@manemyedbli: በዛው ቅፅበት ስልኬ ጠራ ፀሎት ነበረች። እያለቀስኩ እንደነበር እረሳሁት። ሄሎ አብርሼ ቤት ገባህ አለችኝ አዎ ገብቻለሁ እናንተስ አልኳት። እኛማ ገና ወደቤት አሌድን ሰዎቹ እዚህ ለማደር አስበዋል መሰለኝ እይቢ አሉኦ አለችኝ። ያው አንቺን ለማስደሰት ለማገዝ ነዋ ደሞ በጣም ደስ ምትሉ ቤተሰቦች ናችሁ አልኳት። እናመሰግናለን አረ አማዬ እራሱ የተረጋጋ ሰው ነው ደስ ይላል እንደዚህ ሰከን ያለ ልጅ እያለች ነበር እኔማ ጉዱን አላወቅሽ ድንቄም መስከን እያልኩ ብቻዬን ስስቅ ነበር አለችና ሳቀች። ሳቋ ተጋባብኝ ምን እንዳሳቀኝ ባላውቅም አብሪያት ሳኩኝ የተወሰነ እኔ ከሄድኩ ቡሀላ የሰሩትን ነገረችኝና ስልኩን ዘጋሁት። ከዛ ወደቤት ገባሁ ቀጥታ ወደ አልጋዬ ገብቼ ልብሴን ቀያይሬ ተኛሁ። የማልዋሸው ነገር በጣም እርቦኝ እንደነበረ ነው። የፀሎት ሱቅ ተሰርቶ ሙሉ ፊኒሽንጉ አለቀ። ስራ ጀመረች። የፀሎት ሱቅ ከኛ ቤት ቀጥታ እንደወጣን ከምናገኘው አስፋልት ተሻግሮ ባለው ሌላኛው አስፋልት ነበረ። ፀሎት ስራ እንደጀመረች ሙሉ ዘመዶቿ አክስቶቿ እየመጡ እየተሰሩ መረቁላት። እነሱ መምጣት ግር ግር ማለት ሲያቆሙ ግን ደንበኛ ብዙም አልመጣ አላት። ቤቱ ትልቅ ስለሆነና አካባቢው ላይ ካለው ኩልስታፍ ስለሆነ ሰዎች ዋጋው በጣም ውድ ነው በሚል አስተሳሰብ ደፍሮ እሷጋ ገብቶ ሚሰራ ሰው ጠፋ። ለሷ እኔ ጨነቀኝ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ምንም ከስተመር ሳይኖራቸው ጠዋት ገብተው ማታ ይወጣሉ። ከብዙ ጭንቀት ቡሀላ ለእናቴ እህቶች (ለአክስቶቼ) ደውዬ እንዲሰሩ ዋጋው ኖርማል እንደሆነና የወንድሜም ሚስት እንደሆነች ነገርኳቸው ሁለቱ አክስቶቼ እሺ አሉኝ። ከዛ ውጭ በፊት ላይ የማወራቸው ሴቶችጋ እየደወልኩ እናንተ ሰፈር ላይ የተከፈተውን አዲሱን ፀጉር ቤት አይታችሁታል ሲያምር ህዝቤ እዛ እየተሰራኮ እኛ ላይ እየጎረሩብን ደሞ ሲያምር vip የሆነ ፀጉር ቤት ነው ማርካን ይባላል ፀጉር ቤቱ በላይኛው አስፋልትጋ ያለው እያልኩ ለሁሉም እየደወልኩ ነገርኳቸው። ፈጣሪ ይባርካቸው ሰው ወረተኛ አደለ አንዱ ገብቶ ተሰርቶ ለሌላው ይናገራል ብቻ አንዱ ለአንዱ አንዱ ለአንዱ እየነገረ ሰዎች መምጣት ጀመሩ። የሰፈሩ ልጆችም ደንበኞቻቸውን እየተው አዲስ የተከፈተው ትልቁ ፀጉር ቤት ነው የተሰራሁት እያሉ በራሳቸው ፕሮሞሽን ሰሩላት። እንዳሉት ቃላቸውን ጠብቀው አክስቶቼም ሄደው ተሰሩ ሲመለሱ ለእናቴ ደውለው። ታምራትማ በዚህ ፀባዩ እንደዚች አይነት ልጅ አይጠብስም መርጌታጋ ሄዶ አስገድግዶባት ነው እንጂ ብለው ሙድ እንደያዙም ማዘር ነገረችኝ። ፀሎት ስራዋ እስኪስተካከል በደንብ ቤቱ እስኪለምድ ትታ መሄድ ስለማትችል ወንድሜን መጠየቅ አቆመች ግንኙነታቸው በስልክ ብቻ ሆነ። ለምን እንደሆነ ባላውቅም ደስ አለኝ የሷ አለመሄድ ለኔ ጀብድ መሰለኝ። ቴሌግራም ቻናላችን mane1219 #mane #ስነፅሁፍ #እውነተኛ_ታሪክ #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #fyp
✍️✍️
Region: ET
Sunday 07 December 2025 17:42:02 GMT
Music
Download
Comments
nebi6526 :
second😁😁
2025-12-07 18:35:55
3
እናቴ የመኖሬ ትርጉም 😍 :
first
2025-12-07 17:47:03
3
@"yemi" :
1 chemrin 🥰🥰
2025-12-07 18:47:48
1
Rose 🦅🦅 :
fifth🥰🥰
2025-12-07 20:09:49
1
bezi :
👏👏👏👏
2025-12-07 18:41:57
1
karlos :
🥰
2025-12-07 21:26:04
1
To see more videos from user @manemyedbli, please go to the Tikwm
homepage.