@yilupanda: ፈረሰኛዉ ጊዮርጊስ        የካቲት 1996 ዓ.ም ኸይርም በረካ ሁን ሸርም በረካ ሁን ሳትዉል ሳታድር ታፈራለህ አሁን           (የወሎ ስነ-ቃል) የጎደለኝን ሳላውቀው የጠፋኝን ሳልረዳ እንደትለኮስኩ … እንደተጋፈጥኩ እንደተታኮስኩ … እንደተፋጠጥኩ አለሁ ! ሳንጃ ባፈሙዝ ተቀላቅዬ በቁሜ እንደተረዳ የት አዉቅና ደፈጣ እንደ ቅምቡርስ በደረት እየተሳቡ ማነጣጠር የከርሞ ሰዉ እስከሚለኝ ጠፉ ጥፉ እስኪመነጠር አድሮ ለመሰልሰል ለለቱ ከመመሳሰል አጉል ቆርጦ ከመቀጠል ይለይልኝ ልንገብገብ መርሀኔን በጥሼ ጢሼ ጢሼ ልንደድና ልቃጠል በቅጠል መቼም ቢሆን ያልገራልኝ ምን ግዜም ያልተብራራልኝ ይሄ ሚስጥር የሚሉት ሰጥር ነዉ የምንግዴን ሰባት ዙር ሽምጥ በቀንጠፋ ያጠርነዉ ምንም ያልጠረጠርነዉ በሀሌዮ  ብቻ እያነጋገርነዉ በህልም አለም እያሰገርነዉ ደፍረን ያልተሻገርነዉ አድበስብሰን አዉተፍትፈን ስንድንሞነሞን ያዉገረገርነዉ ኤሎሄ ! ኢላሄ ! ምሉዕ በኩልሄ የማይሰፈር ስለካ ከማይደፈር ስፎካከር እሰጥ አገባ ስጎሰጥ ጉንጭ አልፋ ስከራከር እየመሸ እየነጋብኝ ዓይኔ እያዬ ዘጋብኝ! ጌታ ሆይ ኩኬን አዉጣልኝ ከዕዝኔ ሰምቼ ልብ አለማለቴ ነዉ እየዛዘንኩ መባዘኔ የሰጠኸኝን እንዳስተዉል ተለብልቦ ታርቆ መቅናት ተስኖኝ እንደቆሪ ዉሀ እንዳልዋልል መሀል ቤት እንዳላወላዉል የዓይነ ህሊናዬን ጉድፍ አንስተህ የነፍሴን መታዘቢያ ወልዉል በዉል ! የጤናዬን … የጤናዬን ነገር አደራ የዘፍጥረቱንም ጭምር ችዬ አልቆምም ብቻዬን … ያለፅንፈ ዓለሙ ድምር! ችዬ አልችልም ብቻዬን አልፀናም ባንድ ራሴ ድሀ አደግ ምን ቢተባ አይደምቅም እንደደራሴ ጌታ ሆይ በእምርታህ በይቅርታህ ማርከኝ በእዝነትህ እንደ ቸርነትህ ባርከኝ እንኳን የጓረስኩት የቆረስኩት እያነቀኝ አቁማዳ ሲፈታ እንደተያዘ ቀጣፊ ስርቅታዉ እያሳቀቀኝ እንዳልበላ እንዳልዘራ በቅሌት እየሰለቀ አደቀቀኝ ኤሎሄ ! ኢላሄ ! ምሉዕ በኩልሄ እለቴ ሞቴን አታስረሳኝ ወንፊት እንጂ ፊት አነትንሳኝ እንደ ፊኛ ተወጥሬ በሽንገላ ታጥሬ ያላቀበጠጠኝን የሰዉ ላላማ እምብስ ቆስቁሼ ሳራግብ ቁልጭት እንደ ዙር ዝናር ታጥቄ ቁጭት እንደ ወጨፎ ከማነግብ አታደናክረኝ ስቼ ተርሽቼ ተሰንክዬ እንዳልረግብ አፋፋኝ በእቅፍህ ሙቀት ሰዉረኝ ከሰንበት ስደት አዉጣኝ ከነይ ነይ በቀት ያዝልኝ አዛን በጠበሉ እዛዉ ከነጅናዛዉ እዛዉ በርቀት ምንም ይሁን ምንም ይሁን  ምንም ምንም ፍቅሩን በስቅለቱ ያልገለፀ እንኳን ለዘለአለም ለለት ለቅፅበት አይታመንሞ ቃለ ህይወትን አሰማኝ በመላእክትህ ዝማሬ አጅበህ ፅርሓ አርያምን አሳየኝ በህያዋን ክብር በቱጉሃን ስብሐት ተከበህ! አንድዬ.... ምላሴን ኩን አድርገህ አጣፍጥልኝ ሁለመናዬን ለምለም ነው ብዬ ከማንም ጋር ስዳይ ውዬ እንደአባያ ሣር እንዳልነጭ ምሬሃለሁ በለኝ በድንግል የዘለዓለም ማየ ህይወት በልቤ ዉስጥ እንዲመነጭ! መቸም ቢሆን ልጅ ያለአባቱ ቁምጣው እንጂ መች ጉልበቱ ስሜቱ እንጂ መች ደምግባቱ ኤሎሄ ! ኢላሄ ! ምሉዕ በኩልሄ ቤት ለእንግዳ በለኝ በማምላክ ቤት እምቦሳ እንድል በምሥራቅ በር ከጥሬ ዱለት አላለፈም የኔ ያልኩት ምላስ ሰምበር! በብርሀን ሸኘኝ ወደ ፂዮን አሳየኝ የእምዬን ፀዳል ከእሷ የምህረት ስርየት እንደ ከነአን ሸለቆ ማርና ወተት ይቀዳል ጥም ቆልፎኛል በጠና ለቆብኛል የዕምነት ራብ ቀላቅለኝ ከብሉይ ምንጭህ አቅርበኝ ወዳንተ ምኩራብ … ጠብቀኝ ከማላውቀው አውጣኝ ከፍዳ ናዳ … ነፍሴን እንዳይነጥቀኝ መልዓከ ሞት ሳልታጠብ ሳልታጠን ዘንግቼ ሳልሰናዳ ንጋት ስለዉ ንዴት ትጋት ስለዉ ስደት ሰለቸኝ አጎበጠኝ የስጋ ሽክሙ ምራኝ በምልክትህ አፅድቀኝ በአትክልትህ አስረዳኝ በ "ሀ" ግዕዝ "ሁ" ካዕብ በአቡጊዳ ሄውዞ … በመልዕክተ ዮሐንስ … ሐዋርያዉ ወልደዘብዴዎስ … ንዜንወክሙ ገላግለኝ ከኑሮ ሥጋት ሰዉረኝ ከሸክላ መላ … አንተ እንጂ ምን አለኝ ሌላ … ከዚህ በኃላ! ምዕራፍ ሁለት ፪ የንጋት ፈጅር ጎህ መቅደድ በኔ መላ እየመሰለኝ ስንቱን ዘመን አጥመነመነኝ ስንት ግዜ አብሰለሰለኝ ህም ! ዕድሜ ሰጥቶ … እያገላበጠ ጠብሶ ከእሳት አዉጥቶ አበሰለኝ ! ስሉስ ባዛዉር በቃህ ሲለኝ ነው መሰለኝ ሀሌሉያ ! ክብር ለሱ አዎ በስልኩ ህም ! የተመንኩትን የታመንኩትን ጥንት ጥንት በልጅነት የተማርኩትን ከለስኩ ክፉ መሻቴን ምኞቴን ኮለስኩ ዘንጌን ምርኩዜን ያዝኩ የልቤን ሸለፈት ገረዝኩ ቶበትኩ አማተብኩ የጎጆዬን ቀዳዳ ወተፍኩ ጎታ ጎተራዬን መረግኩ ስብሐት ለእግዚአብሔር ብዬ ያለፈውን በምስጋና አሳረግኩ! ዝም ብዬ ስቆዝም ዝም ያልኩ የምመስል ዘገምተኛ የዱዳ ስሞተኛ ሳልናገር ሳልጋገር እ ! የሚለኝ አገር … ነክህን ነው እንጂ እንግዲህ የምን ወክ እንዲያ ወክ እንዲያ የምን ወክ እንግዲህ ወክ’ንዲህ ዘራፍ ! በብርዕ ዘራፍ ! በቀሰም ዘራፍ ! በወርቁ ዘራፍ ! በሰም … ዘራፍ ! ዘራፌ በአዲስ ራዕይ ዘራፍ ! በልዩ ምዕራፍ ዘራፍ ! እናቴ ጽዮን ወንዜ ግዮን ወፌ አሮድዮን ዘራፍ ! በደም ዕንባ በቀለም ቀንድ ዘራፍ ! ቅዱስ ዘንድ ! ዘራፍ ንጉስ ዘንድ በቀኙ ካልባረከ በግራው ካልማረከ ምን ያደርጋል እንቶ ፈንቶ ትርኪ ምርኪ በተረክ። ሀሌሉያ.... ለፓስካል ፓምፓና ፅዋ ሀሌሉያ ! © ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ)

Ý𝑖𝑙𝑎𝑘 Ġ-𝑔𝑖𝑜𝑟𝑔𝑖𝑠
Ý𝑖𝑙𝑎𝑘 Ġ-𝑔𝑖𝑜𝑟𝑔𝑖𝑠
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 06 November 2025 17:52:25 GMT
7536
385
27
61

Music

Download

Comments

habtom.son
habtom :
በብዛት ሁነን እጅግ አደነቅን
2025-11-11 14:33:18
1
endale.tesa
Endale Tesa :
አድናቆቴን እንዴት ልግለጥ ❤️❤️🤲
2025-11-07 05:53:48
3
123daniel773
123Daniel :
ሙሌዋ 😍😍😍😍😍😍😍😍
2025-11-28 16:33:12
0
nigusie.fissiha
Nigusie Fissiha :
እስገኪገባኝ ሰንቴ ላንብ፣ ስንቴ ላድምጥ? የሆነ ነጠር ግን የገባኝ ይመስለኛል። ቅኔ (ኪነጥበብ) ለዘለዓለም ትኑር!
2025-11-08 20:38:07
1
waduwrld
Wadu lll :
የንጋት ፈጅር ጎህ መቅደድ በኔ መላ እየመሰለኝ ስንቱን ዘመን አጥመነመነኝ ሰንት ግዜ አብሰለሰለኝ!! ይሌ🙏🏿
2025-11-07 11:49:51
3
user4077583630818
Walt@፳፯፻፱ :
አቤት በራሱ ድምጽ ደግሞ 👏👏 የኔ ጌታ ነፍስህን ይማረዉ
2025-11-11 19:27:53
1
adilmuha5
አዲል 🇪🇹 🇶🇦 :
አያ ሙሌ 😥🤩 ይሉዬ ወንድሜ 💙
2025-11-06 21:09:27
1
albanfam
colli Alban🇦🇱 :
አያሙሌ🥰🥰
2025-11-06 18:27:18
1
19j006
my name :
techelaleh
2025-11-07 04:07:52
1
user5668534373836
የአያ ሙሌ አገር ሰው :
ምንም አትልም
2025-11-06 18:18:52
1
userashu162
መኃልዬ መኃልይ :
አመሰግናለሁ🙏🙏🙏
2025-11-09 14:32:14
1
user6539631505255
Murad :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2025-11-07 13:35:20
1
yitu1908
ይታገሡ :
🥰👌🙏
2025-11-07 04:31:26
1
muhaba9963
muhaba :
🥰🥰🥰
2025-11-06 20:09:37
1
kidusan_andarg
kidusan 🎤🎵🎶 :
🥰🥰🥰🥰
2025-11-06 19:59:52
1
mebrsh2
Mebresh :
👌👌👌
2025-11-06 18:22:06
1
zeki......poet
zeki poet✨ :
❤❤❤
2025-11-06 18:09:33
1
jossa512
jossa512 :
😁
2025-11-20 15:16:59
0
ms937312
ms olds :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2025-11-14 16:46:38
0
dubalemelak
Dubale Melak (Gudu Gena) :
😳😳🥰🥰🥰🥰🥰
2025-11-08 18:40:24
1
19j006
my name :
lelochenem chemerelegn ebakh
2025-11-07 04:08:14
1
To see more videos from user @yilupanda, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About