@zelealem.official: ☑️እንቁ ሚስት ለባሏ ፍቅሯንና አክብሮቷን የምታሳይበት ወይም የምትገልፅበት መንገዶች የሚከተሉት ናቸው።አንብባችሁ ተግብሩት ታተርፉበታላችሁ። ① ባሏን በትህትና ፣በሙገሳና በቁልምጫ ትጠራዋለች። ② በቤተሰቡ ውስጥ መሪ እንዲሆን ትፈቅድለታለች። ③ እሱ ከተበሳጨ ወይም ከተናደደ አትከራከረውም። ④ እሱ ሲቆጣ ዝም ብላ በኋላ ይቅርታ ለመጠየቅ ጊዜ ትሰጠዋለች ። ⑤ እሱን ካስከፋችው ወዲያውኑ "ይቅር በለኝ ፍቅሬ" ትለዋለች።ይቅር ሲላትም ደግሞ ታመሰግነዋለች። ⑥ በሌሎች ሰዎች ፊት ስለ እሱ ጥሩ ነገሮችን ትናገራለች። ⑦ ቤተሰቦቹን፣ጓደኞቹን አክብራ ታስከብረዋለች። ⑧ ቤተሰቦቹን እንድፈቅድ፣እንድጦራቸው ፣ለወላጆቹ ስጦታ እንዲገዛ ታበረታታዋለች፤ ይህን ማድረጓ ለሷም ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርግ ያነሳሳዋል። ⑨ በተለይ ገንዘብ ሲያጥረው የሚወደውን ምግብ ሰርታ ታስደንቀዋለች/ሰርፕራይዝ አድርጋ ጉድለቱን ትሞላለታለች። ⑩ አሷ እቤት እያለች ለባሏ ምግብ በሰራተኛ እንድቀርብ አታደርግም ያኔ እንደናት በልቶ እንዳልበላ፣ጠጥቶ እንዳልጠጣ እንደምታስብለት ይረዳል። ⑪ ከውጭ ሲመጣ በእቅፍ ትቀበለዋለች፤ ቦርሳዎቹንና ልብሶቹን እንዲያወልቅ ትረዳዋለች ሸዋር ወስዶ ሲጨርስ ሎሽን እየቀባች በስራ የደከመ ሰውነቱን እያሻሸች ጡንቻውን ታፍታታለታለች። ⑫ አብረው እንድመገቡ፣አብረው እንድፀልዩ፣አብረው ሰለነጋቸው እንድፀልዩ ታመቻቻለች። ⑬ ውጪ ሲሆኑ ፈገግ በማለት ትኩረቷን ከባሏ ጋር በማድረግ አክብሮቷን በማሳየት ፍቅሯን ትገልፅለታለች፣በልጆቻቸው ፊት መልካም አባት እንደሆነ ትነግረዋለች፣ታመሰግነዋለች፣ታከብረዋለች፣ትታዘዘዋለች። ⑭ ሰዎች በተሰበሰቡበት፣ሳቅ ጨዋታ በበዛበት ቦታ እንኳን ብትሆን ትኩረቷ ከባሏ ጋር ታደርጋለች በርቀት እንኳን ቢሆን በአይን ጥቅሻ እየተፈቃቀዱ ፈገግ እንድል ታደርገዋለች። ⑮ ለስራ ሲወጣ በምሳ ዕቃው ወይም በቦርሳው ውስጥ የፍቅር መልዕክት ታስቀምጥለታለች። ⑩ ስራ ሆኖ እንደናፈቃት ለመንገር ብቻ ትደውልለታለች። ⑰ ስልክ ሲያነሳ "እወድሃለሁ" የኔ ጀግና መልካም የስራ ቀን ይሁንልህ ራስህን ጠብቅልኝ ኑሪልኝ ትለዋለች። ⑱ ማታ ሲተኙ ይቺን ሰዐት እንደት ናፍቃው እንደምትውል ትነግረዋለች ጠዋት ላይ ደግሞ ለአንድ አስፈላጊ ነገር ቀስ ብላ ቀስቅሳ ፍቅር እንዲሰማው ታደርገዋለች። ⑲ እሱን ባል በማድረጓ እድለኛ እንደሆነች ትነግረዋለች። ⑳ ያለምንም ምክንያት በመቅለስለስ ታቅፈዋለች፣ፍዝዝ ብላም በስስት በማየት በቁመት ብትበልጠው እንኳን በትህትና ዝቅ ብላ ከፍ እንድል ትፈቅድለታለች። ㉑ በሕይወቷ ፈጣሪ እሱን የመሰለ ባል ስለሰጣት ፈጣሪዋን ታመሰግናለች። ㉒ ሁልጊዜ ስለቤተሰቦቿና ስለ ባሏ፣ስለ ስራው፣ስለ አላማው ስለት እየተሳለች ሳይቀር ትፀልይለታለች። ㉓ ሁልጊዜ ከመተኛታቸው በፊት አብረው እንድፀልዩ ታደርጋለች። እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን 🙏 እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሀኒቴ ነው።

ስለ እናት
ስለ እናት
Open In TikTok:
Region: US
Monday 06 October 2025 17:47:13 GMT
33058
2681
0
917

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @zelealem.official, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About