@nar_dy: አሁን ምልሽ ነገር ቢገባሽም ባይገባሽም ስለምወድሽ አላገባሽም የምን ችቦ አይሞላም? የምን አሸወይና? በሰው አፍ መፈተል በሰው አፍ ሽመና የምን ሽማግሌ… የምን ጥሎሽ መጣል? የምወደው ልብሽ ስንት ብር ያወጣል? ስንት ብር? ስንት ወርቅ? ስንት ከብት? ስንት ጨርቅ? ስንት ምን ብሰጥሽ አንቺን ይመዝናል አንቺን ይወክላል ያንቺን ስም ያክላል? ድካም ነው ይቅርብን ጉዳጉድ ማብዛቱ የሳቅሽ አፀድ ነው መኖሬ ግዛቱ ልክ እንደዚህ… ለሌላ እየመሸ ለኔ እንዲነጋ ነጠልሺኝ ቁጭ አልኩኝ ከዚህ ሁሉ መንጋ እድሜ ላንቺ እድሜ ወንጌል አስረሳሺኝ ሰው ቀን የለውም ቅፅበት ነው እያልሺኝ እድሜ ላንቺ እድሜ… ያነበብኩት ሁሉ የቃረምኩት መጥሀፍ ብነካሽ ሄድኩበት እንደ መሬት ምንጣፍ አቤት… አቤት… አቤት… ይሄንን ቢሰሙ የኔታ ምን ይሉ? ያኖርኩትን ኪዳን ድንግልናን ድሼ ጎጆዬ ነሽ አልኩኝ መቅደሴን አፍርሼ ከአንድ አማኝ የማይሆን ነውር እየፈፀምኩ እየተኮነንኩኝ ያን ሁሉ እምነቴን ምን ስትይኝ ካድኩኝ? የት ገባ ፍርሃቴ? የት ገባ እምነቴ? የት ገባ ዕውቀቴ? የት ገባ ልቦና? የት ገባ አይምዕሮ? አስርቱ ትዕዛዝ ለኔ ተቀይሮ "አትግደል" የሚለው "አትሂድብኝ" በሚል "አትስረቅ" የሚለው "አትራቅብኝ" በሚል "ከእኔ ሌላ አምላክ አታምልክ" የሚለው "ከእኔ ሌላ ሴት ጋር አትሂድ" በሚለው ሰርዤ ተክቼ እየተኮነንኩኝ ያን ሁሉ እምነቴን ምን ስትይኝ ካድኩኝ? ልካደው… ልካደው ሁለት ዕምነት የለም ጌታ እንደፈረደው ነይልኝ ገዳም ተዘነጋኝ ባንቺ ስመነኩስ ካዲስ ቤቴ ግቢ ዉሃ ልጣድልሽ ቡታጋዝ ሳለኩስ ልፈር በውርደቴ ዳግም ልንተፋተፍ የማረገው ይጥፋኝ ያልተላጠ ልክተፍ ሳቂ ከት ብለሽ አከራዬ ይስሙ "አገኘ" መባል ነው ሰው የመሆን ስሙ ነይልኝ… በርዶናል እያልን አውቀን ተጠጋግተን ልባችን ይምታብን የምንለው አጥተን ዝምታ ነግሶብን እየተነፈስን ዕቃ ጠፋን እንበል እጅ እየዳሰስን "ምነው ባልመጣሁኝ" የሚያስብል ፍርሃትሽ "ምነው ነይ ባላልኳት" ከአፌ ሊያመልጥልሽ ትንሽ እየቀረኝ ትንሽ እየቀረሽ ጆሮ ጌጥሽ ጋር ሆንኩ ማህተቤ ጋር ደረስሽ ይኸው ልክ እዚህ ጋር… ይኸው ልክ እዚህ ጋ እድሜ ላንቺ ዕድሜ ህልሜን አስቀየርሺኝ "ሰው ዘመን የለውም ቅፅበት ነው" እያልሺኝ አሁን ምልሽ ነገር ቢገባሽም ባይገባሽም ስለምወድሽ አላገባሽም ያገባሁሽ ለታ… ፍቅርን ናፍቆቴን ባለቤት በሚል ስም አጥሬው አጥሬሽ ከአንድ ዕቃ እኩል ቆጥሬው ቆጥሬሽ እንዳንረሳሳ እሺ በይ አለሜ መጋባት እንርሳ ሳታገቢኝ ይቅር ሳላገባሽ ይቅር ሁሌ እንዳንለያይ ሰው ከጁ ያለን ሰው ከመዳብ ነው የሚያይ ስለምድሽ ስትለምጂኝ ሀሳቤ ግድ የለው ያው ሰው አይደለው? መላመድ ይገድላል ጣዕምን ይሸኛል "አለች" እንደማለት ንቀት የት ይገኛል ልጅነቴ ይኑር እደግ ፍርሃቴ በምን ልሙላው ያልኩት ደሞ ይጥበብ ቤቴ እንደ አዲስ ፃፊኝ እንደ አዲስ እናልም ፍቅረኛ እንደሆንን ማርጀት ነው የኔ ህልም የምን ችቦ አይሞላም የምን አሸወይና? በሰው አፍ መፈተል በሰው አፍ ሽመና? የምን ሽማግሌ የምን ጥሎሽ መጣል? የምወደው ልብሽ ስንት ብር ያወጣል? ጉዳጉድ ነው ጉዱ ባይጨፈር ይቅር የቤተ ዘመዱ ግን አሁን ያልኩሽ ሁሉ… ቢገባሽም ባይገባሽም ስለምወድሽ አላገባሽም!!! #Nar_Dy #ኤልያስ_ሽታሁን #ግጥም
🅽︎ᴬᴿᴰʸ ✞
Region: ET
Tuesday 16 September 2025 13:43:04 GMT
Music
Download
Comments
Sisay Chernet :
አቦ ትችላለህ
2025-09-16 14:42:08
128
dava :
ግጥሙን ፅፎልናል
በቃል አብቦታል
የግጥሙ ደራሲ
ፎሎ ላይክ አሶታል።🥰🥰🥰
2025-10-13 09:13:22
2
mulle :
እረ ትለያለህ
2025-10-13 21:21:51
0
አምላክ አለኝ :
ኡፍፍፍ
👏👏👏👏
2025-09-18 04:36:39
1
user3482009904013 :
መስማት ሳይሆን አዳምጥኩት
2025-09-17 15:08:23
39
Birhanuwale Birhanuwale :
ቁልጭ ያለች እውነት ይች ለኔ ናት!!!
2025-09-17 18:43:43
38
user Ritayee :
አቦ ኤላ አንተ ግጠመው በቃ🔥
2025-09-20 18:42:34
7
Mulugeta :
መጨረሻው እንደጠበኩት ባይሆንም...
2025-10-13 17:50:59
0
ፍቅርFree Mesfine :
አቦ ግጥሙ ቦታውን አገኘ ምርጥ ነው 🥰🥰🥰🥰
2025-10-13 09:53:42
0
NINI :
ግጥሙ ጥሩ ነው ግን እንዲህ አይባልም! ምክንያቱም የቤተክርስቲያንና የማህበረሰባችን ህግና ስርአት ይህን አይፈቅድምና ነው::
2025-10-07 10:28:49
4
Tina :
"መላመድ ይገድላል ጣዕምን ይሸኛል
"አለች" እንደማለት ንቀት የት ይገኛል!"🙏
2025-10-10 07:00:34
1
user18794213450347 :
ፍቅር ራሱ እምነት ነው ባክህ ዝም ብለህ አግባት ።ግራ ሳታጋባት።ግራ ሳትጋባ......ዝም ብለህ አግባ !!!!!
2025-10-09 01:46:52
1
Yididya G/tsadik :
ግጥም+ፍልስፍና=👍👍👍
2025-09-23 15:36:44
3
ሚላ ሚላ :
ምነው ቁጭት ውስጥ ከተትከኝ የምር
2025-09-27 01:00:20
0
@madu :
በርዶናል እያልን አውቀን ተጠጋግተን
ልባችን ይምታብን የምንለው አተን
ዝምታ ነግሶብን አየተነፈስን
እቃ ጠፋን እንበል እጅ እየዳሰስን
2025-09-26 16:54:33
7
abi kabera :
yime❤❤
2025-10-11 20:04:25
1
Loza 21 :
አቤት ጥበብ ስጦታ... የግጥም ጥም ቆራጭ🥰🥰🥰
2025-09-23 16:46:36
0
sule car decor :
beka 1gn
2025-09-17 10:52:19
1
user8884622724967 :
ይሄ ሰዉ ያቀናል ወንዴ !!$
2025-09-26 03:17:53
0
Why B/c of you :
የዕውነት ትችላለህ ።እንዳንተ ያሉ ገጣሚያን ያብዛልን
2025-09-20 19:37:10
1
hikma1 :
ርዕስ የለዉም
2025-10-01 16:32:05
0
Berhan Wolde :
እንዲያ ነው ነገሩ?🤔
2025-09-17 18:06:03
1
ID :
ምን ብዬ ላድንቅህ በቃ ትችላለህ።
2025-09-26 13:40:52
0
Kiya :
amesegenalehu aba
2025-09-22 09:22:50
0
tino :
ቃል የለኝም
2025-10-04 23:36:47
0
To see more videos from user @nar_dy, please go to the Tikwm
homepage.