@tigstawek4: ፀፀት 💔 እኔ የ34 ዓመት ሴት ነኝ። ከቀድሞ ባለቤቴ ጋር ስድስት የትዳር ዓመታትን አሳልፌያለሁ መልካም ዓመታት ነበሩ:: ከመጋባታችን በፊት ምርጥ ጓደኛሞች ነበርን ቀስ በቀስ ተዋደድንመዋደዱ ወደፍቅር አደገ:: የዩንቨርስቲ ትምህርቱን እስኪጨርስ ታገስኩት:: ሥራ እስኪያገኝ ድረስ ጠበቅኩት። ቤተሰቦቻችን ግንኙነታችን አወቁ፤ መጀመሪያ ላይ የእኔ ቤተሰቦች ቢቃወሙም እስከህይወቴ ፍጻሜ የግሌ ይሆናል ብዬ ካመንኩት ፍቅረኛዬ መለየት አልቻሉም። ፈጣሪ ሲፈቅድ ሁሉም ነገር ተሟልቶ ተጋባን። የሚያምር ወንድ ልጅም ወለድን። አሁን የሰባት ዓመት ልጅ ነው። ባሌ በጣም ጥሩ ሰው ነበር፤ ቤቱን፣ ሚስቱንና ልጁን የሚወድ የትዳር አጋሬ ነበር። ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ 'ቱግ' ባይ ቢሆንም ወዲያው ይቀዘቅዝ ነበር። ይሁን እንጂ ልጅ ከተወለደ በኋላ እውነተኛው ችግራችን መጉላት ጀመረ። ልጅ መያዝ፣ ማጠብ፣ መመገብ . . . የእኔ ስራ አደረገው። ልጁን ለመንከባከብ ራሴን አለመጠበቄ እንደመቆሸሽ ይቆጥረው ጀመር። የሚደክመኝ አይመስለውም። በዚህ ምክንያት በተጨቃጨቅን ቁጥር ሻንጣዬን ጠቅልዬ ወደ ቤተሰቦቼ እሮጣለሁ። እህቶቼ ይደውሉና ይጮሁበታል። ካልተንከባከብካት "እንፈልጋታለን" ይሉታል፤ ጭራሽ እንደማልመለስ ያስፈራሩታል። 'ከፈለግክ ፍታት" እያሉ ያዋክቡታል። እኔ ግን የእውነት ፍቺ አልፈልግም ነበር። ያም ሆኖ በእህቶቼ መከታነት በኩራት ተሞልቼ ነበር። ደካማና ተሸናፊ መስዬ መታየት ፈጽሞ አልፈለግኩም። አንድ ቀን በጣም ከልክ በላይ ገፋሁት። መታኝና በሩን ዘጋሁበት። ሶፋ ላይ ተደግፎ አደረ:: በማግስቱ በጠዋት ወደ ቤተሰቤ ሮጥኩኝ፣ ነገርኳቸው፤ ሁሉም ሰው እኔ ተጎጂ እንደሆንኩ አመነ። እህቶቼ ተሯሩጠው አሳሰሩት። እውነታው ግን ባለቤቴን በስሜት ስጎዳው የነበርኩት እኔ ነበርኩ። እሱ ፈጽሞ ጠበኛ አልነበረም። ከሁለት ቀናት እስር በኋላ ሽማግሌዎች ልኮ ይቅርታ ጠየቀኝ፤ ክሱን አነሳሁለት፤ ሲወጣ ቤተሰቤ ፊት ተንበርክኮ እያንባ ዳግም ይቅርታ ጠየቀኝ። ታርቀን ተያይዘን ወደቤት ሄድን። ከሶስት ወራ በኋላ እንደገና ትንሽ አለመግባባት ተፈጠረ፤ እንደተለመደው ልብሶቼን ጠቅልዬ ወጣሁ። ከሁለት ቀናት በኋላ ሆስፒታል እንደገባ የሚገልጽ ስልክ ደረሰኝ። ቤተሰቦቼ እንዳልሄድ ከለከሉኝ፤ “ተስፋ የቆረጥሽ ይመስለዋል፤ ይኮራብሻል” አሉኝ። ለአንድ ሳምንት ሆስፒታል ቆየ። ሲወጣ መጥቶ ይቅርታ ይጠይቃል ብዬ ስጠብቅ ቀረ። ሁለት ሳምንታት አለፉ። በጣም ናፈቀኝ። ቤቴ መመለስ በጣም ፈለግኩ። ልጄም አባቴ እያለ ቁም ስቅሌን አሳጣኝ። ሆኖም ቤተሰቦቼ በተለይም እህቶቼ ስንት በደል እንደደረሰብኝ ነግሬያቸው ይቅርታ ሳይጠይቅ መሄዱ በጣም ከበደኝ። ከዛሬ ነገ ሽማግሌ ይልካል ወይም መጥቶ ይቅርታ ይጠይቃል ብዬ ስጠብቅ 21 ቀናት ተቆጠሩ:: በ21ኛው ረፋድ የፍርድ ቤት የፍቺ ጥሪ ወረቀት ደረሰኝ። ፈጽሞ አላመንኩም:: አሁንም ሀሳቡን እንደሚቀይር ተስፋ አደረግኩ:: ግን ኩራቴ “አትለምኚው፤ አትሸነፊ” አለኝ። እናም ለመፋታት ፈቃደኝነቴን ላኩለት። የፍርድ ቤት ቀጠሮ ከመድረሱ በፊት ንብረት መካፈል እንደምፈልግ መልእክት ላኩለት። ምንም መልስ አልሰጠኝም። "ንብረት ጥላልኝ ትሄዳለች፤ ሌላ አገባበታለሁ" ብሎ እንዳያስብና የፍቺ ጥያቄውን እንዲተው ነበር ይሄን ያደረግኩት። መልስ አለመስጠቱ "ትተውልኛለች" ብሎ አስቦ ሊሆን እንደሚችል የነበረኝን ግምት አጠናከረልኝ። ስለሆነም በፍርድ ቀጠሮው ቀን እንደትልቅ አጀንዳ ይዤው የቀረብኩት የጋራ ንብረታችን ድርሻ እንዲሰጠኝ ነበር። ዳኛው በንብረት ላይ አስተያየት ሲጠይቁት “አንድ ላይ ያፈራነው የጋራ ንብረት ሁሉ መካፈል አልፈልግም። ሁሉም ነገር ለብቻዋ ትውሰድ፤ እኔ የምፈልገው ልብሴንና ሰላሜን ብቻ ነው” አላቸው። ያ ቀን ሀምሌ 16/2014 ነበር፤ ፍርድ ቤቱ በሽምግልና እንድንታረቅ እድል ቢሰጠንም ፍቃደኛ አልነበረም። እኔም መሸነፍን በፍጹም አልፈለግኩም። ከሁለት ወራት በኋላ የፊቺ ሂደቱ ተጠናቅቆ የጋብቻ ወረቀታችን ተቀደደ። የትዳር ህይወቴ ተቀደደ። አሁን እሱ ድጋሚ አግብቶ አንድ ልጅ ወልዷል። እኔ ግንፊቱን በብቸኝነት እየተንገዳገድኩ ነው፤ እንድፋታ ሲያበረታታኝ የነበረው ቤተሰብ አዙሯል:: በተለይም እህቶቼ መልሰው እኔን ያሙኛል፤ አያከብሩኝም። እናቴም ከእኔ ይልቅ ታናናሾቼን ነው የምታከብረው:: ሁሉም በተሳሳተ ምክር ከጥሩ ባሌ ነጥለው ባዶ አደረጉኝ። ቤቴንና ትዳሬን እንዲያፈርሱ ፈቅጄ በቁጭት እሳት እየተለበለብኩኝ ነው። የተረፈኝ ፀፀትና ልጄ ብቻ ነው። አንዳአንዴ የጋብቻ ፎቶዬን እያየሁ አለቅሳለሁ፤ ሳላስበው ልጄን አስለቅሰዋለሁ። እህቶቼ ከእኔ ተማሩ።🙏 #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር✝️❤ #yppppppppppppppppppppppp #ethiopian_tik_tok🇪🇹 #ethiopia

Tigist Awoke የክርስቶስ እስረኛ ✝️❤️
Tigist Awoke የክርስቶስ እስረኛ ✝️❤️
Open In TikTok:
Region: SA
Thursday 20 November 2025 18:58:19 GMT
107630
7319
119
672

Music

Download

Comments

helinakassahun8
Hk✨🌸 :
የወንድ ልጅ እንባ ከባድ ነዉ ያዘነብሽ ይመስለኛል የራሱ ህይወት አሁን ላይ ቢኖረውም አንቺ ግን ይቅርታ ጠይቂው ዳግም ለመመለስ ሳይሆን ይቅርታ ከልቡ እንዲያደርግልሽ ከዛ የራስሽን የሆነ ህይወት እግዚአብሔር ይሰጥሻል ጸልይ አይዞሽ
2025-11-22 18:16:14
50
mekdes4528
K...A🦋 :
የኔ እናት እመብርሀን ካችጋ ትሁን🙏
2025-11-20 19:17:03
91
zeni696
user9412491906181 :
አይዞሽ ስውሯ ማርያም ንሂጅ መፍትሄ አላት
2025-11-21 06:49:29
28
alemayehu2013a
alemayehu2013 :
መታሰቢያነቱ ጋብቻ ሳይገባቸው ልጅ ለሚድሩ ወላጆች ይሁንልሽ
2025-11-23 12:03:36
7
girmish008
Girmish Ab :
ክፉ ቤተሰብ ሲኖረን እንዲህ ለፀፀት የሚዳርግ ህይወት ውስጥ ይከቱን እና ዘወር ይላሉ።እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይሁን ''ገጠመኝ'' ትምህርት አዳምጭ መምህሩ ተስፋየ አበራ ይባላል የቤተሰብሽን ሁኔታ አንቺን ራስሽን ከትምህርቱ ታገኚዋለሽ....
2025-11-21 10:12:57
44
betelehemteklehay
bety gitim(ቀና ልብ) :
አይዞሽ ጠንካራ ሁኚ🥰🥰🥰
2025-11-21 03:53:40
11
yaredtena
yared ya mariyam :
ትዳር ውስጥ ቤተሰብ እንዲሁም ጋደኛ ባጠቃላይ ሶስተኛ ወገን አያስፈልግም የትዳር ማነቆ ናቸው በእርግጥ እኔም አደለም ቤተሰብ ማንም እዲገባ አልፈልግም እሷም እኔም ለልጃችን መኖር እንዳለብን መተማመን አለብን ምክንያቱም ልጅ ትልቁ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ በመሀል አለመግባባት ሊፈጠር ይችላል ግን መወያየትን የመሰለ ነገር የለም ሁሉም ነገር መፍተሔ አለው ብዬ ስለማምን ነገሮች ግን ከረው ከሄድ ወደ ድንግልማርያም ልጅ ወደ መዳኒያለም መሮጥ እሱ የጠመረውን እሱ እንዲያስተካክለው ለሱ መስጠት ነው (እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቀን) ።
2025-12-01 08:22:55
2
user5061109695216
ባቢ👍 :
አይዞሽ እህቴ በርቺ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው
2025-12-02 09:14:23
4
tiegsthaylu808
Tigi ❤❤ :
አይዞሽ ታሪክሽን ስላካፈልሽኝ ከልቤ አመሰግናለሁ
2025-11-20 19:33:53
22
user35110543704211
kalkidan yemaryam :
ልጅ ከተወለደ በኋላ ትዳር ባይፈርስ ጥሩ ነው በጣም ያማል
2025-12-03 16:07:29
2
tegeneshet
TEGENU ESHETU :
አይዞን
2025-12-04 19:38:02
0
user715696630521
ልጀ ውበቴ ነው :
በጣም አስታማሪ ታሪክ ነው እውነትም ፀፀት እመብርሀን ትደግፍሽ
2025-12-05 09:21:44
0
.xender5
🦋መሢ➩ዘ➩ጎንደር💪➩በጌምድር💚💛❤️🔒 :
አይዞሽ 🙌🙌🙌
2025-12-05 13:47:54
0
mazaalelign
Maza Alelign :
kebade new🥺🥺🥺
2025-11-21 04:56:30
1
teshomegudeta15
DALIMA :
ከትዳር በኃላ ቤተሰብ?! 😳
2025-11-22 11:00:05
1
hlina.mesfine
hlina 123 :
🙏🙏🙏አይዞሽ እህቴ ሑሉም ነገር ያልፋል
2025-11-24 04:51:14
0
kaffawit59
kiya :
ፈጣር ያጽናናሽ
2025-11-28 16:23:01
0
tadman0444
tadiye0444 :
አይዞሽ እህታችን ሁሉም ያልፋል እመብርሃን ትርዳሽ
2025-12-04 06:56:00
1
m1167339
ስለሁሉም ነገር እግዚአብሄር ይመስገን :
እግዚአብሄር ካቺጋ ይሁን እህት🙏
2025-11-30 01:06:45
0
abica1213
nahom :
እህትየ ፈጣሪ ይርዳሽ
2025-11-22 17:30:19
6
keriketema0
𝕙𝕖𝕣𝕠𝕟 𝕜𝕖𝕥𝕖𝕞𝕒 :
አሜን(፫)🙏🙏🙏🙏
2025-11-25 06:14:57
0
user85073739992224
Jon :
ያሳዝናል ፈጣሪ ማስተዋሉን ያድለን በትዳር 3ኛ ወገን አያስፈልግም
2025-11-21 07:29:39
11
silondis26
Habtamua Eshetu :
ምን ታረጊ አንቺ እግዚአብሄር የፃፈልሽን ህይወትኸ እየኖርሽ ነው ላለፈ ነገር እንዳትፀፀች እኔም እንዳንችው ነኝ እና የተሻለ እንደሚመጣ አምናለው
2025-12-01 19:55:27
0
ymaryamlji
የማርያም ልጅ :
ታውቃለሽ የህቴ ታሪክ ነው ማስተዋል ትባላለች በጣም ነው የምወዳት በጣም ቆጆ ትዳር ነበራት በነገራችን ለይ የኔም ታሪክ እደዛው ነው ልዩነት እኔ ተፋትቸ ወደቤተሰባ አለድሁም እሱ ብቻ ነው ልዩነቱ እህቴ ግን እስካሁንም ቤተሰብ እየናቃት እያግጠጣት አለች ምን እደማረጋት አላቅም እኔ ስደት ነኝ
2025-11-23 13:51:44
0
hana.marym3
እመብርሃን የልቤ ብርሃን :
እኔም ቆይቶ የገባኝ በጋብቻ መሃል ፫ 3 ኛ ወገን አያስፈልግም አሁንም ጸልይ ልዑል እግዚያብሔር መልካም ህይወት ይስጥሽ
2025-11-23 16:35:04
0
To see more videos from user @tigstawek4, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About