@manemyedbli: ሮቢ ከመቅፅበት ከመቀመጫው ተነስቶ ከጠረቤዛው አልፎ የዶከተሩን አንገት ይዞ ምን ማለት ነው ተዘጋጁ ማለት እዛ ክፍል ውስጥ ያለችው ሴት እኮ እናቴ ናት ኪሩ አላቆት ይዞት ወጣ ዶክተሩን ይቅርታ ጠይቄ እባክህ ዶክተር እናቴን አድንልኝ እባክህ አልኩት።ዝም አለኝ።ትቼው ወጣው።ሮቢ ስወጣ ንዴት ዝም ብሎ ይለፈልፋል የሆነ ሰዓት ብድግ ብሎ የሆስፒታሉን ግንብ በቦክስ መታው። ሮቢ ብዬ ያዝኩት እባክህ ተረጋጋ እማዬ ምንም አትሆንም ብዬ አረጋግቼ አስቀመጥኩት።የሆነ ሰዓት ብድግ ብሎ ወጣ ሮቢ አልኩት።ዞር ብሎ ንፋስ ልቀበል ነው አለኝ።ኪሩ አጠገቤ መቶ እባክሽ አንቺ እንኳን ተረጋጊ እሺ ለሮቢ ታስፈልጊዋለሽ አለኝ።አይኑን እያየው ስለዚህ ልከተለው ይገባል ብዬ ብድግ አልኩኝ። ቆይ እንጂ አለኝ።አብሬው ልሁን እና ይዤው እመጣለው አልኩት።ሊዮም የት ልሄድ እንደሆነ ጠየቀኝ ለሱም ነግረው ልወጣ ስል ቆይ ብሎ ለብሶት የነበረውን ጃኬት ሰጠኝ።ዞር ብዬ ኪሩን አየውት ተቀበልሽው በሚል አስተያየት እያየኝ ነው ችላ ብዬው ወጣው።ሮቢን ጊቢ ውስጥ በመከራ ፈልጌው አገኘውት። አጠገቡ ሄጄ ቁጭ አልኩ።እሱም ዝም እኔም ዝም።ሮቢ አልኩት ዝም አለኝ ሮቢ እባክህ ተረጋጋ እናታችን ጠንካራ ናት ምንም አትሆንም አልኩት።እንባ እየተናነቀው እኔ እና ታላቅ ወንድሜን ስታሳድገን ያለ አባት ነው ግን አንድም ቀን የሴት ልጅ እንድንባል አድርጋ አታውቅም አንድም ነገር አጉድላብን አታውቅም።እናቴ ማለት እኮ እያላት እንደሌለው አንገቶ ደፍታ የምትኖር ናት እኔም ወንድሜም በልጅነታችን ነው መኪና መንዳት እራሱ የጀመርነው። ውጭ መሄድ እንፈልግ ስለነበረም ለሱም ያልሆነችው የለም እሱንም አደረገችልን ፍላጎታችንን ስታሞላ ኖራለች ፈጣሪ ምን አድርጌው ሊቀጣኝ እንደፈለገ አላውቅም ግን በምንም ተዓምር በእናቴ አይቅጣኝ አለኝ።ዞር ብዬ ስመለከተው ከአይኑ እንባ እየፈሰሰ ነው። ብድግ ብዬ አቀፍኩት።እሱም ደረቴ ላይ ልጥፍ ብሎ ወገቤን አቅፎ ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ።ውስጤ ተሸበረ ፈራው ሮቢ እንዲ ሆኖ አይቼው አላውቅም አሳዘነኝ ከእናቱ እቅፍ መውጣት እንደሚፈራ ልጅ አቅፎ ለብዙ ደቂቃዎች ቆየን።ሮቢ ተረጋጋክ አልኩተ። ለቀቀኝ እና ከፊቱ ላይ የቀረውን እንባ እየጠረ አው ደህና ነኝ አመሰግናለው አለኝ።አጠገቡ ቁጭ ብዬ እጁን አጥብቄ ያዝኩት።ዞር ብሎ ከተመለከተኝ በኃላ በጣም ቀረበኝ ደንግጬ ፍዝዝ ብዬ የሚሆነው ማየት ጀመርኩ።ጠጋ ብሎ ወደ አንገቴ ገባ ቀስ ብሎ ሳመኝ። ከቴሌግራም ቻናላችን የተወሰደ👇👇 #እውነተኛ_ታሪክ #fyp #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ፅሁፍ #ስነፅሁፍ

✍️✍️
✍️✍️
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 07 October 2025 18:40:11 GMT
544
98
0
32

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @manemyedbli, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About