@mahfuzm11: በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ መንገዱ የጨለመበት፣ በተስፋ መቁረጥ ማዕበል የሚናወጥ ልብ ሁሉ ወደዚህች የቁርኣን አንቀጽ ይምጣ፤ የአላህ ወዳጅ ነብዩላህ አዩብ በዱዓ ወደ ጌታቸው የተማጸኑባትን ቃል ያስተውል፡- "وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ" «አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡» የአዩብ ታሪክ የተጨነቁትን የሚያረጋጋ፣ ያዘኑትን የሚያጽናና እና በፈተና ውስጥ ላሉት ሁሉ የመውጫውን በር የሚጠቁም ነው። ነብዩላህ አዩብ በሀብት፣ በልጆችና በጤና የተትረፈረፈ ጸጋን የተለገሱ ነበሩ። አላህ በዋለላቸው ውለታ ሁሉ አመስጋኝና ታዛዥ ባሪያ ነበሩ። ነገር ግን የአላህ ውሳኔ ሆነና ታላቅ ፈተና ወረደባቸው። ያ ሁሉ ሃብታቸው አለቀ፣ ልጆቻቸው በሙሉ ሞቱ፣ ሰውነታቸውም በከባድ በሽታ ተያዘ። ከባድ ህመም ሰውነታቸውን እስኪበላው ድረስ ደረሰ፤ ከልባቸውና ከምላሳቸው በስተቀር ጤናማ የሰውነት ክፍል አልነበራቸውም። በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ግን ከአንደበታቸው የምስጋና ቃል አልተለየም። ለዓመታት በዘለቀው በዚህ መከራ ውስጥ ቅርብ ያላቸው ሁሉ ራቋቸው፣ ማህበረሰቡም አግልሏቸው ነበር።ከታማኝ ሚስታቸው በስተቀር ማንም ከጎናቸው አልነበረም። እሷም ቢሆን የባሏን ህመም ለማስታገስና ቀለብ ለማቅረብ በሰው ቤት ሰርታ ልታኖራቸው ግድ ሆነባት። በዚህ ሁሉ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ አዩብ ቅንጣት ታክል አላማረሩም፤ "ለምን እኔ?" ብለውም አልጠየቁም። ይልቁንም፣ የትዕግስትን ጫፍ በመያዝ አላህን ማውሳታቸውን ቀጠሉ። ህመሙ ሲጠናባቸውና ድካሙ ሲበዛባቸው ግን ወደ አዛኙ ጌታቸው እጃቸውን ዘረጉ። ዱዓቸው ግን ስሞታ አልነበረም፤ ይልቁንም የአላህን ታላቅነትና እዝነት እውቅና መስጠት ነበር። «ጌታዬ ሆይ! እኔ መከራ አገኘኝ» አሉ፤ የራሳቸውን ደካማነትና ችግር ተናዘዙ። ቀጠል አድርገውም «አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ»በማለት የጌታቸውን የችሮታ ባህሪ አወደሱ። አላህም ይህንን የተማረከ ልመናቸውን ተቀበለ። እንዲህም አላቸው፡- "فَاسْتَجَبْنَا لَهُ فَكَشَفْنَا مَا بِهِ مِن ضُرٍّ ۖ وَآتَيْنَاهُ أَهْلَهُ وَمِثْلَهُم مَّعَهُمْ رَحْمَةً مِّنْ عِندِنَا وَذِكْرَىٰ لِلْعَابِدِينَ" «ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከመከራም በእርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ አስወገድንለት፡፡ ቤተሰቦቹንም ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ከእኛ ዘንድ ችሮታና ለተገዢዎችም መገሰጫ ይሆን ዘንድ ሰጠነው፡፡» ውድ የተጨነቅክ ወንድሜ/እህቴ ሆይ! የአዩብ ታሪክ ላንተና ላንቺ ትልቅ መጽናኛና ትምህርት ነው። የህይወት ፈተና ሲበዛብህ፣ ጭንቀት ሲደራረብብህ፣ ተስፋህ ሲሟጠጥ የአዩብን ትዕግስት አስታውስ። መከራ የአላህ ቁጣ ምልክት ሳይሆን የፈተናና የደረጃ ከፍታ መሆኑን ተረዳ። አብሽሩ!
Mahfuz Muhdin
Region: ET
Friday 17 October 2025 15:59:51 GMT
Music
Download
Comments
Ĥâmžįŷã ĥämü🌸 :
أني مسني الضر وأنت أرحم الرحمين ☺
2025-10-17 16:30:36
20
Mehamed Sebru :
yasfelgy nber bro 🙏 allah ysxely 🥺🥺
2025-10-17 20:31:36
6
إسلام عليكم ورحمة الله وبركات :
أي والله سبحان الله
2025-11-20 18:30:59
0
ፊዳ ይሁንሎት ሩሄም እናቴም አባቴም 🕋🕋🕋 :
@ፊዳ ይሁንሎት ሩሄም እናቴም አባቴም 🕋🕋🕋::ፍትህ ለጋዛ ፍትህ ለፍልስጤም ❤❤❤🇰🇼🇰🇼🇰🇼🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴
2025-10-17 20:10:45
0
DIAR :
በጣም ነው የምወደው የነብዩላህ አዩብን ታሪክ ከዛ የተነሳ i love ayub የሚለውን ስም 🥰
2025-10-17 18:36:40
4
reje'a🌿 :
jezake allah☺
2025-10-17 19:50:37
3
yusri 🥰 :
አላሁም ኢብትለይተኒ ፈጀአልኒ አብደን ሰብር 🤲😔
2025-10-18 13:54:18
5
🎀anel Ⓜ️uslim الحمد الله 🦋 :
ጄዛአኩሙላ ኸይረን 🥰🥰
2025-10-18 11:44:43
6
Ahmed jemal :
Ya allah!Ya rabb!
2025-10-28 19:25:37
1
S^U^L^E^Y^M :
jeza kelah wendmachin brtaln...❤❤
2025-10-17 18:48:15
2
Yakut Amede :
:أني مسني الضر وأنت أرحم الرحمين ☺
2025-10-18 18:42:09
3
qalbi fil medina :
ya selam 🥰🥰😄😄
2025-10-17 18:08:11
2
haha :
wlh balefo btm keftogn selesachew saseb ergete nbr yalkut🥰🥰
2025-10-24 06:32:45
0
Seada Beshir :
allah yabeshrh
2025-10-18 08:21:22
0
fulan garment mechanic :
አልሐምዱሊላህ ዓላ ኒዕመተል ኢስላም🥰🥰🥰🥰🥰
2025-10-18 10:49:03
2
MEDI :
allah yabashirh 🥰
2025-10-17 19:37:07
0
Magfira :
صح ياخ
2025-10-19 18:51:31
0
mirhan589 :
Alhamdulilah
2025-10-20 12:39:52
0
تبسم :
እኔ መከራ አገኘኝ
2025-10-17 16:05:12
0
Ifrhaa Cofii🤎☕🥀🤴🏾 :
Ahaa🥺🥺🥺🥺
2025-10-17 17:54:23
0
فرحا💍🧡 :
فاستجبناله🥰🥺اللهم استجب 🤲
2025-10-22 03:42:05
0
nurehasne :
ya allah
2025-10-17 23:32:06
0
Fatuma Umi :
አሜን
2025-10-23 17:12:59
0
Anuu💫 :
يألله🥺
2025-11-06 17:58:17
1
ʜᴀɴɪꜱᴜ🧕🌺 :
alhamdulillah
2025-10-17 17:37:35
0
To see more videos from user @mahfuzm11, please go to the Tikwm
homepage.