@kifle2129: አንድ በስቃይ የተሞላ ህይወትን የሚመራ ሰው ነበር። ሰውየው ወደ አምላኩ በሚፀልይበት ወቅት "ሁሉም ሰው ደስተኛ ሆኖ ለምን እኔ ብቻ እሰቃያለሁ? ለምን እኔ ብቻ?" ይል ነበር። አንድ ቀን ጥልቅ በሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ለአምላኩ ጸለየ። "አምላኬ የማንኛውም ሰው ስቃይ ብትሰጠኝ ልቀበልህ ዝግጁ ነኝ። እባክህ! እባክህ ጌታዬ የእኔን ግን ውሰድልኝ። ከዚህ በላይ ልሸከመው አልችልም" ሲል ተማጸነ። ጸሎቱን ጨርሶ እንደተኛ ውብ የሆነ ህልም አየ። በህልሙ አምላክ ሰማይ ላይ ተከሰተና እንዲህ ሲል ተናገረ። "ስቃያችሁን ሁሉ ወደ ቤተ መቅደስ አምጡ።" እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ስቃይ የታከተው ስለነበር በተለያዩ ወቅቶች "የማንኛውም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። የእኔን ግን ውሰድልኝ። ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም " ብሎ ይጸልይ ነበር። እንደተባለው ሁሉም ሰው ስቃዩን በቦርሳው አጭቆ ወደ ቤተ መቅደሱ አመራ። ባለታሪኩን ጨምሮ ሁሉም ሰው ጸሎቱ አምላኩ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘ በስፍራው ላይ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ነገሰ። ሁሉም ሰው ከቤተ መቅደሱ ሲደርስ አምላክ እንዲህ ሲል አወጀ። "ቦርሳችሁን ከግድግዳው ስር አስቀምጡ" ሁሉም ሰው ቦርሳውን አስቀምጦ ከጨረሰ በኋላ አምላክ እንዲህ ሲል በድጋሚ አወጀ። "አሁን መምረጥ ትችላላችሁ ማንም ሰው የፈለገውን ቦርሳ መውሰድ ይችላል።" በጣም አስገራሚው ነገር ቀን ከሌት ሲጸልይ የነበረው ሰውዬ ሌላ ሰው ቦርሳውን እንዳያነሳበት እየተጣደፈ ወደ ቦርሳው ሮጠ ሁሉም ሰው አንደ ሰውየው የራሱን ስቃይ ያጨቀበትን ቦርሳ ፍለጋ ተራወጠ። እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ስቃይ ለመሸከም ዝግጁ ነበር። 🤔 ምንድን ነበር የተከሰተው? በህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳቸው የሌላቸውን ችግር ስቃይና መከራ ተመለከቱ። እንደውም እራሳቸው ከያዙት ቦርሳዎች የሚበላልጡ የሌሎች ሰዎች በስቃይ የታጨቁ ትልልቅ ቦርሳዎች እንዳሉ ተገነዘቡ በተጨማሪ ሁሉም ሰው ከራሱ ስቃይና መከራ ጋር ተላምዷል። የራሱን ስቃይ ማባበል እና መቻል ይችላል። የሌላውን የመከራ ቦርሳ ቢወስድ ግን ከቦርሳው ውስጥ ያለው አዲስ አይነት መከራ ምን አይነት እንደሆነ አያውቅም። ምናልባት የባሰም ሊሆን ይችላል። አላሚው ሰው ከእንቅልፉ ሲነቃ በድጋሚ ጸለየ። "አምላኬ ስላሳየኸኝ ህልም አመሰግናለሁ። ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነቱን ጥያቄ ደግሜ አልጠይቅም። የሰጠኸኝን ነገር ሁሉ አመሰግናለሁ። አለ ይባላል።
kifleዘማርያም
Region: ET
Friday 10 October 2025 12:07:23 GMT
Music
Download
Comments
Dereje :
አስተማሪ ፁሑፍ ነው አመሰግናለሁ ።
2025-10-11 04:30:19
8
Rakeb :
👏👏👏👏👏👏👏👏ቃልም የለኝም ለመግለጽ እግዚአብሔር በረከተ ፀጋውን ያድልህ ወንድሜ👏👏👏👏👏👏
2025-10-13 15:51:08
1
Almi C :
እዉነት እስከመጨረሻዉ አንብቤዉ ተምሬበታለሁ የባሠ አለና ሀገርክን አትልቀቅ ነዉ ነገሩ 🥰🥰🥰🥰
2025-10-17 17:42:24
0
እመጓ ኡራኤል መንዝሀ :
አሜን ቃለሕይወት ያሠማልን
2025-10-17 11:44:08
1
Solomon Tesfaye :
ገራሚነው
2025-10-16 17:55:57
1
ድጋፌ ነኝ የኤርምያስ አባት :
ቃለህይዎት ያሰማልኝ
2025-10-15 12:26:29
1
abnet abnet :
በጣም አስተማሪ ነዉ አናመሰግናለን
2025-10-13 17:58:42
1
ፍቅር ይቅደም :
ቃለወት ያሰማልን እግዛብሂር ይባርክህ
2025-10-16 15:51:45
1
𝐒𝐨𝐧 𝐨𝐟 𝐬𝐭 ገብርኤል :
እግዚአብሔር ይመስገን
2025-10-15 10:52:48
2
Bright dream☀️/ብሩህ ህልም ☀️ :
ተባረክ ወንድሜ
2025-10-10 12:41:24
2
beza :
ቃለህይወት ያሰማልን
2025-10-16 11:56:02
1
fkr yashenfal :
ቃለሂወት ያሰማልን
2025-10-16 10:15:08
1
ታገስ ያልፋል :
ኦርቶዶክስ ባልሆን ይቆጨኝ ነበር
ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
2025-10-11 05:34:11
3
ስመር እግዚኦ ከመ ታድኅነኒ :
የኔ የማንንም ፖርሳ አልፈልግም የኔዉ ይበቃኛል 😌😌😌
2025-10-13 12:37:26
1
fasil gonderew :
በጣም አስተማሪ ነው እኛ ግን አንረዳውም ሁሉም ሚሆነው በምክንያት ነው
2025-10-13 11:47:13
1
Haymanot :
ፈጣሪ ይባርክህ 🙏
2025-10-11 19:44:32
1
ትንሿ ጎደሬ :
ፈጣሪይባርክህ
2025-10-10 18:20:04
3
Adenew Bogale :
የሚገርም አስተማሪ ነው🙏🙏🙏🙏
2025-10-14 10:41:26
1
burte💞💞 wonibera :
betam tiru timhirt enameseginalen🙏🙏🙏
2025-10-10 15:56:28
2
Melkie Belay :
ወይኔ በድንግል ማርያም እዴት እሚገርም ትምህርት ነው በማርያም ሌላም ካለህ ጨምርልን ወንድሜ ።🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2025-10-13 05:15:36
1
Hilina Tsegaye :
ቃለህይወት ያሰማል
2025-10-16 01:47:58
1
ቢመርህም ትውጠዋለህ :
እኔም ፍጠሪን ደጋግሜ የማያሰፍልገኝን ጠይቄው ሰላልሰጠኝ ክብር ለሱ
2025-10-12 10:19:17
1
sltan gebre :
ባለንበት እንፅና እግዚአብሔር ያሰበልን አለና አምላኬ ሆይ ተመስገን 🙏🙏🙏
2025-10-11 04:54:13
1
alemayehuman0 :
እንደዝ ነው የተሳጠን መልከሙን ነገር ወደ ጎን በመተው ለትንሹን ችግራችን እግዛአቤሔርን እነመራለን እሱ እቅር እበለን
2025-10-12 08:18:33
1
Shewa :
አስተማሪ ጽሑፍ ነው
2025-10-11 17:00:38
1
To see more videos from user @kifle2129, please go to the Tikwm
homepage.