለልንን መስዋዕትነት ፍንትው አድርጋ በልባችን አተመች፡፡ የወንዙን አውራ ዓባይን የእሷ፤ የብቻዋ አደረገችው፡፡ ‹‹ፍልቅልቅ ፍልቅልቅ አንች ውብ ከተማ ዓባይ ባልሽነው ወይ ሰማሁኝ ሲታማ ሀብታም ባል እያለሽ ምነው ደህይተሻል ብራንባር አልቦሽን ሽጠሽው በልተሻል›› ይህ ግጥም ዓባይ በሚለው ለእጅጋየሁ ሺባባ ሙዚቃ ውስጥ ሊካተት ተጽፎ ቢዘጋጅም በሙዚቃው ላይ ማካተት እንዳልተቻለ በአንድ ወቅት ከኢትዮጵያ ሬድዮ ጋር በነበራት ቃለመጠይቋ ተናግራለች፡፡ ፍልቅልቅ በዓባይ በረሃ ውስጥ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ ዓባይ በስሯ እየሄደ ብራንባሯን ሽጣ የምትጠማ ከተማ እንደሆነች ለመግለጽ፡፡ ‹‹ዓባይ አስተምሮኝ አጉል ደግነት፤ ቤቴ እየተራበ ሳበላ ጎረቤት፤ ምን ይለኛል ሀገር ምን ይለኛል ሰው ዓባይ ወንዛ ወንዙ ብዙ ነው መዘዙ›› በተጨማሪም በዚሁ ቃለ መጠይቋ በዜማዋ እያንጎራጎረች ‹‹ይህን ዘፈን ስሰራ በርካታ ግጥሞች ነበረው፤ ግጥሙ በዝቶ አወጣነው›› ስትልም ተናግራለች፡፡ “የማያረጅ ውበት የማያልቅ ቁንጅና፣ የማይደርቅ፣ የማይነጥፍ ለዘመን የጸና፣ ከጥንት ከፅንሰ አዳም ገና ከፍጥረት ፣ የፈሰሰ ውሃ ፈልቆ ከገነት” ብላ ትጀምራለች፡፡ የዓባይን ዘላለማዊነት በሚገልጹ ቃላት እያሽሞነሞነች፤ ˝የማይነጥፍ፣ የማይደርቅ˝ እያለች የዓባይ መነሻ ከኤደን ገነት እንደሆነ ትነግረናለች፡፡ የዓባይን ውበት፣ ቁንጅናና ዘላለማዊነት ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ድረስም በሙዚቃው ውስጥ ትገልጸዋለች፡፡ ቀጠለች ˝ለዘመን የጸና˝ አለችው፡፡ የጎመራውን የዓባይ ውበት ህይወት ዘራችበት ለትላንት፣ ለዛሬ፣ ለነገም ይሰራ ዘንድ፡፡ ‹‹ግርማ ሞገስ ፣ የሀገር ፀጋ፣ የሀገር ልብስ… ግርማ ሞገስ…ዓባይ፣ የበረሀው ሲሳይ›› በስርቅርቅ ድምጿ ‹‹ግርማ ሞገስ›› አለችን የሀገር ፀጋነቱን፣ የሀገር ልብስነቱን አስረዳችን። ዓባይ ከእግዜሩ የተቸረን እንደሆነ ነገረችን፡፡ ዓባይ መኩሪያችን ነው አለች፡፡ ዓባይ ሲርበን ሲጠማን መሸሸጊያ ልብሳችን ነው አለችን፡፡ በዚያ ግን አላበቃችም ቀጠለች፡፡ ‹‹ብነካው ተነኩ! አንቀጠቀጣቸው፣ መሆንህን ሳላውቅ፣ ስጋና ደማቸው፡፡ የሚበሉት ውሀ፣ የሚጠጡት ውሀ፣ ዓባይ ለጋሲ ነው በዚያ በበረሀ፡፡ ዓባይ… ዓባይ… ዓባይ… ዓባይ፣ ዓባይ ወንዛ ወንዙ፣ ብዙ ነው መዘዙ›› ˝ዓባይ ወንዛወንዙ ብዙ ነው መዘዙ˝ የሚለውን የዜማውን ግጥም ስትደጋግመው ትስተዋላለች፡፡ ሀረጉ ዓባይ ለእኛ ለኢትዮጵያውን የሚሰጠውን ጥቅም ብቻ ሳይሆን፤ ያለውን ፓለቲካዊ አንድምታም ጠቁማለች፡፡ ለማይደርቅ፣ ለማይነጥፍ ውበትና ቁንጅና ቋማጩ እልፍ ነው፡፡ በዚህ ዜማም የጎረቤቶቻችንን ፍላጎትና መቋመጥ ነገረችን፡፡ እንዲሁም ዘመን ተሻጋሪ በሆነ መልኩ የዚያኛውን ወገን የፍርሃት ስሜት እና ፍላጎት ገልጣለች፡፡ "የሚበሉት ውሃ የሚጠጡት ውሃ" አለችን ዓባይ ለእነኛ ሰዎች ህይወታቸው እንደሆነ ሹክም አለችን፡፡ ‹‹ዓባይ የወንዝ ውሀ፣ አትሆንም እንደሰው፣ ‘ተራብን፣ ተጠማን'… ‘ተቸገርን' ብለው፣ አንተ ወራጅ ውሀ …ቢጠሩህ አትሰማ፣ ምን አስቀምጠሀል ከግብፆች ከተማ›› ስትል በዜማዋ ዓባይን አናገረችው "ዓባይ ወንዛ ወንዙ - ብዙ ነው መዘዙ" ብላም ልክ እንደ ሸማኔ በውብ ግጥሟን ቋጨችው። ስለ ዓባይ ውበት እና ጉልበት እጅጋየሁ ሽባባው ዘመን ተሻጋሪ የኪነጥበብ አሻራዋን አሳረፈች፡፡ ዓባይን የገለጸችበት መንገድ በኢትዮጵያውያን ልብ እንደእንቦሳ እንድትቦርቅ አድርጓታል። ዛሬም ድረስ ስለዓባይ ሲነሳ ቃላት ያጥረን እንደሆን ወደ ጂጂ ዘፈን ጎራ ማለታችን አይቀርም። በቃልኪዳን አሳዬ ++++++++++++++++++++++ @ጋዜጣ_ፕላስ
gigi_shebabaw fans
Region: SA
Saturday 09 August 2025 18:11:29 GMT
Music
Download
Comments
neba🍓13 :
አይ ጂጂዬ አባይን እንደሰው እኮ ነው ያውራችው ❤
2025-08-10 06:41:40
32
nani Seifu :
ጂጂየ የኔ ዉድ ፈጣሬ ወደትክክለኛ ቦታሽ ይመልስሽ የኔ ዉድ
2025-09-09 12:23:23
1
ጎጃሜዋ ባለማተቧ የአባይ እህት ✝️✝️🖤💔🖤 :
የሴቶትች ትምሳሌት የወዜ ሽታ ሁሌም ሰላምሽ ብዝት ትርፍርፍ ይመልልኝ የኔ እቁ🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙❤❤❤❤💙💙💗💗💗💗
2025-09-28 18:37:07
0
ሙልየ, :
ጂጂየ ሁሌም ምኞቴ ደሥታሽን ማየት💞💞💞
2025-09-30 18:02:03
1
selam :
ጂጂ ፡ ለአባይ ፡ ምርቃት ፡ መገኘት ፡ ነበረባት🙏🙏🙏🙏
2025-09-28 06:29:53
1
fiker 🫶💚💛♥️ :
እንደዉ ስወድሽ የኔ ንግስት🥰🥰
2025-09-25 04:06:33
0
Eshetu :
ሰለ አባይ ቀድማ ያቀነቀነች ብርቂዬ የኢትዮጲያ ልጅ ጂጂ ዕድሜ ይሰጥልን
2025-08-09 20:58:17
15
user2807531970060 :
ጂጂዬ ሁሌም እንደ አዲስ ታሰለቅሺናለሽ አረጅም እድሜ
2025-09-11 21:27:28
3
Mohammed Adem :
አባይንየዘፈነቺለትጅጅእሄነዉእስቀድሞስላገሩመዝፈን
2025-09-19 13:39:17
0
አልታሠብ :
ማንም ስለ አባይ የመጻፍም የመዝፈንም ሞራል የለውም ጂጂን ከሠማ በቃ አለቀ
2025-08-10 07:22:48
2
eskedar12 :
የማያረጅ ውበት የማያልቅ ቁንጅና ..........ጂጂ🥰🥰🥰🥰🥰 አንች ብቻ ዝፈኝ.
2025-08-19 18:23:25
2
Admas Tigistu :
king off king!¡!
2025-09-16 20:45:55
0
Abrish❤የእንጅባራው :
የኛ ንግስት ሁሌም ክበሪልን ጂጂዬ🥰🥰
2025-08-09 18:45:29
14
𝐈𝐲𝐦𝐞𝐧 :
ወላሂ አየሰማሁት ሳላዉቅ አንባ በእንባ ሆንኩ 🥰🥰
2025-08-25 14:06:09
1
alemgebeyehu1 :
ጅጅ እንቁ ነሽ ስለ ኢትዮጵያ አባይ ቀድማ ያወቀች እድሜ ከጤና ይስጥሽ ……………
2025-08-21 06:02:29
1
Fentahun :
እኔማ የሷን ሙዚቃ ስሰማ እንባየ ነው ሚመጣ ማርያምን,
2025-09-25 07:36:55
0
fifi :
አረ ይሔ እኮ የእውነት ትንቢት ነው
2025-08-09 20:36:34
6
።Aba@27 :
ጂጂ ነገሰቶ🥰🥰🥰
2025-09-11 20:51:08
0
🎀SEBLE🎀(ሰብለወንጌል)፩🌸 :
የኔ ሰው የልቤ ንግሥት 🥰🥰🥰🥰
2025-09-13 10:07:33
0
Ethiopia love :
🥰የኔ ንግስት 🥰🥰🥰🥰
2025-09-16 05:51:33
0
Machalan :
ጂጂ ለህደሴ ግድቡ ምርቃት መገኛት አለበት የኢትዮጵያ ህዝብ ይጋብዘት
2025-08-10 00:13:55
2
sol :
አርቃ ያየች!!!
2025-09-09 16:38:54
1
Tedy :
አንድ ቀን ፈጣሪ ካለ አይሻለው ጂጂዬ የኔ አንበሳ😥😥😥😥😥😥
2025-09-09 22:36:12
1
YimAmamare :
ንግስቷ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2025-09-09 08:14:07
0
ተመስገን ብያለው :
አባይ አባይ አባይ አባይ ወንዛወንዙ ብዙ ነው መዘዙ
2025-08-11 12:47:27
2
To see more videos from user @gigi_shebabawfan2, please go to the Tikwm
homepage.