@zelealem.official: ☑️እውነት ስላለህ እና ታማኝ ስለሆንክ ኩራት አይሰማህ።አንተ ትክክል ሆንክ ማለት ሰዎች ሁሉ ተሳስተዋል ማለት አይደለም።አንዳንደየ ደረቅ እውነት ከስህተት የከፋ ጉዳት ያመጣል።በሰዎች ስህተት የምትቀልድ በራስ እውነት የምትመፃደቅ እንዳትሆን እውነትን በፍቅር ያዝ ፣ለህሌናህ ኑር፣ወከባ እና በሰው መከበብህ ከህሊና ድህነት አያድንህም። ☑️ሃብት ንብረትህ አስተሳሰብህን አይቀርፅም፤ ወዳጆችህ ውስጣዊ ሰላም አይሰጡህም። በእውነት ካልተመራህ፣ በስረዓት ማሰብ ካልቻልክ፣ ጥንያቄን ካልመረጥክ፣ ምላስህን ካልገራህ፣ ተግባርህን ካልቆጠብክ ጉዞህን እንጂ መውደቂያህን አታስተውልም፤ ጭብጨባውን እንጂ ስህተትህን አትረዳም፤ ድጋፍህ እንጂ ጥፋትህ አይገባህም። ☑️አዕምሮህን ክፍት ማድረግህ ሚዛናዊ ማንነት እንዲኖርህ ያደርግሃል። መስማት የሚፈልግ ሰው ሁሉ ይሰማህ ይሆናል፤ የሚወድህም ይከተልህ ይሆናል፤ የሚያምንብህም እንዲሁ ሊደግፍህ ይችላል። ነገር ግን ማንም ሰው እስከመጨረሻው አብሮህ እንደማይቆይ እወቅ። ጥልቁ ማንነትህ እንጂ በራስህ እወነት ከሌሎች ተቃርኖ መቆም ነፃ አያወጣህም። ☑️ህሌና ይፈርዳል እውነት በፍቅር ፣በሚዛናዊነት ከትህትና ጋር ያዝ።እውነትን በልብህ ይዘህ የተሳሳቱ ሰዎችን ስህተት ለማጉላት ሳይሆን ከስህተታቸው እንድወጡበት ምርጉዝ ሁነህ መስዋዕት ሁን። በሰዎች ደካማ ጎን ተጠቅመው ሲበለፅጉ ተመልክተህ ይሆናል፣ ባላቸው ትንሽ እውነት ተጠቅመው ከከፍታው ሲደርሱ አስተውለህ ይሆናል። ነገር ግን አንድ ነገር በቅጡ ተረዳ በሰው ደካማ ጎን የበለፀገ ሰው ከራሱ ጋር ሰላም አይኖረውም።ትንሽ እውነት ይዞ በሰው ደካማ ጎን ለከፍታው የበቃ ሰው ትክክለኛ ስሜቱን አዳምጦ አያውቅም፤ እረፍትን ከውስጡ አጣጥሞ አያውቅም። ☑️እውነት ትህትና ከለለበት ተቀባይነት የለውምና ጥላቻን ያመጣል።ትህትና ከለለበት እውነት ስህተት ውብ ነው።በህይወት ስትኖር ሰው ነህና አውቀህ ታጠፋለህ፣ ሳታውቅ ታጠፋለህ። ቁም ነገሩ የጥፋትህ ብዛት ወይም አደገኝነት አይደለም።ዋናው ነገር ከጥፋትህ ለመማር ዝግጁ መሆንህና ጥፋትህን ላለመድገም ቁርጠኛ መሆንህ ነው። ☑️ህሊና ይፈርዳል፣ የራሱን ብይንም ይሰጣል።ስለተጨበጨበልህ እውነት ተናግረሃል ማለት አይደለም፤ ተቃውሞ ስለበዛብህም ውሸት ተናግረሃል ማለት አይደለም። ለሁሉም ሰው የተሰጠው ኀህሊና የመንገድህ መሪ፣ የንግግርህ ቆንጣጭ፣ የተግባርህ አራሚ ነው። "የራስህን እውነትን ይዘህ ለመፍረድ አትቸኩል፤ ለንግግር አትጣደፍ፤ ያንተ እውነት የሌሎችን ውሸት እንድያጋልጥ አትፈልግ።እውነት ምንጊዜም እውነት ነው ንፅፅር አያስፈልገውም።እውነታውን በጥላቻህ አትሸፍን፤ በእውቅናህ ሰላምን አትግፋ፤ በተሰሚነትህ ክፍተትን አታስፋ።አንተ እውነትነት ስላለህ ብቻ የዋሸን ሰው አትናቅ፣አታዋርድ፣አሳልፈህ አትስጥ። እውነትን ምረጥ ውሸት የአብሮነት ምክንያት ሆኖ አያውቅም፤ ተንኮል ፍቅርን አንግሶ አያውቅም፤ ጥላቻም የሰላምን በር ከፍቶ አያውቅም። ☑️እውነትን ለበጎ ተጠቀምበት፣ያንተ ትክክል መሆን በአንተ እና በተሳሳተው ሰው መሀል ያለውን ልዩነት ካላጠበበ ልክ አይደለም።እውነትን ይዘህ ከምትፈርደው ይልቅ ዋሽቶ ያስታረቀው ይበልጥሃል።በእውነትህ የሌሎችን ስህተትን አታጉላ።ለመፍረድ እና ለማሳፈር የምትጥር ከሆንክ በሰዎች መካከል ፀብን በመዝራት ሰላምን ያደፈርሳል ።እውነት ሰላምን መፍጠር ካልቻለ ልክ አይደለም። ለሰላም ግድ ይኑርህ፣ለመከባበርም ቅድሚያ ስጥ። እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን🙏 እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኒቴ ነው።

ስለ እናት
ስለ እናት
Open In TikTok:
Region: US
Tuesday 14 October 2025 21:59:30 GMT
11660
585
19
86

Music

Download

Comments

seni_mm
Sun-design 21 :
Betam enamesegnalen❤️❤️❤
2025-10-15 14:04:56
0
abuye.abu0
Abuye Abu :
አሜን🙏
2025-10-17 18:10:52
0
myorthodox254
የዝምታ ቅኔ!!! :
በትክክል 🙏
2025-10-21 11:19:57
0
user577823860
ZED :
The best🤞❤👌🏼
2025-10-17 16:48:29
0
tsige.alemayehu7
TSige@ Alemayehu :
እውነት ነው 🥰🥰🙏🙏🙏
2025-10-15 05:03:35
0
user6005721863591
ነገ የኛ ነው!!! :
የህይዎት ትግል
2025-10-19 09:07:37
0
yohannesgizachew3
yohannesgizachew3 :
best
2025-10-15 13:24:30
0
user95086333956212
ጎዶልያስ :
አሜን
2025-10-17 21:49:10
0
maza4050
💞 Mazii 💞 (ሸገር ) :
በትክክል👌❤️💯
2025-10-16 13:05:55
0
susu81617
ሁሉም ያልፍል :
🥰🥰🥰🥰🥰
2025-10-19 05:24:37
1
ilov.you.my.mom
ilov you my mom🌏🌏🌏🌏 :
💝💝💝♥♥♥♥♥♥
2025-10-22 16:41:41
0
user93327576295726
121619 :
🥰🥰🥰🥰
2025-10-20 19:03:16
0
user93327576295726
121619 :
🥰
2025-10-20 19:03:06
0
hiwetgebre65
ሂዊ ጓል ተዋህዶ 🤲💒❤️ :
🥰🥰🥰🙏🙏🙏
2025-10-15 12:27:16
0
kilil198
betel🌟 :
🥰🥰🙏
2025-10-14 23:37:45
0
titanic3609
Titanic :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰❤️❤️❤
2025-10-14 22:21:44
0
jeryy334
Ⓙⓔⓡⓨ ⓳☦️🤱 :
🥰🥰🥰🥺🥺🥺🥺🤲🤲🤲
2025-10-14 22:09:04
0
hiwet894
𝙡𝙞𝙟🦋 𝙝𝙞𝙬𝙚𝙩💔✍️ :
🙏🙏🙏
2025-10-14 22:07:23
0
user9635288180162
➋➐𝑏𝑎𝑙𝑒𝑚𝑎ℎ𝑡𝑒𝑏𝑢𝑤𝑎✝️ :
😢😢😢🥺😢😢😢⚰️🤲🤲
2025-10-14 22:07:20
0
To see more videos from user @zelealem.official, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About