@ethel369ethiopia888: "ሰኔ እና ሰኞ... አይግጠም" ሰኔ እና ሰኞ አይግጠም የሚለው የቆየ የአባቶቻችን አባባል ዘንድሮም በ 2018 ዓ.ም. በአይናችን ልናየው በትክክል ገጥሟል። ሰኔ 1 ቀን ሰኞ ይውላሎል። ከ 1979 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዛሬ... በከፊል እንይ እስኪ.. 1)1979 ዓ.ም. ( ዘመነ ማቲዎስ) በ1979 ዓ.ም. ሰኔ እና ሰኞ ሲገጥም አገሪቱ በከባድ ፈተና ውስጥ ነበረች የ1977ቱ ታላቁ ድርቅ መዘዝ እና በወቅቱ የነበረው የዝናብ እጥረት ተከስቶ ነበረ። 2) 1984 ዓ.ም.( ዘመነ ማርቆስ) በዚህ ወቅት ሰኔ እና ሰኞ በድጋሜ ገጠሙ። ህይ ዓመት የሽግግር ወቅት ቀውስ እንደነበረ የታሪክ መዛግብቶች በጥልቀት ያወሱናል። በዚህም ወቅት በመላው አገሪቱ ከፍተኛ የጸጥታ መደፍረስ ና ግጭት ነገሰ። 3) 1990 ዓ.ም. ( ዘመነ ማርቆስ) በዚህም ወቅት ሰኔ እና ሰኞ ሲገጥም በአገሪቱ ላይ ሊላ የደም ምዕራፍ ተከፈተ።በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተነሳው እጅግ አስከፊ የነበረው የባድሜ የድንበር ጦርነት በዚሁ አመት ፈነዳ። 4) 1997 ዓ.ም. ( ዘመነ ዮሐንስ) በ 1997 ላይ ደግሞ ታሪኩ ይበልጥ ልብ ሰባሪ ሆኗል።1997 ሰኔ እና ሰኞ ገጠመ። ያ ታዋቂው እና ውጥረት የበዛበት አገራዊ ምርጫ 97 የተካሄደው በዚህ ወቅት ነበር። 5) በ2007 ዓ.ም. (ዘመነ ዮሐንስ) ከ 10 ዓመታት በኋላ በ 2007 ዓ.ም. በድጋሜ በዘመነ ዮሐንስ ሰኔ እና ሰኞ ገጠሙ። 6) 2013 ዓ.ም. (ዘመነ ማርቆስ) በቅርብ ጊዜ ትውስታችን በሆነው በ 2013 ዓ.ም. ሰኔ እና ሰኞ በድጋሜ ገጠሙ። በዚህም ወቀት የጦርነት የጭንቀት የከበሮ ድምፅ የነበረ መሆኑን ሁላችንም እናስታውሳለን። የታሪክ ፍሰት አያችሁ? አሁን ደግሞ ወደ ዘንድሮ እንምጣ። ዘንድሮ 2018 ዓ.ም. ነው።አመቱም ድጋሜ ዘመነ ማርቆስ ነው! ሰኔ እና ሰኞ ገጥመዋል። እንደ 1997ቱ, እና 2007ቱ ሁሉ:ዘንድሮም ሰኔ እና ሰኞ በዘመነ ማርቆስ ላይ መውደቃቸው ታዘባቸሁ? ታሪክ እራሱን ይደግማል? ወይንስ እኛ ካለፈው ተምረን ራሳችንን እና አገራችንን እንጠብቃለን? የዘንድሮው የሰኔ እና ሰኞ ገጠመኝ ለኢትዮጵያ ወጣቶች የጥንቃቄ የማስተዋል እና የሰላም ጊዜ ይሁንልን። አባቶቻችን በምክንያት ነው << ሰኔ እና ሰኞ >> ያሉት አስተውሉ ! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ኢት-ኤል ዘ-ኢትዮጵያ🔝➌➏➒⛳️
Region: ET
Monday 01 June 2026 09:31:41 GMT
Music
Download
Comments
Mosisa Tiye :
የዘንድሮ ሰኔና ሰኞ የእድገትና የለዉጥ ዘመን ይሆናል አትጠራጠሩ ጎበዝ 🥰🥰🥰🥰
2026-06-03 08:58:14
69
ጎጃም መርዓዊ :
ግን 2012 ሰኔ ሰኞ ሁኗል
2026-06-03 08:03:39
7
Abe Tadese :
2007
2012
2026-06-03 18:57:10
0
ሉዕል :
እረ 2012 ውሏል
2026-06-03 14:56:58
3
መልዓክ🌹🥀 :
🥰🥰🥰 ግሩም ነው
2026-06-03 19:12:09
1
Semu :
የትኛውም አመት ካለ ጭንቅ አላሳለፈችም ሁሌም ሰኔ እና ሰኞ ነው
2026-06-03 14:33:07
5
miyk :
1997 ሰኔ 1 እሮብ ቀን ነው የዋለው
2026-06-03 18:18:55
1
Habesha :
ሟርተኛ
2026-06-03 17:12:04
0
mesfin A :
ዳግማዊ 2012 ሆነ
2026-06-03 16:34:04
1
B ነኝ🌏 ታማኟ ዱርየ ✋ :
እና ችግሩ ምንድነዉ🤔🤔
2026-06-03 15:42:50
0
ከተፃፈ አይቀርም :
አሁን ደግሞ እሁድ ነው 30 የሚሆነው
2026-06-03 15:27:51
0
Hiwot zenbaba :
አሜን እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ
2026-06-03 16:19:13
1
ዕፀ -መለኮት በ ዕፀ -መግስት :
ዘንድሮዘመንዮሐንስ ነው እንዴ
2026-06-02 20:02:16
0
👉ልኑር በተስፋ💚💛❤️🇪🇹😏 :
ሰኔ እና ሰኞ ከገጠመ ወበከቱ ነው
2026-06-03 13:32:13
1
Abel tapiseri :
በጣም የሚያስፈራ ይመስላል
2026-06-03 12:46:11
1
zerhiun :
ስኔ እና ስንዴ
2026-06-02 04:51:13
7
M :
Obviously it was hard time for all.
2026-06-03 17:43:35
0
Alemayehu :
2012 ዓ,ም
2026-06-02 19:01:51
1
Yebnahu :
ሰኔ 1 2013 ማክሰኞ ቀን ነው የዋለው
ሰኔ 1 1997 ዕረቡ ቀን ነው የዋለው
ሰኔ 1 1977 ቅዳሜ ቀን ነው የዋለው
2026-06-03 18:01:06
5
Ethiopian coffee bnan :
እውነት። ነው
2026-06-02 15:52:14
1
mele=መለኝው :
የባሰ ነው
2026-06-03 19:01:06
0
Sisay love :
አሜን ለሁላችንም ልቦና ይስጠን
2026-06-03 19:04:34
0
Qeeeee :
Amen🙏🙏🙏
2026-06-03 19:20:59
0
tigist aragaw :
ሠላሙን ያምጣልን መድሃኒዓለም
2026-06-03 19:27:56
0
Zekariyas :
1997 ሰኔ እሮብ ነበር
2013 ሰኔ ማክሰኞ ?!?!?!?
2026-06-03 18:44:35
0
To see more videos from user @ethel369ethiopia888, please go to the Tikwm
homepage.