@melakulegalcosultant: ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) እና የአክሲዮን ማህበር ተመሳሳይነትና ልዩነት! ********* በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC ) እና የአክሲዮን ማህበር ይገኙበታል ። ሁለቱም ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ። ተመሳሳይነታቸዉ • ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣ • የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣ • የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣ • ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣ • ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣ • የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣ • ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑን (የንግድ ህግ 256 እና 501 ) • በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣ • በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ ፣ ልዩነታቸዉ አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ አንቀጽ 495(4) ላይ ተገልጿል። የአክሲዮን ማህበርን ( share company ) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ አንቀጽ 248(3) ላይ ይገኛል። • ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር አንድ በመቶ ማነስ አይችልም (የንግድ ህግ ቁጥር (496) • አክሲዮን ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች መሆን አይችልም (የንግድ ህግ ቁጥር 247) • ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4 (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል (የንግድ ህግ ቁጥር (495(1) • ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ ክፍት የሚደርግ አይደለም አንቀጽ 495(2) ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ (የንግድ ህግ ቁጥር248) • ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transfrable አይደለም። ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ። • አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( plc) ዉስጥ ቦርድ የለም።

መላኩ ፍቃዱ
መላኩ ፍቃዱ
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 13 September 2025 14:56:58 GMT
65710
887
15
389

Music

Download

Comments

ethiopiantiktok39
የሰራሀው ይከተልሃል :
ቀጣይ
2025-09-23 16:36:57
1
user7378344328018
user7378344328018 :
ተመሳሳይነታቸው የንግድ ማህበር መሆናቸው። ልዩነታቸው pLC 2እና ከዚያ በላይ ያሉ ሰዎች ማቋቋም ይችላሉ። ካፒታል 15ሺ በላይ። SC ከ50በላይ ሰዎቾ ማቋቋም ይችላሉ።ባላንድ አባል ምን ሊያሟላ ይችላል???
2025-09-15 16:28:49
1
tigist19973
Tigest Tefera jalleta :
ንብረት ለመሸጥ እንዴት ነው plc ማህበር ሳይበተን
2025-10-20 21:12:06
0
awoke.getaneh
awoke getaneh :
dividend tax ያለው የትኛው ነው
2025-09-15 20:04:12
0
nathan.zdarik
አርዳ :
cooperative share company የሆነ ነገር በለኝ ከነዚህ ጋር አንፃር
2025-09-21 08:05:32
0
user1706775495674
user1706775495674 :
I want to shift my business model from partnership to PLC , what's your Advice.
2025-09-15 15:55:57
0
alphaomega933
alpha-omega :
No ባለ አንድ አባል PLC ተፈቅዷል
2025-09-13 15:37:02
5
gashitygonderew26
@this is gashity :
gin le plc be board memerat gideta nw
2025-09-14 08:36:51
0
janmelkamu1
Melkamu :
🥰🥰🥰🥰
2025-09-13 15:35:40
0
mohammedabdella488
Zafuuwa :
🥰🥰🥰
2025-09-13 15:07:13
1
user4600202082170
Birhanu@Ermiyas :
🥰🥰🥰🥰
2025-09-14 09:10:08
0
2ndalez
Alez :
🥰🥰🥰
2025-09-13 15:03:49
0
yo_na_s202245678667
ሞት እያለ' ክፋት :
stketeri degmo attendace eyasmola even five minute stzegyi arfaji eyasfereme hulu report yemiyadergbsh control kfl endale asbi.
2025-09-28 09:48:43
0
To see more videos from user @melakulegalcosultant, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About