@kidanemihret3: ታህሳስ 3 /፫/ በዚች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው ። እርሷ ለእግዚአብሔር የስእለት ልጅ ነበረችና ። እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ የሌላት ስለሆነች በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ከሴቶች ተለይታ ርቃ ትኖር ነበር ሽማግሌ ከሆነ ከኢያቄም ከባሏ ጋርም እጅግ የምታዝን ሆነች ። እግዚአብሔርም ኀዘናቸውን ሰማ ቅድስት ሐናም እንዲህ ብላ ለእግዚአብሔር ተሳለች የሰጠህኝን ፍሬ ለእግዚአብሔር አገልጋይ አደርገዋለሁ ። ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምንም በወለደቻት ጊዜ ሦስት ዓመት በቤቷ ውስጥ አሳደገቻት ከዚህም በኋላ ከደናግል ጋር ትኖር ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደቻት በቤተ መቅደስም ምግቧን ከመላእክት እጅ እየተቀበለች ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረች ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም መጥቶ ከእርሷ ሥጋን እስከ ነሣ ድረስ ። ከሴቶች ሁሉ የተመረጠች ይቺ ናት በቤተ መቅደስም በመኖር ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲፈጸምላት እርሷ ለእግዚአብሔር የተሰጠች የስዕለት ልጅ ናትና ለሚጠብቃት ይሰጧት ዘንድ ካህናት እርስበርሳቸው ተማከሩ በሴቶች ላይ የሚደርስ በርሷ ላይም ይደርስባታል ብለው ስለፈሩ በቤተ መቅደስ ውስጥ ይተዋት ዘንድ ለእነርሱ ትክክል መስሎ አልታያቸውም ስለዚህም ሊጠብቃት ለሚገባው በእርሷ ላይ እጮኛ ሊአኖሩ ወደዱ ። ከዚህም አስቀድሞ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልጄ ማርያም ሆይ አንቺ እንዳደግሽና ለአካለ መጠን እንደደረስሽ ዕወቂ ልትታጪ ትወጃለሽን እግዚአብሔርን የሚፈራ መልካም የሆነ የተባረከ ጐልማሳ እንፈልግልሽን ወይም በሕይወትሽ ዘመን ሁሉ በቤተ መቅደስ ተቀምጠሽ እግዚአብሔርን ልታገለግዪው የምትሺ ከሆነ በሴቶች ላይ የሚደርሰው በሚደርስብሽ ወራት ወደ ቤተ መቅደስ ደጅ ከመግባት ትጠበቂ ዘንድ በኦሪቱ የተጻፈውን የርግማን ሥርዓት በአንቺ ላይ እንሠራለን አላት ። ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋዩ በፊታችሁ ነኝ አባትና እናት የሉኝም ስሙ ቡሩክ ምስጉን ከሆነ ከእግዚአብሔር በታች በእናትና አባት ፈንታ እናንት ናችሁና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንደምታውቁ አድርጉ ብላ መለሰች ። ካህናቱና ማኅበሩም ሁሉ ዘካርያስን ወደ ቤተ መቅደስ ገብተህ ስለዚች ብላቴና ማርያም ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት ዘካርያስም ገብቶ ሲጸልይ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ። ዘካርያስ ሆይ ወጥተህ ከዳዊት ወገን ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን ሁሉ ወንዶች ሰብስብ የየአንዳንዱንም በትር ከስሙ ጋር ውሰድ ወደ ቤተ መቅደስም በምሽት አግብተህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይበት በነጋ ጊዜም በትሮቻቸውን አውጣ እግዚአብሔርም በበትሩ ላይ ምልክት ለገለጠልህ ለዚያ ሰው ማርያምን ተቀብሎ ሊጠብቃት ይገባዋል ። ካህኑ ዘካርያስም ወጥቶ አንድነት ለተሰበሰቡት ሕዝብ የእግዚአብሔር መልአክ የነገረውን ነገራቸው በዚያንም ጊዜ ከዳዊት ወገን ጐልማሳም ቢሆን ሽማግሌም ቢሆን ሚስቱ የሞተችበት ሁሉ በኢየሩሳሌም ወደአለ ቤተ መቅደስ ይሒድ እያሉ ዓዋጅን ዙረው የሚናገሩ በእስራኤል አገር ሁሉ ላከ ። ከዳዊት ወገን የሆነ ጠራቢው ዮሴፍም በሰማ ጊዜ በትሩን ይዞ ከናዝሬት ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ካህኑ ዘካርያስም የሁሉንም በትሮች ተቀብሎ ስማቸውን በላያቸው ጻፈ ቁጥራቸውም አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ሆነ ዘካርያስም በትሮችን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እንዲሁም ሰዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ውጭ ቁመው ይጸልዩ ነበር ዘካርያስም ጸሎቱን በፈፀመ ጊዜ ለየአንዳንዱ በትራቸውን አውጥቶ ሰጠ ጠራቢው ዮሴፍም በትሩን ሊቀበል በቀረበ ጊዜ ከእርሷ ነጭ ርግብ የመሰለች ተገለጠች እየበረረችም ሒዳ በጠራቢው ዮሴፍ ራስ ላይ ተቀመጠች ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ አይተው እጅግ አደነቁ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ። ዘካርያስም ዮሴፍን ዮሴፍ ሆይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ እንደ ተናገረ ድንግል ማርያምን ወደ ቤትህ ወስደህ ጠብቃት አለው ዮሴፍም ቅድስት ድንግል ማርያምን ከካህናት እጅ ተቀበላት በእርሱም ዘንድ ኖረች ። ከዚህም በኋላ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ስለ እግዚአብሔር ልጅ ከእርሷ ሰው ሁኖ ስለመወለዱ በዮሴፍ ቤት አበሠራት ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር #funny #ኪዳነምህረትእናቴ #አቡነተክለሀይማኖት #brook90days #broochallenge #brooknews #brookperspective
ኪዳነ ምሕረት እናቴ።
Region: ET
Thursday 12 December 2024 05:49:19 GMT
Music
Download
Comments
🧚♀️💅☕️ :
የኔ ባለማተብ ህዝብ🥰እናቴ ህዝብሽን ጠብቂልን😥😥
2024-12-12 10:01:27
14
user5395010471249 :
እንኳን አደረሳችሁ።
2024-12-12 08:36:50
8
Birhan Sewnet :
እናቴ ባዕታ
2024-12-12 17:38:33
0
user1626392481997 :
ንፁሁን ለ ዉሾች አትስጡ አሜን 3
2024-12-12 14:13:46
3
romi :
🥰🥰🥰🥰 bata enate
2024-12-12 07:13:55
6
Emnte :
የኔ እናት
2024-12-12 10:42:55
4
Tigist :
እንኳን አደርሳቹህ አደርሰን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2024-12-12 12:25:38
2
etsegi :
እመቤቴ የኔናት ንፅህይተ ንፁሀን
2024-12-12 09:50:21
3
Nani Abebe :
yamet sew yebeln ባዕታ ለ ማርያም እናቴ
2024-12-12 13:35:21
1
Helu :
ባህርዳር በዓታ ማርያም 🥰🙏
2024-12-12 11:19:19
2
yehunetesefahun :
እኩን አደርሳችሁ
2024-12-12 09:33:59
2
sol m :
ማርያም ማርያም ማርያም 🥰🥰🥰🥰🥰
2024-12-12 12:06:53
2
enatalemlingerh :
እልልልልልልልልልል 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2024-12-12 08:20:37
2
user421315002815 :
አሜን
2024-12-12 12:12:31
2
Birhan Aytegeb :
ድንግል ማርያም እናቴ የዛሬ አመት በሠላም ታድርሰን ታድርሳችሁ ለደጇም ታብቃን
2024-12-12 16:35:23
1
himen ye mirame lje :
enata bata abzche ymwedsh yngrkweshen idera🥰🥰🥰
2024-12-12 12:33:26
2
Lij arsema Sami :
ያብዛን ጨምሮ ደሥስንል
2024-12-12 15:39:51
1
Declan :
13
2024-12-12 17:41:05
0
ቃል የ ቅድስት አርሴማ ልጅ 6❤ :
ኦሮቶዶክስ መሆን እኮ መታደል ነው ይክበር ይመስገን የድንግል ማርያም ልጅ❤🙏❤🙏❤🙏
2024-12-12 17:44:04
0
Ababa Lakaw :
333333333333333333333
2024-12-13 19:25:03
0
Tigist Amare :
🥰🥰🥰🥰🥰
2024-12-12 07:24:37
3
habtamu :
🥰🥰🥰
2024-12-12 06:52:35
3
Hunter Bloomfield :
🍰
2024-12-12 13:38:24
2
amen amen amen 🙏 :
🙏🙏🙏
2024-12-12 12:33:10
2
Mahanaym Ayanaw Emuye :
🥰🥰🥰
2024-12-12 12:22:17
2
To see more videos from user @kidanemihret3, please go to the Tikwm
homepage.