@mame7877: ፊቷን አይቼ አንቺ ግን ደህና ነሽ ? ስል በመፍራት ጠየቅኋት። «... ምንም እንኳን ህመም እየተሰማኝ ቢሆንም ለስሜቴ በቂ ትኩረት አልሰጠሁም። በቀላሉ ከመደሰት ይልቅ ሀዘን፣ ጭንቀትና ጫና የበዛበትን ስሜት እየታገስኩ መኖር ከጀመርኩ ከወር በላይ ሆኖኛል። አንዳንድ ሰዎች ውጥረት ውስጥ እንዳለሁ ቢመለከቱም ብዙዎች ግን ተረጋግቼ በጥሩ ሁኔታ ስራየን እየሰራሁ እንደሆነ ያስባሉ። ላለፉት ሳምንታት ለማንም ምንም አይነት ስሜት አላሳየሁም። ከውስጤ የሆነ ነገር እንደጠፋ ማንም አላስተዋለም። አዕምሮየ ሙሉ በሙሉ ምስቅልቅል ውስጥ ስለሆነ የማስበው ሁሉ እየጠፋ እንደሆነ የሚመስለኝ ጊዜ አለ። ሁሉም የሰውነት ክፍሌን የሚያመኝ የሚመስለኝ አንዳንድ ቀን አለ። እራሴን ከማስታመምና ከማበረታታት ይልቅ ሌሎችን ለማስቀደምና እነሱን ለማፅናናት እሞክራለሁ። ብቸኝነት የሚሰማኝ ጊዜ አለ ነገር ግን ስሜቴን ችላ ብየ ስራየን እሰራለሁ። ጭንቅላቴ ውስጥ ምንም አይነት ችግር እንደሌለብኝ አስመስላለሁ። ለምን እንደማደርገው አላውቅም ግን ዝም ብዬ እራሴን ከአቅሜ በላይ እገፋለሁ። የድባቴና የፍርሃት ስሜት በተሰማኝ ቁጥር ዝም ብዬ ችላ እለውና ስራዬን እቀጥላለሁ። ደህና እንዳልሆንኩ እየተሰማኝ ውስጤን ችላ እላለሁ። አሁን አሁን ግን ከራሴ ጋር ከባድ ጦርነት ገጥሜያለሁ። ላለፉት ሳምንታት ለስሜቴ ትኩረት ሳልሰጥ ሁሉንም ነገር ማስተናገድ እንደምችል አስብ ስለነበር ችላ ያልኳቸው ከባድ ስሜቶች ሁሉ አሁን ሙሉ በሙሉ እንደጎዱኝ ይሰማኛል። አሁን አሁን የደበቅሁትን ስሜቴን ብቻየን ለመሸከም በጣም ከባድ እንደሆነ ይሰማኛል። በጣም የተጎጂነት ስሜት ይሰማኛል። አሁን አሁን የምር የሀዘን ስሜት ይሰማኛል። አዎ ዛሬ ደህና እንዳልሆንኩ ለራሴ አምኛለሁ !!» . . . ይሄን ሁሉ ስታወራልኝ በዕንባ ጤዛ የረጠቡ ዐይኗቿን ማየት ከብዶኝ ነበር። ብቻ ግን የሚሰማትን አውርታልኝ ስተጨርስ እፎይ ማለቷን አስታውሳለሁ።
mame official peg 📄
Region: US
Monday 03 November 2025 18:51:19 GMT
Music
Download
Comments
🙋መንገደኛዋ❤🔐 :
🥺🥺በዝምታ ውስጥ እንዳለ ህመም ምን ከባድ ነገር አለና
2025-11-03 20:32:39
27
አፀደ 🥀❤️ :
ሰደሰትም ስከፋኝም ዝም ነው ሌላ አማራጭ የለም።😔🤲
2025-11-04 12:41:16
4
ቀበጥ ነኛ 🫰🩵 :
እግዚአብሔር ይመስገን 🙏
2025-11-04 19:48:08
1
𝖘𝖊𝖒𝖎𝖗𝖆🖤👑✨ :
alilhamdulila dena naing🫡🤍✨
2025-11-05 03:52:01
1
tsega yegeta liji 🙏❤️ :
እኔ ያለውበት ሁኔታ 😭😭
2025-11-04 14:45:13
5
●ኑኒ ነኝ የኮቻዋ●የሤቶች●ፕሬዝዳት🤞🦋 :
አልሃምዱሊላህ የባሥ አለዉ 🤕
2025-11-04 20:17:05
1
meri💃 :
አይደለሁም🥺🥺🥺🥺🥺
2025-11-04 17:10:25
1
ሀብታም ያባቷ ልጅ :
ዛሬ አለቀስኩ በፅሁፍህ ምክንየመቱም እኔን ያናገርከኝ መስሎኝ ይሄ ነው አሁን ያለሁበት ስሜት🥺🥺🥺🥺💔
2025-11-04 08:35:26
3
Hawii tesegaya🦋🦋 :
ከነገርኩህ በዋላ ቀሎኛል ግን አሁንም ደና አይደለሁም 🥺😔
2025-11-04 16:32:18
1
ህመምተኛዉ ልቤ💔 :
ደህና አይደለሁም ግን በዝምታ የተሸፈነ በደህና ነኝ የተሸፈነ ህመም
2025-11-04 15:43:49
1
Madeena Kader :
እህህህህ ስል ይቀለኛል።😳
2025-11-04 18:57:18
3
〰️h̤e̤r̤ṳ Q̤ṳe̤e̤n̤ 〰️6️⃣💠 :
ደህና ነኝ ብዬ ልለፈው እንጂ ደህናማ አይደለሁም ድክም ብሎኛል 🥺
2025-11-04 18:40:20
2
sol.2335 :
koy gen lemen yehon yehenen yahal emewedat
2025-11-04 15:47:28
1
ላኮነኝ አታልፋኝ😴 :
ደከመኝ. ግን. ደህናነኝ😔
2025-11-04 09:18:07
3
የራስዋ ጨረቃ❤ :
ያለሁበት ሳምንት😥
2025-11-03 23:36:55
3
𝐅ikir..🇨🇦 :
አሞኛል ህመሜን ግን በዝምታ እያስታገስኩኝ ነው ኡፍፍፍፍ
2025-11-04 12:00:33
1
Ãsñì Hãbéshãwét 💚💛❤ :
ደህና ነኝ 🥺
2025-11-04 17:38:17
1
ኪያ የናፍያድ ልጅ :
ምንም ደህና አይደለሁም እዉነት ለመናገነር
2025-11-04 14:54:50
1
Never look back :
ያልታደልን ትውልድ ቁሰለኛ😭
የተከዳን በባዱ እረኛ ፣
እሰከመቼ እቁዘም እንተኛ?
2025-11-04 14:14:43
1
lidu-life=🧸❤️ :
ene enja🥹
2025-11-04 10:43:17
1
love you. mom :
ayizoshi🥰🥰🥰🥰🥰🥰😢
2025-11-04 08:42:13
1
life is short😔 :
አሁን ያለሁበት ሁኔታ 😭😭😭😭
2025-11-03 20:03:21
1
ሱናማይት :
ልክ እኔ እያወራሁ እየሰማኽኝ እስኪመስለኝ ተመስጬ ሳነብ አለቀብኝ😔
2025-11-04 18:31:03
1
የሀኒ እናት ❤️hanicho❤️ :
የኔ ስሜት ነው ግን ደህና ለመሆን በግድ እየሞከርኩ ነው🥺
2025-11-04 11:50:07
1
rahma :
ለካ ሁሉም በሽተኛ ነዉ መቸ ይሆንጤነኛ የምንሆነዉ
2025-11-04 16:31:23
1
To see more videos from user @mame7877, please go to the Tikwm
homepage.